አልማዝ አያና ላይ በአብዛኛው የሚቀርበው ትችት “አንድ አይነት የአሯሯጥ ታክቲክ ብቻ ነው ያላት – ፍስሀ ተገኝ

ሳተናው
By ሳተናው August 14, 2017 08:14

አልማዝ አያና ላይ በአብዛኛው የሚቀርበው ትችት “አንድ አይነት የአሯሯጥ ታክቲክ ብቻ ነው ያላት። በሌላ አይነት መንገድም ማሸነፍ እንዳለ ማወቅ አለባት” የሚል ነው።

ለዚህ አስተያየት ወይም ትችት መልስ ለመስጠት እንዲረዳ በሚል ከአምስት አመት በፊት የባርሴሎናው የመሃል ተጨዋች አንድሬስ ኢንዬስታ ክለቡ ለምን አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ የአጨዋወት ስታይል እንደሚጠቀም ሲጠየቅ የሰጠውን መልስ ወርወር ለማረግ ወደድኩ…

ኢኒዬስታ እንዲህ አለ “…we play the way we do because it suits us. We don’t have the players to pull it off playing a different way. It’s the way we like to play and it’s the way we believe we have the best chance of winning.”

አልማዝም ይሄ የምትከተለው የአሯሯጥ ዘዴ በርካታ ድሎችን አስገኝቶላታል – የኦሊምፒክና የአለም ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳሊያዎችና ሌላ አይነት ቀለም ያላቸው ሜዳሊያዎችን ጨምሮ። አልማዝ ተፎካካሪዎቿን ማሸነፍ ወይም መቋቋም የምትችለው በዚህ አይነት የአሯሯጥ ዘዴዋ እንደሆነ ታውቃለች። መጨረሻ ላይ ፍጥነት የመቀየር ብቃት ስለሌላት ባለድል ለመሆን ወይም ለሜዳሊያ ለመፎካከር ያላት ብቸኛዋ አማራጭ ጉልበቷን ተማምና ውድድሩን ከመጀመሪያው ወይም ከመሀል ጀምሮ ማክረር እና ተፎካካሪዎቿን ማራገፍና መቀነስ ነው። ይሄንንም አድርጋ በተደጋጋሚ ባለድል ሆናለች። ወርቅ ብቻ ሳይሆን የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎች፣ ሌሎች በርካታ ውድድሮችን በድል አድራጊነት አጠናቃ በትራኩ አለም ነግሳለች። የአለም ክብረወሰንንም እንክትክቱን አውጥታዋለች።

ኢኒዬስታም አለ – “…we play the way we do because it suits us. We don’t have the players to pull it off playing a different way. It’s the way we like to play and it’s the way we believe we have the best chance of winning.”

አልማዝ አያና… #Ethiopia

ሳተናው
By ሳተናው August 14, 2017 08:14
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives