እንኳን ለአድሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ! አድሱ ዘመን የሰላም የደስታና የብልፅግና እንድሆንላችሁ አመኛለሁ !!!!!!

ሳተናው
By ሳተናው September 11, 2017 01:39 Updated

ያለፈዉ አመት የአማራነት ከፍታ መሰረት የተጣለበት ፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃም በሚባል ስንጣሪ ዘዉግ ተከፋፍለዉ የነበሩት የአማራ ልጆች በአማራነት ስጋና መንፈስ ዳግም ተዋህደዉ አማራነትን በህብረት ያቀነቀኑበት፣ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን የፈጠሩ፣ የመሩና ያስከበሩ ስመ ጥር ነገስታትን እንደየ ግብራቸዉ የዘከሩበት ፣ አማራ ለአማራ ቅድሚያ ሰጥቶ የመከረበት ፣ ስለ መብቱ ተግቶ የሞገተበት የከፍታ ዘመን ነበር ።

አድሱ ዘመን እንዳለፉት ዘመናት አማራ አማራ ሆኖ በመፈጠሩ የማይገለልበት፣ የአማራ አባቶች በጅምላ የማይወገዙበት፣ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት የሚበለፅጉበት የኢትዮጵያ ከፍታ ዘመን እንድሆን አመኛለሁ !!!!!!!!!!!

ሙስናን የሚጠየፍ፣ በህግ የበላይነት የሚያምን፣ የተጣለበትን ህዝባዊ አደራ በአግባቡ የሚወጣ፣ ካለፈዉ ግብዝ ትዉልድ የእኔ አዉቅላችኋለሁ እሳቤ የፀዳ፣ እረግጦ ሳይሆን ተመርጦ ለስልጣን የበቃ የህዝብ አገልጋይ መሪ ተፈጥሮ ማየት የአድሱ አመት አብይ ምኞቴ ነዉ !!!!!!

ጓደኞቼ፣ አጋሮቼና ቤተሰቦቼ ! ልጆቼና ባልተቤቴ እንኳን ለአድሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ! አድሱ ዘመን የሰላም የደስታና የብልፅግና እንድሆንላችሁ አመኛለሁ !!!!!!

ባለፈዉ ዘመን ለነበረኝ አነስተኛ ስኬት በግንባር ቀደምትነት ከጎኔ በመቆም ስላበረታችሁኝ፣ ሸክሜን ስላቀለላችሁልኝ ፣ መንገደን ስለመራችሁኝ ተወዳዳሪ ያልነበራችሁ የእኔ ምርጦች ናችሁ !!!!!

ሳተናው
By ሳተናው September 11, 2017 01:39 Updated
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives