መልካም የነጻነት ዘመን:- ሞትን ለተጋፈጣችሁ የህዝብ ቀንዲሎች ሁሉ – ሸንቁጥ አየለ

ሳተናው
By ሳተናው September 10, 2017 22:48

 

እናንተ በእስር: በመከራ እና በእንግልት ዉስጥ የምትመላለሱ የእዉነት ጠበቃ ጋዜጠኞች: ፖለቲከኞች እና የሰበአዊ መብት ተከራካሪዎች ሁሉ ክብር ይገባችኋል::
ስለ ራሳችሁ ሳይሆን ስለወገናችሁ መገፋት ታስራችኋል እና ደስ ይበላችሁ::ስለ ሚገፋዉ: ስለሚራበዉ: ስለሚገደለዉ: ስለሚፈናቀለዉ እና ስለሚጨቆነዉ ህዝባችሁ ተከራክራችኋል እና ክብር ይገባችኋል::ከራሳችሁ ይልቅ ወገንን አስቀድማችኋል እና ብትታሰሩም ነጻ ናችሁ::የተደበደባችሁት እና የተገረፋችሁት ግርፍ የክርስቶስ ኢየሱስ ግርፍ መሆኑን አትርሱት::

ክርስቶስ ስለ እዉነት እና ስለ ሰዉ ልጆች ነጻነት ሊመሰክር ተገፋ እንጅ ስለ መላዕክት ክብር ወይም ስለራሱ መንግስት ሊመሰክር ሲል አልተገረፈም ወይም አልተሰቀለም::እናንተም ስለወገናችሁ: ስለሰዎች ልጆች መበደል እና መገፍት በመቆርቆር ወደ ወህኒ ወረዳችሁ: ተገረፋችሁ : ተገፋቹ እንጅ ስለ እራሳችሁ ክብር እና ጥቅም አልተገፋችሁም::

እናንተ ነጻዎች ናችሁ::ነጻነታችሁን ቀድማችሁ አዉጃችኋል እና::የህዝባችሁን ነጻነትም በመራራ መከራ ዉስጥ እንደምታልፉ እያወቃችሁ እንኳን ቀድማችሁ አዋጅ አስነግራችኋል እና::

ሀያል ናችሁ::ድል እና ማሸነፍ ብቻ አይደለም ሀያል የሚያስብለዉ::ለተገፋ ወገን በእዉነት ስለ እዉነት መቆም በራሱ ከሀያልነትም በላይ የነጻነት ተምሳሌት መሆን ነዉና እናንተ የነጻነት ከዋክብት ሁላ ደስ ይበላችሁ::ግፈኞች መንበርከካቸዉ አይቀርም::እዉነትም መታወጁ እሙን ነዉ::እናንተ ግን እዉነቱ ከመታወጁ በፊት በማወጃችሁ ልትከበሩ ይገባል::ነጻነት ከመታወጁ በፊት የህዝባችሁን ነጻነት በማወጃችሁ የነጻነት ከዋክብት ናችሁ::ፍርሃትን ያሸነፋችሁ: ሞትን የተጋፈጣችሁ: የህዝባችሁ አንደበት የሆናችሁ የህዝባችሁ ቀንዲል ናችሁ እና ለ እናንተ ከፍ ያለ አክብሮት ይገባል::

ፍርሃትን ላሸነፋችሁ: ሞትን ለተጋፈጣችሁ: የህዝባችሁ አንደበት ለሆናችሁ የህዝብ ቀንዲሎች ሁላ መልካም የነጻነት ዘመን ይሁንላችሁ::

የዘመን እና ያዝማናትን ልክ በክንዱ የሚመትር ጌታ እግዚአብሄር የተመኛችሁትን ቀን አፍጥኖ ያምጣው !

ሳተናው
By ሳተናው September 10, 2017 22:48
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives