ይድረስ ከገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር – ሰለሞን ዳኛቸው

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 14:16

ጳጉሜ 3 ቀን 2009 ዓ.ም

ኢሳት ባሰራጨው ዘገባ ከዛሬ 10 አመት በፊት በግጨውና ጎቤ አካባቢ በሟች ጠቅላይ ሚኒስተር አመራር ሰጪነት ህዝበ ውሳኔ ተካሂዶ ከ90% በላይ የሆነው የአካባቢው ነዋሪ አማራ ነን በማለቱ ውጤቱ በፌደሬሽን ም/ቤት እንዲታፈን ተደርጎ ለህዝብ ይፋ ሳይደረግ ቀርቶል ብሏል።

ኢሳት በወቅቱ የአካባቢው የመሬት አስተዳደር ባለሞያ የነበሩ ግለሰብን አቅርቦ በሰራው ዘገባ ከምርጫ 97 በኋላ የትግራይ ተወላጆች የግጨውና ጎቤን መሬት በከፍተኛ ቁጥር መውረራቸውን ተከትሎ በአካባቢው የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት ፀጋዬ በርሄና የአማራው አቻቸው አቶ አያሌው ጎበዜ በዳንሻ ፋና ሆቴል ያደረጉት ስብሰባ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች በይገባኛል ጥያቄው ላይ ባለመስማማታቸው ስብሰባው ሲበተን ሟች ጠቅላይ ሚኒስተር በሰጡት ትዕዛዝ ህዝበ ውሳኔ መደረጉን፤ በ1999 ዓ.ም በተደረገው ህዝበ ውሳኔ ከ90% በላይ ድምፅ የሰጠው አማራ ነን በማለቱ ውጤቱ በፌደሬሽን ም/ቤት ታፍኖ እስከዛሬ ለህዝብ ይፋ አልመደረጉን አጋልጦል።

በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም በጎንደር የተቀጣጠለውና በባህር ዳር በአንድ ቀን ከ50 በላይ ወጣቶች ህይወት የከፈሉበት የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘጋ በህወሓት በተቀነባበረ ሴራ ወልቃይትን አልፎ ዳንሻን ተሻግሮ ግጨው ላይ ያሰመራችሁትን የትግራይና አማራ ወሰን የተቀበላችሁት እርሷዎና እንደ ድርጅት የታላቋ ትግራይ ህልም እውን ለማድረግ ህወሓት ጠፍጥፎ የሰራው እርሷዎ የሚመሩት ብአዴን ብቻ ነው። በርግጥ ትውልደ አማራ የሆኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በፍላጎትም ይሁን ራስን ከጥቃት ለመከላከል ብአዴንን የተቀላቀሉ የትግራይና አማራ ተፈጥሯዊ ድንበሩ ተከዜ፣ ወልቃይትም አማራ ነው የሚሉ የሚያምኑ አሉ። በያዙት አቋምም ከስራ የተባረሩ ወደ እስር ቤትም የተጋዙ ለመኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።

የአማራው ህብረተሰብ ከወላጆቹ የወረሰው ታሪክ፣ ባህልና አስተዳደግ ከምንም በላይ ኢትዮጵያን አስበልጦ እንዲያይ፣ ከዚያ ውጪ በነገድና በጎጥ ደረጃ ወርዶ ለማሰብ ስላልፈቀደ እርሷዎ ጠላቶቹ የደገሱለትን አማራን ነጥሎ የማጥፋት ዕቅድ ግንባር ቀደም ሆነው እያስፈፀሙለት ነው።
ቅማንትና አማራን ለመከፋፈል መሞከር አንድን ሰው ለሁለት ከፍሎ ህይወት ይኑርህ የማለት ያህል ከባድ ነው። እነዚህ ህዝቦች እየብቻ የሚሆን የላቸውም፤ እጣ ፈንታቸው አንድ ላይ ነው እንዳላሉን ሁሉ አማራና ቅማንት ተደባልቀው በሚኖሩበት 12 ቀበሌዎች ቅማንትን ከአማራ ለመነጠል መስከረም 7 ቀን 2010 ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ ፍቃደኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ስለዚህም ለእርሷዎ የማቀርበው ጥያቄ ሁለት ይሆናል፤ የመጀመሪያው እንደ ፌደሬሽን ም/ቤት አባልነትዎ ከ10 አመት በፊት በግጨውና ጎቤ አካባቢ የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ውጤት ለህዝብ ይፋ ሳይደረግ በፌደሬሽን ም/ቤት ለምን ታፍኖ እንደቀር ለአማራ ህዝብ ማብራሪያ እንዲሰጡ። ሁለተኛው ደግሞ አማራና ቅማንትን ለመክፈል መሞከር አንድን ሰው ለሁለት ሰንጥቆ ህይወት ይኑርህ የማለት ያህል ከባድ ጉዳይ ነው ያሉትን ማስፈፀም አቅም ያነስዋት፣ በአቋምዎም መፅናት ያልቻሉ ስለሆነ ስልጣንዎን ይልቀቁ የሚል ነው።
መልካም አዲስ አመት ይሁንላችሁ!
የአማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!

 

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 14:16
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives