ዲያስፖራው አማራ ኦሮሞ ትግሬ ወላይታ እየተባባለ እርስ በእርሱ ሲባላ በአንፃሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ስቃይ ውስጥ ይገኛል – #ኤርሚያስ_ቶኩማ

ሳተናው
By ሳተናው February 2, 2017 13:49

ዲያስፖራው አማራ ኦሮሞ ትግሬ ወላይታ እየተባባለ እርስ በእርሱ ሲባላ በአንፃሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ስቃይ ውስጥ ይገኛል – #ኤርሚያስ_ቶኩማ

ልጆቻቸውን በእስርና በሞት ያጡ እናቶች አሁንም እንባቸው አልቆመም ባለቤቶቻቸው የታሰሩባቸው ኢትዮጵያውያን ሚስቶች ልጆቻቸው እና በእስር የሚገኙ የትዳር አጋራቸው እንዳይራቡ በሴትነት ጉልበት ዛሬም ይንከራተታሉ፤ ቅድሚያ ለነፃነት ያሉ እንደነወይንሸት ሞላ፣ እየሩሳሌም ተስፋው እና ሌሎችም በየእስር ቤቱ የሚደርስባቸው ስቃይ ብዙ ነው፤ የታሪክ ፀሐፊው አንድሪው ሒልተን The Ethiopian Patriots “Forgotten Voices of the Italo-Abyssinian war 1935-41   በሚለው መፅሐፉ ላይ ስለኢትዮጵያዊያን ሴቶች እንዲህ ይለናል “በዚህ አለም ማንም ሴት እንደ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ቀን ከለሊት ሳይለዩ፣ ሳይደክሙ፣ ሳይሰለቹ ጦሩ ወደጉዞ ይዞት የሚሄደዉን ስንቅ በማዘጋጀት ዉሀ በእንስራ ተሸክመዉ ከተራራ ተራራ በማጓጓዝ በማቅረብ የሚሠሩ ጠንካራና ብርቱ ሴቶች የሉም” ሲል የሀገራችንን ሴቶች ይገልፃቸዋል።

ሐሚልተን የገለፀው የኢትዮጵያውያን ሴቶች ስቃይ ዛሬ ላይ ቢብስ እንጂ አያንስም ይህ ሁሉ ስቃይ በሀገር ቤት እያለ አሁንም ዲያስፖራው ምንም ጠብ የሚል እንቅስቃሴ ሳያደርግ በየስብሰባ አዳራሹ እርስ በእርሱ ሲነታረክ ይውላል። አንዳንዱ የአሜሪካ ዜግነቱን እንደተቀበለ የጎሣ ስም እየጠቀሰ ኢትዮጵያዊ አይደለም ይላል፤ እኔ በግሌ የማውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ጎሣ የለም ባይሆን ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ፖለቲከኞች ከተቃዋሚውም ከገዢውም ፓርቲ በርካቶች ናቸው።

በተለይም የሕወኃት ባለሥልጣናትን ብንመለከት አብዛኞቹ ኤርትራውያን ልጆቻቸው ደግሞ አሜሪካውያን ናቸው። በረከት ስምኦን ምሳሌ መሆን ይችላል ጎንደር ቢያድግም ኤርትራዊ ነው ልጆቹን ደግሞ የአሜሪካ ዜግነት አሰጥቷል። እንደነዚህ አይነት ባንዳዎች ናቸው ኢትዮጵያን የሚመሩትና ወደፊት ሥልጣን መያዝ የሚፈልጉት። የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ትግላችን በተሰኘው መፅሀፉ የተናገረው እውነት ነው “…በኢትዮጵያ የሚንደላቀቁት ለኢትዮጵያ የደከሙላት የሞቱላት ለአገሪቷ አንድነት እና ታላቅነት የታገሉ ልጆቿ ሣይሆኑ የከዷት የወጓት ያስገነጠሏት ያደሟትና አጥፊዎቿ ናቸው …..ኢትዮጵያ ዛሬ ጀግና አልባ ብቻ ሣይሆን ሠው አልባ ምድረ በዳ እየሆነች ነው ዛሬ ሠው የምንላቸው ኢትዮጵያውያን አንድም ተገለዋል አንድም ተሠደዋል አብዛኛውም በወያኔ እስር ቤቶች ታጉረዋል በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚዋጋና የሚታገል ቀርቶ የሚናገርም የለም::” ለማንኛውም ትግሉም ሆነ ስቃዩ ያለው ሀገር ቤት ነው ከሀገር ቤት ውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ መባላቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል ተጨማሪ ቁስል ከመሆን ውጭ መድሃኒት አይሆነውም።

 

ሳተናው
By ሳተናው February 2, 2017 13:49
Write a comment

1 Comment

 1. tamirat February 9, 10:26

  አቶ ኤርሚያስ ይህ የሆነው ለምን ይመስሎታል? እሲቲ የዚህን ድርጅት አደረጃጀት ተመልከቱ

  የግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች እነማን እንደሆኑ እዩና ትግሉ ወደዋላ እንደምሄድ ፍረዱ
  1ኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ————ጉራጌ G7 Executive
  2ኛ ዶ/ር ታደሰ ብሩ————-,<< << <<
  3ኛ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ——–ከምባታ << <<
  4ኛ አቶ ነዓምን ዘለቀ ———-ኤርትራና ኦሮሞ << <<
  5ኛ አቶ አበበ ቦጋለ————–አኦሮሞ << <<
  6ኛ አቶ ቸኮል ጌታሁን———–ጉራጌ G7 Higher leader Ship
  7 ኛ አቶ አንድነት ሐይሉ ——–ጉራጌ << Council
  8ኛ አቶ ሙሉነህ እዮኤል———ከነባታ << <<
  9ኛ አቶ አበረ አዳሙ————-ኦሮሞ << <<
  በዚህ አይነት ጉዞ ነው ሃገርን ከወያኔ ነጻ አውጥቶ እነሱ ደሞ በተራቸው ሊገዙ የሚፈልጉት በኔ አመለካከት ሁለቱንም ነው መዋጋት ያለብን

View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives