የመልካም አዲስ አመት መልእክት – ወጉ ነውና እንቁጣጣሽ-በየዓመቱ ያምጣሽ እንባባል!! – ታደሰ ንጋቱ

ሳተናው
By ሳተናው September 10, 2017 23:21

ዐውደ-ዓመቱን ከቤተሰብና ሲቻልም ከቤተዘመድና ከምትቀርቡት ሁሉ ጋር በሠላምና በደስታ እንድታሳልፉ እመኛለሁ!!

በዚህኛው በአለቀው ዓመት ውስጥ በገዥዎች የሚፈጸሙት ግፍና በደሎች አስቆጥተውት ሕዝቡ በከፊልም ቢሆን ጠንካራ ተቃውሞዎቹን አድርጓል። እነዚህ መነሳሳቶች በአዲሱ ዓመት ውስጥ ጎልተው ተስፋፍተውና ርስ-በርስ ተሳስረው መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ለድል እንዲያበቁት ከልብ እመኛለሁ!!\

ዐመቱን በሙሉ ነባርና አመርቃዥ እንዲሁም አዳዲስ ችግሮች የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ክፉኛ ተፈታትነውታል። ግፍና በደሎች በዝተው መላውን ሕዝብ አንገሽግሸውታል። በተወሰኑ
የሀገራችን ክፍሎች ውስጥ በተለይም ወጣቶች ቆርጠውና ደፍረው ገዥዎቻችንን በመጋፈጣቸው እብሪተኞቹ ገዥዎች እንዲርበተብቱ አድርገዋል። ስለሆነም ዐመቱ የማይረሳ
ሕዝቡ በራስ-ተነሳሽነት ብርቱ ትግል ያደረግበት ታሪካዊ ዐመትይ ሆኖ ነው የሚኖረው። ግፈኞቹ ገዥዎች በሠላማዊ ሠልፈኞች ላይ የፈጸሙት ጭፍጨፋ፣ ግድያና ድብደባ፣ በገፍማሠርና ማሠቃየት፣ ለአሥር ወራት የቀጠለ በአስቸኳይ-ጊዜ ዓዋጅ ሥር የተፈጸመ የረገጣ-አገዛዝ፣ በቅሊንጦ እስር-ቤት ውስጥ የተሰጸመው ግድያ፤ በዒሬቻ-በ ዓል ላይ የተፈጸመ የግፍጭፍጨፋ፣ በቆሻሻ ናዳ መደርመስ የተፈጸመ ዕልቂት፣ በድርቅ-ሳቢያ የተባባሰው ከ 8 ሚሊዮን የሚበልጡ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ርሃብና ችጋር፣ በግብር ተመን ስም ነግደውና
ቸርችረው የሚያድሩትን የማፈናቀል ግፍ፤ ….

ይህ እንግዴህ በመላው ሕዝብ ላይ ከሚደርሱት በነባሮች የመብት ረገጣ፣ የአንድ ጎሰኛ ቡድንን ክልል ለማስፋፋት የሚፈጸሙት በደሎች፣ ይሁን ብሎ በርካታውን ህዝብ ርስ-በርስ የማጋጨት ተንኮል፣ መሬት ነጠቃና ባለቤቶቹን የማፈናቀል ተግባር፣ ጭምልቅ-ያለ ሙስና፣ የሕግ-የበላይነት አለመኖርና የፍትኅ ዕጦት፣ የኑሮ -ውድነት፣ ዐይን ያወጣ አድላዊነትና ብልሹ አስተዳደር፣ ወጣት ዜጎች ሀገራቸው-ውስጥ ሰርቶ በሠላም የመኖር ተስፋ-እያጡ ወይንም ለህይወታቸው ከመስጋት እየተሰደዱ በየምድረ-በዳው፣ በየባህሮቹ ዉስጥ በባእዳን ሀገሮች ዉስጥ ለመሠቃየት፣ ለመማቀቅ ለመደፈርና ለዕልቂት እንዲዳረጉ በሚያደርጉ፣ … ሁኔታዎች ላይ በተጨማሪ ነው!!! ገዥዎቻችን ሀገሪቷን ያለጥርጥር የምድር ሲዖል አድርገዋታል!!
በወገንና በሀገር መጨከንም ሆነ ተስፋ መቁረጥ የሚቻል አይደለምና፣ መጭውን ዐመት የተሻለ ለማድረግ ሁላችንም እጅ-ለጅ ተያይዘን እንነሳ!!

ሳተናው
By ሳተናው September 10, 2017 23:21
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!Archives