የፌስቡክ ተቃዋሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል…! (አምዶም ገብረስላሴ)

Abay-Wolduየትግራይ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኣብዮታዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው መሆኑ በኣባይ ወልዱ የሚመራው የህወሓት ኣንጃ ኣሳወቀ።
ኣንጃው ይህ ኣብዮታዊ እርምጃ እንደሚ ወስድ ያሳወቀው “12ተኛ ጉባኤ እንዴት ኣለፈ…?” የሚል ኣጀንዳ በየመንግስት መስርያ ቤቶች፣ ከመቐለ ከተማ ኑዋሪዎች፣ የክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ካድሬዎችና ኑዋሪዎች ውይይት እየተካሄደ ነው።

በመቐለ ማዘጋጃ ቤት ማክሰኞ 3/ 13/ 2007 ዓ/ም በኣቶ ተስፋኣለም ተወልደብርሃን (የመቐለ ከንቲባ)፣ ኣቶ ኣሰፋ ተገኝ ምክትል ከንቲባ የተመራ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን የህወሓት ጉባኤ ምን ይመስላል? የሚል ኣጀንዳ የተሰጠው ሲሆን የትግራዩ ኣንጃ በጉባኤው ወቅት በፌስቡክና በተባራሪ ወሬ የኣቶ ኣባይ ወልዱ ስም ክፉኛ ጠፍቷል በሚል እሳቤ የስም እዳሴ እያካሄዱ ነው።

1) ህወሓት ተከፋፍለዋል የሚል ወሬ ውሸት ነው።

2) ዳዊት ገ/ሄር በትግራይ መንግስት የሰጠው ቃለ መጠይቆች ውሸት ነው።

3) በፌስቡክ የሚሰራጩ መልእክቶች ውሸት ናቸው እንደታምኑ።

4) የጉባኤው ተሳታፊዎች ሚስጢር እንዲጠብቁ ማስጠንቀቅያ ቢሰጣቸው በቀጥታ ስርጭት ሊባል በሚችል ደረጃ በፌስቡክ ተዘግቧል።

5) በኣሁኑ ሰዓት ሁለት ዓይነት ጠላቶች ኣሉን። ፊት ለፊት ወጥተው የሚታገሉን እንደ ዓረና የመሰሉና በውስጣችን ሁኖው የሚታገሉን ክራይ ሰብሳቢ ሃይሎች( ከቅርብ ግዜ ጀምሮ በፌስቡክ ደረጃ ህወሓት መስለው ጀርባችን የሚወጉን ሃይሎች) ናቸው።

6) ኣባይ ወልዱ ሙስናን የሚጠየፍ፣ ታግሎ የሚያታግለን ጀግናና ብቁ መሪ ነው።

7) በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን።

8) ጉባኤው ፍፁም ዲሞክራሲያዊና በድል የተጠናቀቀ ነበር። ወዘተ የሚል ሃሳብ ወደ ተሳታፊዎች ኣቅርበዋል።

ተሰብሲቢዎቹ ታማኝ ካድሬዎችና ኣባላት በጥንቃቄ የተመረጡ ቢሆኑም ያቀረቡት ሃሳብና ተቃውሞ ግን ስብሰባው ላዘጋጀው ኣካል ኣስደንጋጭ ነበር።

ከተሳታፊው የቀረቡት ጥያቄዎች
ሀ) ኣባይ ወልዱ በጉባኤተኛ በ20ኛ(የፌስቡክ ማህበረሰብ ከክፍል 20ኛ ከዩኒት 1ኛ ብሎ የቀለደበት ነው።) ደረጃ ተመርጦ እያለ ሊቀ መንበርነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ? እዚህ ላይ የጉባኤው ዲሞክራሲያዊነት የቱ ላይ ነው?

ለ) እነ ኣርከበ በድምፅ እንዲሳተፋ የተደረገበት፣ ለማእከላይ ኮሚቴ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉበት ኣሰራር በየትኛው ደንብ ይገኛል?

ሐ) ዘመኑ ያመጣው የፌስቡክ ቴክኖሎጂ ህዝቡ እንዳይጠቀም እርምጃ እንወስዳለን ማለታቹ ግዜው የ21ኛ ክፍለ ዘመን መሆኑ ስላልገባቹ ነው? የሃይል እርምጃ ቴክኖሎጂው ምን ያህል ይቆጣጠረዋል ብላቹ ታስባላቹ?

መ) ኣቶ ዳዊትና ተቃዋሚ ድርጅቶች የሚነሱት ጉዳይ በመሬት ያለና ቀንተቀን የሚያጋጥመን ሃቅ ሁኖ ሳለ ኣትመኑት ውሸት ነው ማለታቹ ችግሮቹ ለመፍታት ኣቅም እንዳጠራቹ ኣያመላክትም ወይ? የሚሉትና ሌሎች ፈታኝ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆኑ የመቐለ ከንቲባና ምክትሉ የሚመልሱት ኣጥተው አንገታቸው ኣቀርቅረው በሃፍረት ከስብሰባው ወጥተዋል።

የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች የመሩት የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባዎች እየተካሄዱ ያሉ ሲሆኑ ዘመቻው ኣቶ ኣባይ ወልዱ የደረሰባቸው የይውረድልንና የስም ማጥፋት ዘመቻና የጠፋው ስም እንደገና የማደስ ስራ ተጠምደው ይገኛሉ።

የዚህ ዘመቻ ትኩረት ተደርጎ ያለው ፌስቡክና የፌስቡክ ተጣቃሚ ዎች ናቸው። ሰብሳቢዎች በተለያዩ መድረኮች ፌስቡክ ወጣቱ ትውልድ በኣሉታዊ ጎን እያበላሸው፣ የተቃውሞ መንፈስ እየበረዘውና እየበከለው በመሆኑ መንግስት እርምጃ ይወስዳል በማለት ኣዋጅ እያስነገሩ ይገኛሉ።

በክፍለ ከተሞች ከተካሄዱ ስብሰባዎች የሓወልቲ፣ ዓይደር፣ ሓድነትና ቐዳማይ ወያነ ተሰብሳቢዎች ከፍተኛ ውጥረት የተፈጠረ ሲሆን ባለ መግባባት ሊበተን ችለዋል።

ፌስቡክ ኣስመልክተው ከቀረቡት የኣቤታዊ እርምጃ ይወሰዳል ዛቻ ለትግራዩ ኣንጃ ደጋፊዎች የቀረበ ግምገማ ” በቁጥር እኛ እንበዛለን፣ በኢንቴርኔት ኣክሰስ እኛ እንቀርባለን፣ ለነዚህ በጣት የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተቃዋሚዎች መቃወምና ማሸነፍ ለምን ኣቃተን…?” የሚል ቁጭት ኣቅርበዋል።
እቺ ነገር መንግስቱ ሃይለማርያም ” ትጥቅ ኣቀረብን፣ ስንቅ ኣቀረብን፣ ኣሁን የቀረን ልብ ማደል ነው። …… እንደ ወያነ ጠንክራቹ ኣትዋጉም ወይ…!” ብሎ ያደረገው የተስፋ መቁረጥና የስርዓቱ ማብቅያ ኣመላካች ንግግር በእጅጉ ይመሳሰላል።

የህወሓት ኣንጃዎች ክፍፍል ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በነ ዶክተር ሰለሞን ዑንቋይ ለቀናት የፈጀ ሽምግልና ከመበተን እንደዳኑ ፀሓይ የሞቀ ሓቅ ለመካድ ቢሞክሩም ከህዝቡ የተሸፈነ ግን ኣልነበረም።
ኣሁን በመላ የትግራይ ወረዳዎች የኣባይ ወልዱ ስም ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ፊታውራሪ የሆኑት ዶክተር ደብረፅዮን በ12ኛ ጉባኤ የፌስቡክ የሚነሱ ሃሳቦች እንደ ትልቅ የሃሳብ ምንጭ ተቆጥሮ በጉባኤው ቀርቦ እንደተወያዩበትና ለጉባኤው እንደ ግብኣት እንደተጠቀሙበት ለቪኦኤ መግለፃቸው ይታወሳል።

የኣባይ ወልዱ ስም ለማጥፋት ኣገልግሎት ውለዋል የተባለው ፌስቡክና ተቃዋሚ ተጠቃሚዎች ኣቤታዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።
የኢንቴርኔት ማእከላት ሊዘጉ ይችላሉ። ማነው ትግራይ ሰሜን ኮርያ ያላት ያው ውድድራችን ከሰሜን ኮርያ መሆኑ ነው።

ትግራይ ለምትገኙ ፌስቡክ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያውያን ኣብዮታዊ እርምጃ እንዳይወሰድባቹ የመንፈስ ዝግጅት ብታደርጉ እንመክራለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

IT IS SO……!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.