አባይ ወልዱ ትግራይን የመምራት አቅም የለውም ሲሉ የህወሃት የጉባኤ ተሳታፊዎች መቃወማቸው ተነገረ

የህወሃት የጉባኤ ተሳታፊዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም አባይ ወልዱ ትግራይን የመምራት አቅም የለውም ድህነትና ሙስና እንዲስፋፋ አድርጎ ህዝባችንን እያሰቃየ ነው የሚል ሃሳብ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።

ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደው የይስሙላ የህወሃት ጉባኤ የተሳተፉ ሰዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካቀረቡት ሃሳብ መካከል አባይ ወልዱ የትግራይ ክልልን መምራት የለበትም በሱ ፋንታ አርከበ ዕቑባይ መምራት አለበት ካሉ በኋላ ምክንያቱም ህወሃት ስልጣን እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ምንም ለውጥ የሚባል ነገር አልታየም በሙስና እሱ ተዘፍቆ ሌሎችም እንዲጨማለቁ ፈቅዷል ህዝቡም ችግሩን እንዲፈታለት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ፈጣን ምላሽ አይሰጥም በአጠቃላይ አባይ ወልዱ አቅም ስለሌለው ይወገድ የሚል እንደነበር ምንጮቻችን ከስፍራው ያደረሱልን መረጃ አብራርቷል።

መረጃው ጨምሮም- በዞን ደረጃ ሙስና ከታየባቸው ዞኖች መካከል ምዕራብ ትግራይ መሬት ለሃብታሞች በማደል በርካታ ገንዘብ መቀበል በመቀለ ዞንም የቤት መስሪያ መሬት እንሰጣችኋለን ለግል ጥቅማቸው ገንዘብ መቀበል ማዕከላዊ ዞን ለከተማ ልማት የተመደበ በጀት ተባብሮ ማጥፋት በአጠቃላይ የትግራይ ክልል በልማት ኋላ ቀር እንድትሆን ያደረጉ ባለስልጣናት መቀየር እንዳለባቸው ቀርቦ መፍትሄ ሳይደረግበት እንደታለፈ ታወቋል።