ጎንደር ከተማ ብላጅግ ቀበሌ ከ 50 የሚበልጡ የቅማንት ሰወች ከሩቅ ቦታ በመምጣት ያለ መታወቂያ ካልተመዘገብን ብለዉ ረብሻ ፈጠሩ – አያሌው መንበር

ሳተናው
By ሳተናው September 12, 2017 14:10

ዛሬ ጎንደር ከተማ ብላጅግ ቀበሌ ከ 50 የሚበልጡ የቅማንት ሰወች ከሩቅ ቦታ በመምጣት ያለ መታወቂያ ካልተመዘገብን ብለዉ ረብሻ የፈጠሩ ሲሆን፡፡ ብላጅግ ላይ 1120 አማራ 6 ቅማንት እስከዛሬ ድረስ ተመዝግበዋል፡፡

ቀበሌዉ ሙሉ ለሙሉ አማራ የሚኖርበት ሲሆን ምርጫዉን ለመረበሽና ለማስተጓጎል ብቻ በቅማንት ኮሚቴ ኦርጋናይዝ ተደርገዉ የተላኩ ናቸዉ፡፡ የአካባቢዉ አማራ ለመረበሽ እንደመጡ ሁኔታዉ ስለገባዉ የከተማዉን ምክትል ከንቲባ በመጥራት እዚህ ቀበሌ ላይ ምንም ጠብ እንዲፈጠር አንፈልግም ነገር ግን የማናዉቃቸዉ ሰወች ተደራጅተዉ ለመረበሽ መተዋል ብለዉ ስላመለከቱ፡፡

ከንቲባዉም ከሌላ ቦታ የመጡትን ቅማንቶች ሰብስቦ ወንጀል እንደሆነና ምንም አይነት ግጭት ቢነሳ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ነግሯቸዉ ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡ ምርጫዉ እንዳይካሄድ የቅማንት ኮሚቴ በመበጥበጥ ላይ ይገኛል፡፡ የአካባቢዉ አማራ ነገሩን በትግስት እየጠበቀ ሲሆን ሁሉም መሳሪያዉን ይዞ ተሰባስቦ እንደሚዉል ያገኘነዉ የፎቶ መረጃ ያሳያል፡፡ የቅማንት ኮሚቴ ሚባለዉም አካባቢዉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ አበክሮ እየሰራ ነዉ፡፡

በተለይም እነዚህን ቀበሌወች በምንም መንገድ እንደማያሸንፍ ሲያዉቀዉ የምርጫ ሄደቱ እንዲበጠበጥ እንደሚያደርጉ ከትናንት በፊት ላነድ ማርክ ላይ በነበረዉ ስብሰባቸዉ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ ሊቀመንበሯ ቅማንት ስትሆን በመቶወች የሚቆጠር መታወቂያ አባዝታ ሰታለች ተብሎ የቀበሌዉ ማህተም እንድትነጠቅ ተደርጓል፡፡

ሳተናው
By ሳተናው September 12, 2017 14:10
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!

Archives