የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል

ከዳባት አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው መንገድ በአገዛዙ ከፍተኛ ባለስልጣናት ውሳኔ መታጠፉ ተገለፀ፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከዚህ ቀደም መንገዱ የሚገነባበትን አካባቢ ህዝብ ማለትም ከዳባት እስከ ጠገዴ ለሚገኘው ነዋሪ መንገድ ሊገነባለት ዕቅዱ እና በጀቱ አልቆ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ቃል ከመግባት አልፎ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ አድርጎ ነበር፡፡ የይስሙላሁ ጠ/ሚንስትር ኃ/ማሪያም ደሰላኝም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ዓመት በፊት ጎንደር ተገኝቶ “ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ የሚደርስ መንገድ በፌድራል መንግስቱ ወጭ እንገነባለን…” ሲል ቃል ገብቷ፡፡ ነገር ግን ከሰሞኑ ዕቅዱ መሰረዙ ለወረዳው ባለስልጣናት ከፌድራል አገዛዙ ባለስልጣናት በቀጥታ ተገልፆላችዋል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ድረስ ሊሰራ የተከለለው መንገድ ግንባታ ዕቅድ የታጠፈው መንገዱ ጠገዴ ከደረሰ በቀላሉ ከወልቃይት ጋር ይገናኛል በሚል ምክኒያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ የህወሓት አገዛዝ የወልቃይትን ህዝብ ያለፍላጎቱ ከጎንደር ገንጥሎ ከትግራይ ጋር በመቀላቀል በኃይል አፍኖ ረግጦ እየገዛው መሆኑ የሚታወቅ ነው በመሆኑም መከረኛው የወልቃይት ህዝብ ከማንም እንዳይገናኝ ለማድረግ እና ነጥሎ ለማቆየት ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ የታቀደው መንገድ ተሰርዟል፡፡
ከዳባት-አጅሬ ጠገዴ ሊሰራ በዕቅድ ተይዞ የወልቃይትን ህዝብ ለመነጠል ሲባል ብቻ የተሰረዘው መንገድ እንዲገነባ በህዝቡ የተጠየቀው ከ1997 ዓ.ም በፊት ነበር፡፡
የአካባቢው ህዝብ መንገዱ አይሰራም በመባሉ ብቻ ሳይሆን አገዛዙ ዕቅዱን ለመሰረዝ የተነሳሳበት ምክንያት እጅግ በጣም እያበሳጨው እንደሆነ እና ለለውጥ ለመታገል ውስጥ ለውስጥ መደራጀት መጀመሩን የአርበኞች ግንቦት 7ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች የላኩልን መረጃ ያረጋግጣል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.