የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር እና ቅድመ መከላከል የጤና ፖሊሲ ደካማነት ተከትሎ የ’አተት’ በሽታ ወረርሽኝ በድጋሚ ተከሠተ .. (ይድነቃቸው ከበደ)

ሳተናው
By ሳተናው August 30, 2017 14:02

አጣዳፊ ተቅማጥ እና ተውከት በምህፃሩ ‘አተት’ ተብሎ የሚጠራው በሽታ በፍጥነት የመሠራጨት ፀባይ ያለው እና በጊዜው አስቸኳይ ሕክምና ካላገኘ ብዙዎችን ለሞት የሚዳርግ አደገኛ የወረርሽኝ በሽታ ነው ።በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ይህ የወረርሽኝ በሽታ አብዛኛው መንስኤ የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር ሲሆን ፣ የአካባቢ እና የግል ንጽህና ችግር በዋነኛነት የወረርሽኙ መንስኤ ነው። በኢትዮጵያ የ’አተት’ ወረርሽኝ የመጀመሪያው እና ትልቁ መፍትሔ ወረርሽኙ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ‘ የማህበረሠብ ተኮር የጤና ፖሊሲ’ ትልቅ ሚና እንዳለው በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የወረርሽኙ መከሰት ተከትሉ፤ የንፁህ መጠጥ ዉኃ ችግር እና የማህበረሠብ ተኮር የጤና ፖሊሲ ደካማነት እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ይታመናል። በዚህም መክንያት በተደጋጋሚ የሚከሰተው የ’አተት’ በሽታ ቁጥር ቀላል የማይባል የሰውን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን አብዛኛውን ሰው ለከፍተኛ ህመም ዳርጎል። በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰው የ’አተት’ ወረርሽኝ በሽታ ወደ ተቀረው አካባቢ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ ሊዛመት እንደሚችል ሥጋት ያለ ሲሆን፤ ‘የአተት/ በሽታን’ አስመልክቶ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እየተሰጠ ያለው መግለጫ ግን በተቃራኒው ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሃት/የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ሆነ በሚያገለግሉበት ወቅት ‘የአተት/ ‘በሽታ’ በተደጋጋሚ የተቀሰቀሰ ሲሆን ለብዙዎች ህመም እና የተወሰነ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል ። እኚህ ባለሥልጣን ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተርነት በሚወዳደሩበት ወቅት፤ የምረጡኝ ዘመቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲያካሂዱ “የወረርሽኝ እና ተላላፊ በሽታ” በታዳጊ ሃገራት ለማስቀረት እና ለመከላከል እንደሚሰሩ ጭምር ገልፆው ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ “ቅድመ መከላከያ የጤና ፖሊሲ” ተግባራዊ በማድረግ የተስቦ እና የወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠር እንደተቻለ እና ይሄን ልምድና ተሞኩሮ
በዓለም ለመተግበር እንደሚሰሩ ቃል ገብተው እንደነበረ የሚታወሰ ነው።

ሳተናው
By ሳተናው August 30, 2017 14:02
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives