ድርቅ ሂወት እየቀጠፈ ነው…! – አምዶም ገብረስላሴ

ድርቅ በትግራይ ኣስከፊ ሁኔታ ላይ በመድረሱ የቤት እንስሳ ሂወት እየቀጠፈ ነው።

በትግራይ ኣብዛኛው ወረዳዎች የድርቅ ኣደጋ የተጠቁ ሲሆኑ እጅግ ኣስከፊ የሚባል ጉዳት ያደረሰባቸው ወረዳዎች ግን ኣፅቢ ወንበርታ 12 ቀበሌዎች፣ የክልተ ኣውላዕሎ በርካታ ቀበሌዎች፣ ኣብዛኛው ራያ ዓዘቦና ራያ ኣለማጣ ቀበሌዎች፣ የኦፍላ ግማሽ ቀበሌዎች፣ ኣብዛኛው ሕንጣሎ ወጀራት፣ ከግማሽ በላይ ሳምረ ሰሓርቲ፣ ኣብዛኛው ጣንቋ ኣበርገለ ወረዳ፣ የምዕራባዊ ዞን የርካታ ቀበሌዎች ናቸው።

በተጠቀሱት ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት የእንስሳት ምግብ እጥረት ኣጋጥሞ በርካታ የቤት እንስሳት ለሞት ተዳርገዋል።

የትግራይ ክልል መስተዳድር ምንም ዓይነት የሂወት ኣድን ስራ መስራት ኣልቻለም። በጣም የሚያሳዝነው መንግስት ሃላፊነቱ በመዘንጋት በድርቅ ለተጠቁ ኣከባቢ ኑዋሪ ገበሬዎች “በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቹ ሽጣቹ ተገላገሉ” የሚል መመርያ መስጠቱ ነው።

በጣም የሚገርመው እስካሁን ለእንስሳም ይሁን ለሰው እርዳታ ማቅረብ ያልተጀመረ ሲሆን በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች ኑዋሪ የሆኑት የዓረና ኣባላት ከጥናቱ ውጭ እያደረጓቸው ይገኛሉ።

ለምሳሌ በኦፍላ ወረዳ ዓረና_መድረክ ወክሎ ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረው ኣቶ ጡዕማይ ስዩም “ዓረና ይርዳህ” በማለት ከእርዳታው ውጭ በማድረግ ከነብስ ማጥፋት የማይተናነስ ወንጀል እየፈፀሙ ይገኛሉ።

ከድርቅ ኣደጋ በተጨማሪ በርካታ ቀበሌዎች በበረድና የጎርፍ ኣደጋ ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ ሆኖባቸዋል። የህወሓት መንግስት ለነዚ ተጎጂዎች “እርዳታ ስጡኝ” ብሎ ለልመና ለዓለም ማህበረሰብ እጁ ዘርግቷል።

ይሁን እንጂ ኣስቸኳይ እርዳታው ለፖለቲካዊ ጥቅሙ እያዋለው ይገኛል።
የዚህ ወንጀል ሰለባ ከሆኑት በዓብይ ዓዲ_ሃገረሰላም ምርጫ ክልል የዓረና_መድረክ የክልል ምክርቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት ኣቶ ኪሮስ ታደስ እንደሌሎች የደጉዓ ተምቤን ወረዳ ደጎል ወያነ ቀበሌ ኑዋሪዎች ሰብላቸው በበረድ ከጥቅም ውጭ የሆነባቸው ሲሆኑ ለዚህ ጉዳት ለመከላከል ጥናት የሚያደርጉ የወረዳው ሹመኞች የቀበሌው ህዝብ እንደተሰበሰበ “ዓረና ይርዳህ” ተብለው ከነቤተሰባቸው ከሞት የማይተናነስ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተወስኖባቸዋል።

ይህ ስራ በ1977 ኣስከፊው ድርቅ ወቅት በትግራይ ህዝብላይ ሻእብያ የወሰደው ኣስነዋሪ ውሳኔ በህወሓት እየተደገመ መሆኑ የሚያመላክት ነው።

የትግራይ ክልል መንግስት በድርቅ ለተጠቁ ኣከባቢዎች የውሃና ሳር ድጋፍ እስካሁን ኣለደረገምና እየጠፋ ያለው የእንስሳ፣ ሂወትና በእርዛት ነብስ ውጪ ነብስ ግቢ እያለ ያለው ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ ማድረግ ይገባዋል።

ከኦሮምያና ዓፋር ክልሎች ተሞክሮ እንዲወስድም እንጠይቃለን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው……!

IT IS SO………!

Drought