ጆን ቴሪ የፊታችን ግንቦት ወር ቼልሲ ከሰንደርላንድ በሚያደርጉት ጫወታ ክለቡን እንደሚለቅ ይፋ አደረገ።ተጫዋቹ ከቼልሲ የለቀቀበት ምክንያት እና ቀጣይ ክለቡን የት ይሆን?

ሳተናው
By ሳተናው April 17, 2017 18:13
በቶማስ ሰብሰቤ
በሰማያዊዎቹ ቤት ስሙ ትልቅ ነው።አራት የሊግ ፣አንድ ሻምፒየስ ሊግና ኢሮፓ ሊግ በዋናነት ማንሳት ችሏል።ከ13 አመቱ ጀምሮ በስታንፎርድ ብሪጂ ያደገ ነው።ከሰማያዊው የቸልሲ ማልያ ውጪ ሌላ ለብሶ አይተነው አናውቅም።የለንደኑ ክለብ ታማኝ እና የመሃል ተከላካይ ማዘን ጆን ቴሪ።
ከ13 አመቱ ጀምሮ የለበሰውን ማልያ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በሰንደርላንዱ ጫወታ ይሰናበታል።እንግሊዛዊው ተከላካይ ሰታንፎርድ ብሪጅን የለቀቀበት ሶስት ምክንያቶች ናቸው።አንደኛው የመሰለፍ እድል ያለማግኘቱ ነው።በዚህ አመት ብቻ አራት ጫወታዎች ብቻ በመጀመሪያ አሰላለፍ የገባው።ወትሮ የክለቡ አንበል እና የመጀመሪያ ተሰላፊ የነበረው ቴሪ ባለፊት ሶስት አመታት በተቀያሪ ወንበር ብዙ አሳልፋል።በተለይ በዚህ አመት አንቶኒዮ ኮንቴ አሰቀምጦታል።ለሁለት አሰርት አመታት በስታንፎርድ ብርጂ የመጀመሪያ ተሰላፊ ብቻ ሳይሆን ጉዳት ካጋጠነው የቸልሲ የተከላካይ ክፍል ይብረከረክ ነበር ነገር ግና ባለፉት ሶስት አመታት የ35 አመቱ ተከላካይ እንደ ኮርት ዙማ ፣ሊውስ እና ጋሪ ካይል በእሱ ቦታ እድል አልሰጡትም።ለዚህም ከተጫዋችነት ይልቅ ከሳምንት ሳምንት ተቀያሪ ወንበር ላይ ነበር።
ሁለተኛው እድሜ ነው።እድሜ እየገፋ መምጣቱ ብዙ ተወዳዳሪ እንዳይሆን ሲያደርገው በአንፃሩ ለሌሎቸ በእሱ ቦታ ያሉት ተጫዋቾች እንዲጠነክሩ አድርጎቸዋል።ቼልሲዎችም የእሱን ምትክ ለመፍጠር ለታዳጊ እድል ይሰጣሉ አሰልጣኞቹ።
ሶስተኛው በመጨረሻው ዘመኑ የሌላ ሊግ ልምድ ይፈልጋል።በአሜሪካ ፣ቻይና ወይም አረብ ሊግ መሞከር ይፈልጋል።በተለይ የቻይና ሊግ ረብጣ ዝውውር እና ልምድን ይሻል።በአሜሪካ ሊግም ከቀድሞ ኮከብ ተጫዋቾ  የመጫወት ፍላጎት አለው ይባላል።ለጆን ቴሪ የዘንድሮ መልቀቅ ውሳኔው ደሞ ያበዛለት ቼልስ ሊጉን ሊያሰነሳ የ6 ጫወታ እድሜ ብቻ ስለቀረው ነው።በአራት ነጥብ ልዮነት ሊጉን እየመራ ያለው ቸልሲ በዋንጫ ሲጨርስ በአንበልነት የመጨረሳ ስኬቱን በድል አድርጎ መውጣት ይፈልጋል።እጅግ ፈታኝ በሆነው የእንግሊዝ ሊግ ቀጣይ አመታት ቢጠብቅ ቴሪ ዋንጫን በቀላሉ ማንሳት ይከብደዋል።እድሜውም ስለሄደ ስጋት አለው ለዚህም አጋጣሚውን መጠቀም ይፈልጋል።
ጆን ቴሪ በቸልሲ ብዙ ጨወታዎች በማድረግ የክለቡ የምንግዜም ሶስተኛ ተጫዋች ነው።713 ጫዋታዎችን ሲጫወት 578 ጨዋታዎችን አንበል ነበር።ዛሬ ቸልሲን እንደሚለቅ ይፋ ሲያደርግ ከማንም ቀድመው የክብር ምስጋና ያቀረቡት የዮናይትድ ደጋፊዎች ናቸው።”እኛ የዮናይትድ ደጋፊዎች መቼም አንረሳህም።አንተ የእኛም ጀግና ተጫዋች።ሁሌም በኦልትራፎልድ ትታወሳለህ” ሲሉ በ2008 እሱ በሳተው ፍፆም ቅጣት ምት ኳስ የአውሮፓ ሻምፒየስ ሊግ ስላነሱ የማላገጥ ምስጋና ሰተውታል።ላነ
ቸልሲ ከሰንደርላን በሚያደርጉት የመጨረሻ የሊጎ ጫወታ 66 ጎሎችን ከተከላካይ ተነሰቶ ያገባውን ፣የክለቡ የምን ጊዜም ምርጡን አንበል ፣ታማኙን ተጫዋች ፣የአሰፈሪው ቸልሲ ቀዳማይ ሞተርን ፣ የተከላካይ ማገር ፣ የጆዜ ሞሪንሆውን ምርጥ ቡድን መለያን በክብር የሰማያዊዎቹ ደጋፊዎች ይሸኙታል ፤ እሱም በእንባ ከክለብ በላይ የሆነበትን ክለብ ይለያል።ጆን ቴሪ የእኔም ትዝታዮ ነህ !እናተስ!
ምንጭ፣ቢቢሲ
ሳተናው
By ሳተናው April 17, 2017 18:13
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives