የቀድሞ የሌስተር አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊመለሱ ነው።አዲሱ ክለባቸው እና አመጣጣቸው እንዴት ይሆን?  (በቶማስ ሰብሰቤ)

ሳተናው
By ሳተናው April 17, 2017 18:06
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የራሳቸውን ታሪክ ፅፈዋል።ትንሹን ሌስተር የሊግ ዋንጫ አሸናፊ አድርገውታል።ቀድሞ የሻምፒየስ ሊግ ተመልካች ብቻ የነበሩት ሌስተሮችን በአውሮፓ መድረክ ተሳታፊ አድርገዋል ብልሁ እና ቁጡው አሰልጣኝ ክላዉዲዮ ራኔሪ።
ከሌስተር ያልተጠበቀ ስንብታቸው በሃላ ሰራ አጥ ናቸው።ስለ ቀጣይ የአሰልጣኝነት ህይወታቸውም አልተናገሩም።ዛሬ የተሰማው ነገር ግን ሰውየው ውስጥ ለውስጥ ወደ ቀድሞው ሊግ ለመመለስ እየሰሩ ነው ተብሏ።ልክ እንደ ሌስተር ትንሽ ክለብ የሆነው ዋትፎርድ ደሞ ፈላጊቸው ነው።ዋትፎርድ በሊጉ 11 ደረጃ ቢይዝም ለባለሀብቱ አልተመቻቸውም።የክለቡ ባለቤት ጂኖ ፖዛ ( Gino Pozzo)  ዋትፎርድ ስኬታማ ለማድረግ ራኔሪን ይፈልጋሉ።ባለሀብቱ በራኔሪ የሌስተር ሰኬት እምነት ያደረባቸው ናቸው።ቦርዱም ከሰር አሰልጣኙን የማሳመን ሰራ እየሰራ ነው ተብሏል።
ክላውዲዮ ራኔሪን ከፍተኛ የዝውውር ዋጋ ሊመድቡላቸው እና ጠቀም ያለ ደሞዝ አቅርበውላቸው አሰልጣኙን ለማምጣት አስበዋል ነው የተባለው።ጣልያናዊው አሰልጣኝም ያለክብር ካሰናበታቸው ሌስተር ጋር እልህ ውስጥ ስለተጋቡ መመለሰሱን ይፈልገሉ።ልክ እንደ ጆዜ ከቼልሲ ከተባረሩ በሃላ ዮናይትድ እንደመጡት እኝህም አሰልጣኝ መመለስ ፍለጎታቸው ነው ተብሏል።ከጣልያን ሴሪ አ የተሻለ በእንግሊዝ መስራት ይፈልጋሉ።
የአሁን የዋትፎርድ አሰልጣኝ ዋልተር ማዛሪ እንግሊዝ አልቀናቸውም።አሰልጣኙም በዋትፎርድ ስኬታማ አለመሆናቸው መሰናበታቸው ሳይወዱ በግድ ያመጣባቸዋል።በተለይ በተከታታይ መሸነፋቸው ማዛሪም ውላቻው በአመቱ ሲያልቅ ቆያታቸው ያበቃል።ከዛም በፖዛ ቤተሰብ ፣ እጅግ ተወዳጁ ሰው ራኔሪን እይመተጣሉ ።አዛውንቱ አሰልጣኝ  በዋትፎርድ አንጋታቸው ደፍተው እንደ ሌስተር ከሰሩ ሌላ ስኬትን ሊያመጡ ይችላሉ።ነገር ግን አሁን ሊጉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተወዳዳሪ እና ጠንካራ ሆኗል።በቀጣይ አመት ጋርዲዮላ እና ሞሪንሆ ሁለተኛ አመታቸው ስለሆነ የግድ ዋንጫ ይፈልጋሉ ፣ክሎፕ በመጨረሻው አመት በአንፊልድ ለመቆየት ሰኬት ይሸሉ  ፣ኮንቴ ፍፁም የማይተኛ ብድን አለው ፣የቶተነሃም ምርጥ ቡድን በመጨረሻው እጅግ ፈታኝ ነው ፣ አርሰናል ተንገጫግጮም የአውሮፓ ተሳታፊነት ይሞክራል እናም በዚህ ውስጥ እንደ ሌስተር ያለ ቡድን ማምጣት ከባድ ይሆንባቸዋል።ኢሮፓ ሊግ የራኔሪ የቤት ሰራ ሊሆን ይችላል።ዋትፎርድን ከምርጥ አራት ማስቀመጥ ግን ራኔሪ ከመጡ ይጠበቅባቸዋል።
ምንጭ፣ዘ ሰን
ሳተናው
By ሳተናው April 17, 2017 18:06
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives