አማራ የፖለቲካ ቁማርተኞች እና የታሪክ ደላሎች መቆመሪያ “ጆከር” አይሆንም!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ሳተናው
By ሳተናው April 3, 2017 16:26

ይሄንን ፅሑፍ ለመፃፍ የተገደድኩበት ዋናው ምክንያትም ዶ/ር ዮሃንስ ዘለቀ በሚል ስም የሚጠራ ግለሰብ ኢሳት ” በተባለው ሚዲያ ቀርቦ ታሪክን እንደ ልብ ወለድ ሲተርከው እና እንደ ላሜ ቦራ ተረት ሲተረትረው በመስማቴ “ምሁራዊ እፍረት እና ስነምግባር የት ጠፋ? ” በሚል ስህተቱን የሚያርም ከሆነ ለመጠቆም በማሰብ ነው ።

በመጀመሪያ ዶ/ር ዮሃንስ ዘለቀ ስለተባለው ግለሰብ የትምህርት ዝግጅት እና ለቃለምልልስ ከተጋበዘበት ጉዳይ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው ለማወቅ ስለግለሰቡ ለማጣራት ሞክሬ ነበር።

የዶ/ር ዮሃንስ ስራ “ቱሪስት አስጎብኝ ” ሲሆን የትምህርት ዝግጅቱ ደሞ አንትሮፖሎጅስት ነው ። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያሳተመው መፅሃፍ ወይም በጆርናሎች ላይ የታተመለት የሰራው ጥናት ካለ ብዬ ብፈልግ ምንም ሊገኝ አልቻለም።
ይሄ የቱሪስት ጋይድ አማራንና የኢትዮጵያን ነገስታት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ አደባባይ ወጥቶ ” ምሁራዊ” እውነታዎችና አስተያየቶች ለመስጠት ከተራ መንገደኛ የተሻለ ምንም እውቀትና ምርምር የለውም።


አቶ ሲሳይ አጌና ይሄን ግለሰብ በምን መስፈርት እንደመረጠው ግራ ያጋባል ።በተረፈ ግለሰቡ እንደ ” ምሁር” በተናገረው ርዕስ ሊያናግረው የሚችለው ምንም ዝግጅት የለም። ግለሰቡ የተናገረው የአማራን ማንነት ከተራ ሰው እስከ ነገስታቱ ክዶ በሌላ ማንነት መቀባት ነው። የአማራን አማራነት አውድሞ ነው ያቀረበው። ይኼ አካሂያድ እጅግ አደገኛ እና ወልቃይትም እየሆነ ያለው ይኸው ነው። የESAT ተጠያቂነት እንዲህ አይነት መንገደኞች እያመጣ የአማራን ማንነት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ተውፊት በተደጋጋሚ እንዲደመስሱ፣ እንዲያኮስሱ እንዲያጨልሙ የሚፈቅደው ለምንደነው ነው? የሚል አግራሞት የሚያጭር ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

ይኼ ሰውየ በተለይ ከወያኔ ጋር እንደሚሰራ እየታወቀ ኢሳት ለዚህ ቃለምልልስ መጋበዙ የኢሳትን የተደበቀ አጀንዳ እና ሴራ የሚያጋልጥም ነው።


በመሰረቱ እንደ ዶ/ር ዮሃንስ ያሉ ምሁራን ነን ባዮች ታሪክ መፃፍ እና መናገር ልብወለድ ከመፃፍና ከመናገር የተለየ ቀመርና እሳቤ የለውም የሚል አቋም ይዘው መነሳታቸውን እንገነዘባለን። ያልነበረውን ታሪክ እንደነበረ፣ ያልተፈፀመውን እንደተፈፀመ አድርጎ በመፃፍና በማስተላለፍ አዲስ ፖለቲካዊ አመለካከት እንፈጥራለን ብለው ያሰቡት እነ ዶ/ር ዮሃንስ እና መምህር ገብረኪዳን ያሉ የታሪክ ደላሎች አንዳችም የተጨበጠ መረጃ ሳያቀርቡ ታሪክን ለእኩይ አላማቸው ለማዋል ሌት ተቀን የሚደክሙ መሆናቸውን ግንዛቤ መውሰድ ይገባል።

ለፖለቲካዊ ፋይዳ ሲባል በኢሳት ተቀናብሮ በቀረበው በዚህ የፈጠራ ታሪክ የአማራን ታሪክ እያንኳሰሱ የሌላውን የማጉላት ሴራ ጣሊያኖች ለፕሮፓጋንዳ ፎጆታ ሲሉ የፈጠራ ታሪክ ይሰሩት የነበረውን እና ህውሃት ለአለፉት አርባ አመታት እያደረገ ያለውን የሚያስታውስ ነው። ይሄ የማያባራና ተከታታይ የታሪክ ቅሸባና ቅስቀሳ አማራን አንገት እናስደፋለን ከሚለው የ60 ዎቹ እባጭ ትውልድ መንጭቶ እስካሁንም የሚሰራበት ተከታይ የፕሮፓጋንዳ አካል ነው።


ይሄ ዶ/ር የሚል ማእረግ የተሸከመው “ምሁር” የአማራ ነገስታትን “እብድ ” እያለ ከመሳደብ ጀምሮ የአማራን ህዝብ ” ቡዳ ” በሚል ፀያፍ ስድብ እስከመዝለፍ ችሏል ።

ግለሰቡ የፈጠራ ተረቱን የጀመረው ከአክሱም ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ከነበረችበት ደረጃ ቁልቁል መውረዷን በመጥቀስ ይጀምራል። ይሄ ነገር ያስታወሰኝ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2000 ሚሊኒየም በአል ላይ ያደረገው ንግግር ነው። የዶክተር ዮሃንስን ቃለምልልስ ስሰማ ከሟቹ ባለራእይ መሪ ጋር ” ወይ መመሳሰል አልኩኝ “። የዶክተሩን ተረት ተረት እንተውና እውነታው ስንመረምር ኢትዮጵያ ከአክሱም ዘመነ መንግስት በኋላ በግዛትም በስልጣኔም የበለጠችበት የታሪክ ወቅት እንደነበር አ ንደ ዮሃንስ ፎርጅድ ምሁራን ሳይሆኑ ትክክለኛ የታሪክ ምሁራን ይመሰክራሉ።


በ 1262 በአፄ ይኩኖ አምላክ በሚባል የአማራ መሪ ተመስርቶ ለተከታታይ ለ 700 አመታት ኢትዮጵያን በስልጣኔና በግዛት ስፋት ጫፍ የደረሰችበትን ዘመን በማንሻፈፍ አገሪቱ በስልጣኔ ቁልቁል የወረደችበት ዘመን ነው እያለ እንደ ጣቃ ሲተረተር መስማት ሰውየው እድሜውን ሲያንጎላጅጅ እንዳሳለፈ መረዳት አይከብድም ።

እስኪ ለዶ/ር ዮሃንስ መረጃ ይሆነው ዘንድ በፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ መፅሃፍ ስለዘመኑ ሃያልነት የፃፉትን ልጥቀስ…
“የአማራ ነገስታት የነበሩት አፄ ዮኩኖ አምላክና ተከታዮቹ በተለይም አፄ አምደ ጽዮን ( በ 14ኛው መቶ አመት) እና አፄ ዘርአያእቆብ ( በ 15 ኛው መቶ አመት) ከዛግዌ የወረሱትን ግዛት በማስፋፋት ከአክሱም መንግስት የሚበልጥ ገናና መንግስት ለማቋቋም በቅተዋል” ገፅ 7

በተጨማሪም የቱሪስት ጋይዱ ዶ/ር ዮሃንስ ታሪክን እንደ ጎመን ሲቀነጥሰው ምንም ትንሽ እንኳን ይታዘበኛል አይልም ። ዶ/ር ዮሃንስ በ 1629 በአፄ ፋሲል እና በአማራ ህዝብ አሻራ እና ድንቅ ጥበብ የተሰራውን የጎንደር ህንፃዎች በሌላ ብሄር እንደተሰሩ ሲዘባርቅ መመልከት ቢያበሳጭም በግለሰቡ አላዋቂነት አዝነው ይተውታል። የአፄ ሰርፀ ድንግል የልጅ ልጅ ልጅ የሆነውንና የአፄ ሱሲኒዮስ ልጅ የሆነውንና መቶ በመቶ ከአማራ የሚወለደውን አፄ ፋሲልንም ኦሮሞ ነው ፣ሃደያ ፣ወላይታ ነው እያለ ሲዘባርቅ እኔ በሰውየው አላዋቂነት በጣም ተሳቅቄ ነበር። ታሪክን ለተራ ፖለቲካዊ ፎጆታ ማዋል እጅግ አስቀያሚ ወንጀል እንደሆነ መሰመር አለበት።

በራስ ሚካኤል በተጫረው ዘመነ መሳፍንት ሳቢያ ተከፋፍላ የነበረች ኢትዮጵያን አንደ ቀድሞ አንድ ለማድረግ የደከሙትን እና “መፈጠር በሌለበት ዘመን የተፈጠረ ” ፣”ከጨረቃ የወረደ ” እያሉ ውጭ ፀሃፊዎች አድናቆታቸውን የቸሩትን ጀግናውን አፄ ቴዎድሮስን “ደም አፍሳሽ …እብድ ” እያለ በአደባባይ መሳደቡ እጅግ ያበሳጫል። የምትበሳጩት ግን ዶክተር ዮሃንስ በሚባለው አንጋፋ መሃይም ብቻ ሳይሆን ድብቅ አጀንዳ በሚያራምደው ኢሳት ነው።


ዶክተር ተብየው ምን የቀረው አለ አማራ የተባለውን ሁሉ በአለው አቅሙ ያዋረደበት ያንኳሰሰበት ቃለመጠይቅ ነው ማለት ይቻላል።
በዛው በለመደው አፉ ወደ አፄ ምኒልክም ተሻግሮ ባላዋቂ አንደበቱ ያልሰሩትን ሃጢያት ሲደፈድፍባቸው ነበር ። “ኤርትራን ምኒሊክ ኢትዮጵያን ነፈጋት” በማለት ትግሬ ጓዳ ለጓዳ የሚያወራውን ሃሜት ይዞ አደባባይ ላይ ያለአንዳች መረጃ በህዝብ ፊት ማውራቱ በመረጃ አምናለሁ ከሚል የሳይንስ ሰው የማይጠበቅ አሳፋሪ ንግግር ነው።


በመሰረቱ በ 1960 ዎቹ እንደ አሸን ብቅ ያለውና በመጥረጊያ ተጠርጎ እየወጣ ያለውና “አሮጌ ትውልድ ” ሊባል ትንሽ አመታት የቀረው ትውልድ በብዙ መልኩ ቢለያዩም የአማራን ታሪክ ፣ወግና ባህል “ድሞናይዝ “በማድረግ ስምምነት አላቸው።
አማራው ደሙን ያዘራበትን ነፃነት እንኳን ከማእዱ ሳይቋደስ ሌሎችን ለነፃነት አድርሶ ለዛ ለከፈለው መስዋትነት እንደገና ዘመን የማይችለው ፍዳና መከራ የውለታው ስጦታ አድርገው ሊጭኑበት ይዳዳቸዋል ፡፡ አማራ ደሙን አፈሰሰ እንጅ ደሙን አላፈሰም። አማራ ከዚህ በኋላ ለአረጁ እና በሴራ ለተካኑ የፖለቲካ ቁማርተኞች ጆከር አይሆንም። ከብዙ መስዋእትነት በኋላም ቢሆን መራራውን ነገር ግን ነፃ የሚያወጣውን ትምህርት ተምሯል ። የታሪክ ደላሎች ፃፉ የሴራ ፖለቲከኞች በማኪያቬሌ ስልት ተጓዙ አማራን ግን መጠቀሚያ የማድረግ ዘመኑ አልፎበታል። እነዚያ የየዋህነት አመታት ላይመለሱ ትምህርት ሰጥተውን ላይመለሱ አልፈዋል ።

ሳተናው
By ሳተናው April 3, 2017 16:26
Write a comment

1 Comment

 1. Dereje April 5, 11:14

  እንደሚታወቀው ወያኔ ትግሬዎች ሰውን በመስደብና በማዋረድ የተካኑ ባለጌዎች ናቸው። የሰውን ስነልቦና ለማጥቃት ሲፈልጉ ሰውየው የሚወደውንና የሚያከብረውን ሰው ወይም ታሪኩን በመስደብና በማዋረድ ነው ማሸማቀቅ የሚፈልጉት። አጼ ምኒሊክን፣ አጼ ቴዌድሮስን፣ ጀግናውን በላይ ዘለቀንና ሎሎች የአማራ ጀግኖችን ባገኙት አጋጣሚ ምክንያት እየፈለጉ የሚሳደቡት በፈጠራ ታሪክ በውሸት ስማቸውን የሚያጠፉት አሁን ያለውን የአማራን ትውልድ ለማሸማቀቅና አንገቱን ለማስደፋት መሆኑ ግልጽ ነው።

  በኢሳት የቀረበው ዶ/ር ዮሐንስ ዘለቀ የሚባል የተሪስት አስጎብኚ አማራን የማጥቃት ተልእኮ ስላለው ነው የትግሬውን አፄ ዮሐንስና ራስ ሚካኤል ስሁል የሰሩትን በደልና ጭካኔ አንዳችም ነገር ሳያነሳ አድበስብሶ እያልልፈ በተቃራኒው ደግሞ ለሃገራቸው ብዙ የደከሙና መስዋእት የሆኑ የአማራ ንጉሶችን ስልታዊ በሆነ መንገድ ስማቸውን ሲያጥላላ የነበረው።

  አፄ ዮሐንስ ቦሩ ሜዳ ላይ 30 ሺህ የወሎን ሙስሊም አፍንጫና ምላስ መቁረጣቸውና ተወልደው ካደጉበት ከሃገር ማባረራቸውን ጠፍቶት ነው? ወይስ የጎጃምን ህዝብ በጅምላ ዮሐንስ መጨፍጨፋቸውን ሳያቅ ቀርቶ ነው ስለ አማራ አፍራሽ (Negative) እየፈለገ ሲዘባርቅ የነበረው? እኔ ግን አይመስለኝም። ሰውዬው እውነተኛውን የኢትዮጵያን ታሪክ ሳያቅ ቀርቶ ሳይሆን ሆን ብሎ የአማራ ታሪክና ሥራን ለማንኳሰስ ነው።

  እንደሚታወቀው፦ የአፄ ዮሐንስ 5ኛ አያት የሆኑት ራስ ሚካኤል ስሁል የጎንደሩን ንጉስ ኢዮአስን በሻሽ አንቀው በመግደል የቤተ መንግስቱ የቆሻሻ ገንዳ ከጣሏቸው በኋላ ነበር ዘመነ መሳፍንት በይፋ የተጀመረው። በራስ ሚካኤል በተጫረው ዘመነ መሳፍንት ሳቢያ ተከፋፍላ የነበረች ኢትዮጵያን አንደ ቀድሞ አንድ ለማድረግ የደከሙትን ጀግናውን አፄ ቴዎድሮስን “ደም አፍሳሽ …እብድ ” እያለ በአደባባይ መሳደቡ እጅግ ያበሳጫል፣ ያንገበግባል።

  ሌላው ደግሞ ዶ/ር ዮሐንስ ሌላው ኢትዮጵያዊ በአክሱም ላይ ስላለው የታሪክ ድርሻና ባለቤትነት አድበስብሶ አልፎታል። በመቀጠል ደግሞ ጎንደር እና ሸዋ ግን የአማራ መንግስታት አይደሉም፣ ንጉሶቹም አማሮች አይደሉም ሲል በተቃራኒው ደግሞ በግእዝ ቃል የሚጠሩ የቦታ ስሞችን እየፈለገ ይህ ህዝብ ትግሬ ነው በማለት ዘባርቋል። ኦሮሞነት የሌለበት ጎጃሜ ቡዳ ነውም ብሏል። “ኤርትራን ምኒሊክ ኢትዮጵያን ነፈጋት” በማለት ትግሬ ጓዳ ለጓዳ የሚያወራውን ሃሜት አደባባይ ላይ በመዘርገፍ በመረጃ አምናለሁ ከሚል የሳይንስ ሰው የማይጠበቅ አሳፋሪ ንግግር ተናግሯል።
  …..
  እውነቱ ግን አፄ ዮሐንስ በ1876 ዓ.ም የሂዎትን ውል ለእንግሊዝ ከፈረሙ በኋላ ነበር ጣሊያኖች በእንግሊዝ አማካኝነት ምጽዋን የተቆጣጠሩት። ከዛም ዮሐንስ ራስ አሉላን ከስልጣናቸው በመሻራቸው ነበር ጣሊያኖች ቀስ በቀስ በመስፋፋት አስመራንም ሆነ እስከ መረብ ወንዝ ምላሽ ድረስ የተቆጣጠሩት። አፄ ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ የዮሐንስ ልጅ የሆኑት ራስ መንገሻ አፄ ምኒሊክን በመክዳት አስመራ ድረስ በመሄድ ከጣሊያን ጋር በሚስጥር የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለመስጠት ተዋውለዋል።

  እውነተኛ ከሆነ ከጎንደርና ከሸዋ ተነስተው ምጽዋ በርሃ ድረስ ተጉዘው ቱርክንና ግብጽን በመውጋት ሃገሩን ከጠላት ነጻ አድርገው ስለተመለሱ ስለ አፄ ሚናስ፣ ስለ አፄ ሰርጸ ድንግል፣ ስለ አፄ አምደ ጽዮን፣ ስለ አፄ ዘርያቆብ እና ስለመሳሰሉት የአማራ ነገስታት በተናገረ ነበር።

  አጼ ምንሊክ የኢትዮጵያን ህዝብ አስተባብረው ከሸዋ ተነስተው ትግራይ ከመድረሳቸው በፊት እነ ራስ አሉላ፣ እነ ራስ መንገሻ እና የመሳሰሉት አሉ የሚባሉ የትግራይ ሹማምንት ከአንዴም ሦስት አራት ጊዜ ከጣሊያን ጋር ጦርነት ገጥመው ተሸንፈው ሃገሩን በሙሉ አስረክበው አልፈረጠጡም? አጼ ምንሊክ ከመድረሳቸው በፊት 80% በላይ የሚሆነው የትግራይ አካባቢ በጣሊያን ቁጥትር ስር ውሎ አልነበረም? ጣሊያንን ጠራርገው አድዋ ላይ ሰብስበው ድባቅ የተመታው በምኒሊክ ስልትና ጀግንነት መሆኑ እየታወቀና እነ ራስ መንገሻ ግራ በተጋቡ ጉዜ ትግራይን ነጻ ያወጡት አጼ ምንሊክ መሆናቸው እየታወቀ ታሪክን ማዛባት ተገቢ አይደለም።

  የአድዋ ጦርነት በድል እንደተጠናቀቀ አፄ ምኒሊክን መረብን ተሻግረው ውጊያው እንዲቀጥል ያላደረጉት ለ100 ሺህ ሰራዊት የሚበቃ ቀለብ ስለሌለ፣ ተዋጊው በመዳከሙ እንዲሁም ምጽዋ ላይም አዲስ ጦር ከሮም በመላኩ እና በሌሎች ምክንያት እንደሆነ በበርካታ መጻህፍት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

  ይህ ዋሾ ቀዳዳ ቱሪስት አስጎብኚ ግን የመቀሌው ጦርነት ሲደረግ አፄ ምኒሊክ ቤተ መንግስታቸው እንደነበሩ መናገሩ ፍጹም ውሸት ነው። በወቅቱ አፄ ምኒሊክ እዛው ትግራይ ውስጥ ከሰራዊታቸው ጋር ነበሩ።—-//——

View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives