የስኳር እና ዘይት እጥረት እንዳማረራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ

ሳተናው
By ሳተናው September 13, 2017 07:15

BBN – በአዲስ አበባ የተከሰተው የዘይት እና ስኳር እጥረት በእጅጉ እንዳማረራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ለቢቢኤን አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ‹‹እጥረቱ መከሰት ከጀመረ ትንሽ ቆየት ቢልም፤ አሁን ላይ ግን አማራሪ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡›› ብለዋል፡፡ እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፣ በአሁን ወቅት ስኳርን በፈለጉት ሰዓት ማግኘት ዘበት ሆኗል፡፡ ዘይትም ቢሆን፣ ከዋጋው መወደድ ጀምሮ እስከ ከገበያ መጥፋት ደረጃ መድረሱንም ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡
በተለይ ከአዲሱ ዓመት የበዓል ሸመታ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ እጥረት እንደተከሰተ የሚናገሩት የችግሩ ተጠቂዎች፣ መንግስት በቂ ምርት አለ ማለቱንም ያጣጥሉታል፡፡ ‹‹በቂ ምርት ካለ ለምን አውጥቶ አያሳየንም ታዲያ?›› ሲሉ ጥያቄ አዘል አስተያየት ያቀረቡት ነዋሪዎቹ፣ ሀገሪቱ በየጊዜው ቁልቁል እየሔደች እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ አክለውም ‹‹መንግስት መሰረታዊ ነገሮችን በአግባቡ አሟልቶ ሳይጨርስ፣ ስለ ዕድገት ባያወራ ይመረጣል፡፡›› ብለዋል፡፡
በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ ከፍተኛ እጥረት መከሰት የጀመረው በተለይ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2002 ወዲህ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ በገበያ ስርዓቱ ላይ ተፈጠረ የተባለውን አለመረጋጋት ለማስተካከል በሚል፣ ነጋዴው ማኅበረሰብ መንግስት ባወጣለት ተመን ዕቃዎችን እንዲቸረችር ተደርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ሁኔታ ከተወሰነ ጊዜ በላይ መዝለቅ አለመቻሉን ታዛቢዎች ያስታውሳሉ፡፡ በወቅቱ መንግስት የእዝ ኢኮኖሚ ስርዓት በመከተል ነጋዴው፣ መንግስት ባስቀመጠለት የዋጋ ተመን እንዲሸጥ ማስገደዱ እስከ ዛሬ ለቀጠለው የገበያ ስርዓት ቀውስ የራሱን አስተዋጽዖ ማድረጉንም ታዛቢዎቹ ይስማሙበታል፡፡
ዛሬ ገበያ ወጣ ብሎ የፈለጉትን ዕቃ ገዝቶ መመለስ ከባድ እየሆነ ነው ያሉት ለቢቢኤን አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ዘይት እና ስኳር አልያም ሌላ ዕቃ ለመግዛት ረዥም ሰዓት ሰልፍ ለመያዝ እንደሚገደዱ ገልጸዋል፡፡ ‹‹መንግስት ነጋዴውን ማኅበረሰብ እንደ ጠላት ስለሚያየው፣ በሁለቱ አካላት መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር አድርጓል፡፡›› ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ መንግስት በተለያየ ጊዜ በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ የተከተለው አካሔድ፣ ለሀገሪቱ የገበያ ስርዓት መመሰቃቀል ትልቅ ሚና ተጫውቷል ብለዋል-ነዋሪዎቹ፡፡

ሳተናው
By ሳተናው September 13, 2017 07:15
Write a comment

No Comments

No Comments Yet!

Let me tell You a sad story ! There are no comments yet, but You can be first one to comment this article.

Write a comment
View comments

Write a comment

Your e-mail address will not be published.
Required fields are marked*

ትኩስ ዜናዎችን ቀድመው ለማግኘት ይመዝገቡ.

ሳተናው ሰበር ዜና - ማወቅ መብትዎ ነው!

Archives