ገድለው አስከሬኑን በጅብ ያስበሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በፉርጋሳ ትርፌሳ

በዱላ ደብደበው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን በጅብ እንዲበላ አድርገዋል ያላቸውን ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ:: በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በአካባቢው ከሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ተዝናንቶ ሲወጣ ከመንገድ ላይ ጠብቀው በዱላ ደብድበው ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን ጅብ እንዲበላው በማድረጋቸው ነው ተብሏል::
እንደ ፖሊስ መምሪያው ገለፃ ከሆነ የሟች በቀለ ጫላ አስከሬን በጅብ ተበልቶ ማንነቱን ለመለየት አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም በተገኘው መታወቂያው መሰረትም ምሽቱን በሆቴል ውስጥ ሲዝናና ያየው ሠው እንዳለውም አንዱ የሚያውቀው ተጠርጣሪ ተከትሎት እንደወጣ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው መቻሉን ነው የተገለፀው:: በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጀመረው የምርመራ መዝገብ እንደተጠናቀቀ ለሚመለከተው የፍትህ አካል እንደሚላክ ፖሊስ ጠቁሞ የሟች አስከሬንም ለምርመራ ወደ ደግማዊ ሚኒሊክ ተልኮ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑም ተገልጿል::

Source – http://www.federalpolice.gov.et/documents/10157/20991/D_30-11-2007+police+ena+ermejaw+gazeta.pdf

34

Spread the love
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  
  •  

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.