የጭቁኖች የበደል እንጉርጎራዊ ዜማ የትም ምንጊዜም ይዘመር – ቬሮኒካ መላኩ

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 13:54

የጭቁኖች የበደል እንጉርጎራዊ ዜማ የትም ምንጊዜም ይዘመር እንጅ ቅላፄውና ምቱ ሜሎድውና ሪትሙ ተመሳሳይ ነው። ለዚህም ነው በሌላው በሐውርት ላይ በሚገኙት በበርማ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመ ድርጊት ሲያሳምመን የከረመው ።
ዛሬ እኛ አማራዎች “ዘመቻ ወልቃይት ” ጀምረናል። የወልቃይት አማራ ጉዳይ እኔንም ይመለከተኛል የሚል ሁሉ በዚህ ዘመቻ ይሳተፍ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

ቬሮኒካ መላኩ እባለለሁ ። ትግሬ ወያኔ በወገናችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ የማያባራ የዘር ማጥፋትና የመሬት ወረራ መፈጸሙን ተከትሎ መላው የአማራ ህዝብ የተባበረበት ወልቃይትን ወደ ነባሩ የጎንደር ግዛት የመመለስ ትግል ከተጀመረ አመታትን አስቆጥሯል ። ትግሬ ወያኔዎች ይሄንን ህጋዊ የሆነ የህዝብ ጥያቄ የተለያየ ስያሜ በመለጠፍ በህዝብ የተመረጡ የወልቃይት ህዝብ ተወካይ ኮሚቴዎችን ጨምሮ በርካታ ንጹሃን አማሮች ለግድያና ለእስራት ሰለባ ዳርገዋል። ይባስ ብለው በቅርቡ የህዝቡን ጥያቄ ሊያዳፍንልን ይችላል በሚል ይመስላል በቅማንት ማሊያ የየአማራ ህዝብ ከነባር ይዞታው ለማፈናቀል ያለሙ መሆናቸውን ሾልኮ የወጣው መረጃ ያመለከተ ሲሆን በሌላ በኩል የአማራ ህዝብ ጥያቄ ያልሆነ የግጨውና ጎቤ ጉዳይ ፈተንላችሗል በማለትአስረክቦ ጎቤ የተባሉ ሰፋፊ የእርሻና በእጣን ምርት የታወቁ ቦታዎችን ለትግራይ አስረክቦ በአማራ ህዝብ ትግል ላይ ማሾፋቸውን ቀጥለዋል ።

ስለሆነም መቀመጫውን መቀሌ ባደረገ ኮሚቴ አማካኝነት በቅማንት ማሊያ ወንድማማች የአማራና የቅማንት ህዝብን ለማጫረስ የሚደረግ ሸፍጥ እንዲቆም እንዲሁም የግጨውን መሬት በተመለከተ ህወሃትና ብአዴን የተፈራረሙት ውል የአማራን ህዝብ የማይመለከት በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግ አሳስባለው ።
ከተከዜ ወንዝ በታች የትግራይ ድንበር የለም ። የወልቃይት ህዝብ ተወካይ ኮሚቴዎች ይፈቱ ፣ ጥያቄውም በአስቸኳይ ይመለስ ስል እጠይቃለሁ ።

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 13:54
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives