ህወሃት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከስልጣን በቅርቡ እንደሚወገድ ለአባላቱ በላከው ደብዳቤ ገለጽ! – ወልቃይት

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 19:18

ወልቃይት ዜና

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ህወሃት ከብአዴን ጋር ከወሰን ጋር በተያያዘ ያደረገዉን ስምምነት በተመለከተ ለአባላቱ በፃፈዉ ፅሁፍ፤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉን ከስልጣን ሊያስነሳዉ እንዳቀደ ለህወሃት አባላት ገለጽ ህወሓት ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ/ም ከብአዴን ጋር ከወሰን ጋር በተያያዘ ያደረገውን ስምምነት በተመለከተ በአገር ውስጥና እና ከአገር ውጭ ያሉ ለፍተኛ አመራሮቹ ማብራሪያ በመጠየቃቸው የሚከተለውን መል ዕክት በጽሁፍ አስተላልፏል። ህወሃት አቶ ገዱን እና ብአዴንን በሚመለከት በአገር ቤትና በውጭ አገር ለሚኖሩ አባላቱ ያስተላለፈው መልዕክት እንደወረደ ከዚህ በታች አንብቡት።

እንደሚታወቀው በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ከማንነትና ከመሬት ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም በመጀመሪያ ጥያቄውን ስንገመግመው የህዝብ ጥያቄ እንዳልሆነ እና የትምክህተኞች ጥያቄ እንደነበር ገምግመን ጉዳዩን ብአዴን እና የክልሉ መንግስት መፍቴሄ እዲሰጠው ነግረን ነበር። ሁኖም ብአዴን ሊፈታው እንዳልቻለና ጉዳዩ በመካከለኛና በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ የብአዴን ሰዎች የትምክህተኛውን ጥያቄ በመደገፍ እና በማራገብ ነገሩን ወደ ህዝብ በማውረድ ከፍተኛ ችግሮች ተፈጠሩ፣ ከዚያም እንደኢህአዴግ ባየነው ሳዓትም ከፍኛው አመራርም በትምክህተኛው አስተሳሰብ ሰለባ ሁኖ ተገኘ ፣በወቅቱም ጉዳዪ ወደ አልሆነ አቅጣጫ ሲቀየር የብአዴን ነባር አመራሮች ለጉዳዩ መፍቴሄ ለመስጠት እነ ጓድ በረከት እና ጓድ አዲሱ የተወሰኑ አመራሮችን በመያዝ ተንቀሳቀሱ። በወቅቱ የህወሓት ሰዎች ዝምታን እንድናደርግ ነገሩን ፣ነገር ግን እነሱ በክልሉ በመሄድ ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ከከፍተኛ አመራር እስከ ዝቅተኛው ድረስ በትምክህት አመለካከት የተበከሉ ናቸው።

ጉዳዩ እጅግ አስቸጋሪ ስለሆነ ከፊደራል የተወጣጣ ቡድን ተቋቁሞ እዲታይ ጓድ በረከት ባቀረበው የመፍቴሄ ሃሳብ መሰረት ከመከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከፊዴሪሽን ምክርቤት፣ ከፊዴራል ጉዳዬች የተወጣጡ ሰዎች የሚገኙበት ቡድን ጉዳዩን እዲያዩት ተደረገ ። ጥናቱ የብአዴን መካከለኛና ዝቅተኛ ካድሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች በችግሩ ውስጥ ተዘፍቀው ተገኙ ፣፡ በዚህም በአደረግነው ግምገማ እነ ጓድ በረከት በክልል ደረጃ በተደረገው ግምገማ ሰዎችን የመለየት ስራ በመስራታቸው፣ በመጀመሪያ ከማባረርና ከማሰር ይልቅ ይህን የተከማቸን ኃይል የመበተን ስራ መሰራት ስለነበር መካከለኛው እና ዝቅተኛው አመራር ውስጥ የሚገኙ ፅንፈኞችን በማገድ የተወሰነውን በመቀየርና በማውረድ ኃይሉ ቀነሰ።ከዚያም ከከፍተኛ አመራሩ ውስጥ የሚገኙትን ደግሞ በፕወዛ መልክ ወደ ፊዴራልና ሊሎች ቦታዎች በማዛወር የነበረው ጫና እዲቀንስ ተደረገ።

በተለይ ገዱ አንዳርጋቸው በነበረው ርካሽ ተወዳጅነት በተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችና አመራሮች ድጋፍ ስለመበረው በዚህ ሰው ላይ በወቅቱ እርምጃ መውሰድ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ምንም እንኩዋን እልህ አስጨራሽ ቢሆንም በተከታታይ ስራዎች ይህን ሰው ከህዝብና ከአመራሩ የመነጠል ስራዎች ተሰርተዋል። በዚህም መነሻነት ከቅማንት ቢሔረሰብ ጋር የተሰራው የሰባዓዊ ጥሰትን በዋነኛነት እሱ ተጠያቂ እንደሆነ እና ሊሎች ተዛማጅ ችግሮች እንዳሉበት በማጋለጥ ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ በመምራት ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ/ም አይደለም ወልቃይትን ሌሎችን፣ እነ ግጨውን ጭምር የትግራይ ክልል መሬት መሆናቸውን ራሱ በአንደበቱ እዲናገርና ፊርማውን እዲያስቀምጥ ተደርጓል፣

በመሆኑም ይህ ሰው ያደረጋቸው ንግግሮችና ፊርማውን ጭምር በትግራይ መገናኛ ብዙሃን፣ በቲሌቪዥን፣ በወይን ጋዜጣ እና በኢቢሲ፣ በሬዲዩ ፋና፣ በአብዩታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣ፣ በግል ሚዲያዎች በይፋ ለህብረተሰቡ የመንገርና የማሳየት ስራዎች በተከታታይ እንዲቀርቡ ይደረጋል። ከዚያም ይህ ሰው ከህዝብና ከአባሉ ይነጠላል፣ በመጨረሻም በክልሉ፣ ልክ እደ ኦሮሚያና ደቡብ እንዳደረግነው እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት ከትምክህትና ከጠባብ አመለካከት የፀዳ ህወሓትን እንደ አጋር ድርጅት እንጂ በጠላትነት የማይመለከት ሰው በእሱ ምትክ የሞሸም ስራ ይሰራል።

ሳተናው
By ሳተናው September 9, 2017 19:18
Write a comment

3 Comments

  1. Dan September 9, 23:19

    I really don’t understand the political game being played, Yestarday President Gedu signed the worst agreement in history and today hearing a speculation of his dismisal. It would have been better if he had acted acted like his preceder President Gobezie who refused to sign the sellout agreement on Ethiopian Sudan border. It is bad time for Amhara state for lossing a leader who faced the TPLF at several ocassions and stood for the people. It is sad he didn’t foresee the conspiracy. President Gedu not only lost the thrust of the people but also being sacked by his own government soon. What a dirty game! Whoever they put on power won’t be a game changer will be thrown out like his preceder once he fulfils their dreams.

  2. gghh September 10, 05:05

    less IQ subhuman what trash propoganda you are doing

  3. mulualem September 10, 05:11

    The so called tplf fake eprdf let gedu anderagachew sign on tegede and throw him like a plastic cup kkkkkkk . the very timektgna or arrogance , dominance , dictatorial in the exterim tplfs call amharas temektgna .

View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives