የዓባይ ፀሓየ ኑዛዜ ጊዜው ከመሸ በኋላ መናዘዙ ፋይዳውና ወጤቱ ለምንድነው? – አስገደ ገብረስላሴ

 

ከአሰገደ ገብረሥላሴ

ዓባይ ፀሃየ ለሀ ወ ሓ ት ኢ ህ ኣ ደ ግ በሊቀመንበር በድርጅት ሃላፊነት እጅግ ብዙ ኣጃቢና የህወሓት ሎሌ ፓርቲዎች ፈጥረዋል:: በመንግስት መዋቅር በፈደራል ጉዳዮች በስኳር ኢንዱስትሪዎች በጠቅላይ ምኒስቴር አማካሪነት ሰርተዋል:: 40 ዓመት ሙሉ በስልጣን በነበሩበት ቡዙ ስራዎች ፈፅመዋል:: በተለይ በሀወሓት ኢህአደግ ስርኣት ውስጥ ዘርፈብዙ የመልካም ዓስተዳደር የፍትህ የሰብኣዊ ዲሞክራሲ መብቶች መጠበቅ ተጥሰዋል:: በ5 ዙር ሃገራዊ ምርጫ ብዙ ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ኣባሎቻቸው ታስረዋል ተገድለዋል:: ካገር ውጭ ተሰደዋል:: ፕሬሶች ተዘግተዋል:: እጅግ በዙ ጋዜጦኞች ታስረዋል ተገርፈዋል ወደውጭ ፈልሰዋል:: በየተሰደዱበት ሞተዋል::

ህወሓት ትላንትና ለደርግ ፋሽሽት እያለ ሲኮንን የነበረ ህወሓት ልክእንደደርግ ንጹሃን ዜጎችም ገድሏል:: የሥቃይ ምርመራ ፈጽሟል:: ይህ ተግባር በጋምቤላ በሁሉ የኦሮሞ ክፍለሃገራት በደቡብ ብሄረሰብ በኦጋዴን በትግራይ በጎንደር በጎጃም በኣዲስአበባ ወ ዘ ተ ተፈፅሟል:: የእምነት ነፃነት ተጥሶ ከሁሉም ኣማኒያነ መሪዎቸነ ተራ አማኒያን በወህኒ ቤት ታጉረዋል:: የሞቱም ኣሉ በመላው የሃገራችን ህዝቦች በትግላቸው ፋሽሽት ደርግ ኣስወግደው ከህወሓት ይጠብቁት የነበረ ሰላም ፍትሕ ነጻነት የህግ የበላይነት ልማትና ፀጥታ መረጋጋት ሁሉም አይነት መብቶች ነበር ግን አልሆነም ውሀ ዘግነው ቀሩ::

በኣንፃሩ ኣባይ ፀሀየና ጓዶቻቸው ኣይናቸውን በጨው ታጥበው ይህችን ሃገር ወደወታደራዊ አገዛዝ ኣስገቧት;:
በኢህአደግ 10ኛ ጉበኤ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተዘጋጅቶ አንብበው ተበሎ የተሠጣቸው ሪፖርት ካነበቡ በኋላ አባይ ፀሃየ አስታያየት ሲሰጥ ያረጋገጠልን ቢኖር “ህዝባችን እሥካሁን ድረስ ነገ ከነገወድያ ይሻሻላሉ እያለ ተሸክሞን መጥተዋል በሁሉም መንገድ ፈትኖናል:: ለዚሁ ማሳያ በዘንደሮ ምርጫ ህዝብ እንዳልመረጠን አሳዩቶናል” ብለዋል::
በመጨረሻ አባይ ጸሃየ የተናዘዘው እንዲህ ይላል በአሁኑ ጊዜ ለህዝባችን መልካም አስተዳደር የማረጋገጥ ጉዳይ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው; በመልካም አስተዳደር ስርነቀል ለወጥ ካላመጣን በከባድ አደጋ ነው የምንወድቀው ብለዋል:: ዋዋ አባይ ፀሃየ የትሊያደሩ ነው?

የአባይ ፀሃየ ነገር ግን የሚገርመው ያ 17 ዓመት ሙሉ ታግሎ ተሸክሞ ወደ ሙቅ ወንበር የሰቀላቸው ኋላም 24 ዓመት ሙሉ እየቀጠቀጡት የመጡት ፍትሕ ዲሞክራሲ ልማት ኣጥቶ ወደ ኣረብ ና ኣፍሪካ አውሮፓ የተበታተነው ቀይ ባህር መዲትራንያን ህንድውቅያኖስ ባህር የበላው ወጣት እህት ወንድም ና በትግራይ ያለው ስር የሰደደ ማህበራዊ ችግር ሊታየው አልቻለም ስለሆነም የአባይ ፀሃየ በአሟሻሹ በ11 ኛ ው ሰኣት ኑዛዜ የጭንቀት ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.