ጌታነህ ከበደ የክለቡን ማሊያ ቀዶ አሰልጣኙ ፊት ላይ ወረወረ

ሳተናው
By ሳተናው April 19, 2017 15:07

(ኢትዮ-ኪክ ኦፍ)  በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ በ24ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ መደበኛ ጨዋታ ደደቢት ከአርባ ምንጭ ጋር ሲጫወቱ በመጨረሻው ደቂቃ አርባ ምንጮች የአቻነት ግብ አስቆጠረው ጨዋታው 2ለ2 አለቀ። ውጤቱ የደደቢት ክለብን ሊያበሳጭ እንደሚችል ይገመታል ምክንያቱም ቢያሸንፉ ሊጉን በ1ኝነት ስለሚመሩ ።

በአንፃሩ የፕሪምየር ሊጉን በኮከብ ግብ አግቢነት በ19 ጎል እየገሰገሰ ያለው ጌታነህ ከበደ ዛሬ በጨዋታው መጨረሻ ያደረገው ተግባር ብዙዎችን አስደንግጧል። ጌታነህ ጨዋታው ሲጠናቀቅ መለያውን 9 ቁጥር ቀዶ አሰልጣኙ ፊት ላይ ወርውሮታል ! በርግጥ ጌታነህ በአሰልጣኙ የተበሳጨበት ነገር ቢኖርም የክለቡን ማሊያ መቅደዱ ከስፖርታዊ ስነምግባር ድርጊት ውጭ እንደሆነ አንዳንድ የስፖርት ቤተሰቦች በአስተያየታቸው ለኢትዮ-ኪክ አድርሰዋል።

 

ሳተናው
By ሳተናው April 19, 2017 15:07
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives