አማራውን በሂደት ከግዛቱ እናስወጣዋናለን” የሚል ራዕይ የያዘው በህወሃት የሚደገፈው የቅማንት ኮሚቴ አማራ ይዉጣልን በማለት ሆቴሎችን ሰባበሩ

ሳተናው
By ሳተናው September 12, 2017 13:22

አያሌው መንበር

አማራውን በሂደት ከግዛቱ እናስወጣዋናለን” የሚል ራዕይ የያዘው በህወሃት የሚደገፈው የቅማንት ኮሚቴ አይከል ከተማ የሚገኝ ሁለት የአማራ ሆቴሎች ላይ አይከል በሚገኙ የቅማንት ኮሚቴዎች በተደራጁ ወጣቶች አማራ ይዉጣልን በማለት ሆቴሎችን የሰባበሩ ሲሆን፡፡ የአማራና ቅማንት ማህበረሰብ ነገሩን ለማብረድ ጥረት ሲያደርጉ እንዳመሹ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ባካባቢዉ ከፍተኛ ተኩስ የነበረ ሲሆን ህወሃት የመደባቸዉ የጸጥታ ሓይሎች ነገሩን ለማብረድ ምንም ሳያደርጉ መቅረታቸዉ ግጭት ባካባቢዉ እንዲነሳ የህወሃት ትግሬ ፍላጎት መሆኑን ያሳየ ነዉ፡፡ እጅግ ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ ከ50 ሰው በላይ ቅማንት የሆነ በማይኖርባቸው የሰሜን ጎንደር ቀበሌዎች ሁሉ የ10ሺዎች አማራዎችን መብት በሚጋፋ መልኩ ጥያቄ እንዲያነሱ የተደረጉት ራሳቸውን የቅማንት ኮሚቴ ብለው የሚጠሩ በጎንደር የህወሀት ስራ አስፈፃሚዎች “አይከልን በረጅም ጊዜ የቅማንት እናደርጋለን” በሚል ሰሞኑን ድብቅ ሰነዳቸው በጀግና የአማራና ቅማንት ተወላጆች በመሰረቁና በመበተኑ ምክንያት የጨዋታውን ህግ በመቀየር ወደ ግጭት ለማምራት እየጣሩ መሆኑ ታውቋል።

በዚህ አጋጣሚም አይከል ላይ ምልክቱ ታይቷል። ለቅማንት የተሰጡት 42 ቀበሌዎች አማራዉ ምንም ጥያቄ ስሌለለዉና በዚም ምክንያት ግጭት አይነሳም ብሎ ያሰበዉ ህወሃት አማራ ብቻ የሚኖባቸዉን ቀበሌዎ ሪፍረንድም ይካሄድባቸዉ በማለት በሁለቱ ህዝብ ላይ ግጭት እንዲነሳ አበክሮ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ለአማራም ይሁን ለቅማንት ልጆች ያለን መልዕክት ከህወሃት ኮሚቴዎች እኩይ ተግባር በመራቅ ምርጫዉን መጨረስ እንጂ የህዝብ ለህዝብ ግጭት ለማስነሳት እጅግ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ህዝቡ ይሄን ጉዳይ በሰከነ መንገድ ሊያየዉና ሊያከሽፈዉ ይገባል፡፡ ከሌላ አካባቢ የሚኖሩና በስማቸው ካርድ የተሰራላቸውን በምርውጫ እለትና ከዚያም በፊት እንድታሳውቁ፣ ኮሮጆ እንዳይሰረቅ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ነው።

የቅማንት ኮሚቴ የሚባለዉ ጣልቃገብነትን በጋራ እንከላከል።ከዚህም በተጨማሪ እስከዛሬ ድረስ በየቀበሌዎቹ በተመዘገቡት የህዝብ ብዛት መሰረት የቅማንት ኮሚቴ ሁሉንም ቀበሌወች ላይ በሰፊዉ እንደሚሸነፉ ያመኑ ሲሆን ሰሞኑን በላንድ ማርክ ሆቴል (ጎንደር) ስብሰባቸዉ ላይ የምርጫዉን ዉጤት እንዴት ማዛባት እንዳለባቸዉ ሲመክሩ ዉለዋል፡፡ የምርጫ ኮሮጆዉን መገልበጥ ካልቻልን ባካባቢዉ ብጥብጥ በማስነሳት በድርድር ቀበሌዎች ወደ ቅማንት እንዲካለሉ ማድረግ እንችላለን ያሉ ሲሆን፡፡ ማታ ደግሞ ምስራቅ ፔኒሲዎን (ጎንደር) የቅማንት ኮሚቴና የህወሃት ደህንነቶች አልጋ ይዘዉ ሲወያዩ እንደሚያድሩ ዉስጥ ያሉ የቅማንትና የአማራ ልጆች መረጃዉን አድርሰዉናል፡፡

ሳተናው
By ሳተናው September 12, 2017 13:22
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!

Archives