መኢአድ እና ሰማያዊ የአዲስ አበባን አስተዳደር ከሰሱ

መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ

“ዕውቅና ነፍጎናል” ባሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ አካል ላይ ክሥ መመሥረታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡

“ዕውቅና ነፍጎናል” ባሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንድ አካል ላይ ክሥ መመሥረታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቁ፡፡ፓርቲዎቹ ዶሴውን የከፈቱት የፊታችን ዕሁድ፣ መስከረም 28 / 2010 ዓ.ም ሊያካሂዱት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ዕውቅና ሳያገኝ ከቀረ በኋላ መሆኑን ገልፀዋል።

በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው መመሪያ እንዲሰጡም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለአንዳንድ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደብዳቤ ማስገባታቸውን አመልክተዋል።

ፓርቲዎቹ በጠሩት በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ተማሪዎች ላይ ተወስዷል ያሉትን “ኢሰብዓዊ” ሲሉ የጠሩትን እርምጃ አውግዘዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

[jwplayer mediaid=”38793″]

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.