(ሰበር መረጃ …) አሳዛኙ የሚና / ጀማራት አደጋ – * የሟች ቁጥር 700 በላይ የቆሰሉት ከ800 በላይ ደርሷል * ከቆሰሉትና ከሟቾች መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ተብሏል

ሰበር መረጃ … አሳዛኙ የሚና / ጀማራት አደጋ … ! Updated
==============================
* የሟች ቁጥር 700 በላይ የቆሰሉት ከ800 በላይ ደርሷል
* ከቆሰሉትና ከሟቾች መካከል ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ተብሏል
* የሳውዲ መንግስት ኃላፊዎች የኢትዮጵያን የሃጅ ኮሚቴ ኃላፊዎችን እንዲቀርቡ ጠይቀዋል

saudi saudi 2 saudi 3ዛሬ ማለዳ የሀጅን ሥነ ሥርዓት ተከትለው ሰይጣንን በድንጋይ በሚመታበት ምሳሌ በሚከዎንበት በጀማራት በሀጅ ተጓዦች መካከል በመጨረሻው ሰዓት በተፈጠረ ግፊያና መጨናነቅ በመጨረሻው ሰዓት በተከሰተ አደጋ የሟ ቾች ቁጥር ወደ 700 ከፍ ያለ ሲሆን የቆሰሉት ቁጥርም ከ800 በላይ መድረሱ ታውቋል ! የሟችና የቁስለኞች ቁጥር በየሰአታቱ በመጨመር ላይ ሲሆን የሳውዲ መንግስትና የአረቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ከሚናና መካ በመሆን መረጃውን በሰፊው በመዘገን ላይ ናቸው !

ምንም እንኳን ስለደረሰው አደጋ ገና መንስኤ በውል የተሰጠ ምክንያት የለም ። ያም ሆኖ ሌሊቱን ሙዝደሊፋ ላይ ጸሎት ሲያደርጉ ያሳለፉት ሀጃጆች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ ሚና ጀማራት መምራታቸው ተጠቅሷል ። ጀማራት እንደደረሱም በሰይጣን ላይ ድንጋር የመወርወር ሥርዓት ለመካፈል በሚደረገው ሥርዓት ዛሬ ማለዳ የደረሰው አደጋ ከዚህ በፊት ከተሚከሰተው ግፍያና መተፋፈን የተለየ እንደማይሆን ይገመታል ።

አደጋው ከደረሰ እስከ እስካሁን በመካና በሚና ዙሪያ የሚገኙ የእሳት አደጋ ፣ የአደጋ ጊዜ ተወርዋሪዎች ፣ የቀይ ጨረቃ ሰራተኞች፣ የሰራዊቱ አባላትና ፈቃደኛ የሀጅ ድጋፍ ሰጭዎች ሟቾችንና ቁስለኞች በማንሳት በመረባረብ ላይ መሆናቸው የሳውዲ መንግስት ጠቁሟል ። ከደረሰው አደጋ ጋር የአየሩ ሞቃታማ መሆን አደጋውንና የአደጋ ጊዜ ድጋፉንና አወሳስቦት ተስተውሏል ። አደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በርብርቦቭ ሲቀጥል ቁስለኞችን ወደ ሚናና በአቅራቢያው ወዳሉ ሆስፒታሎች የመውሰዱ ድጋፍ እየተካሔደ ነው !

አደጋው የደረሰበት የጀማራት ህንጻ በርካታ አመታት በሀጅ ወቅት በሚከሰት ግፊያ በርካታ ሃጃጆች ሲሞቱበት ተስተውሏል ። ያም ሆኖ አደጋውን ለመቆጣጠር እጅግ ለህንጻው ከቢሊዮን ሪያል ከፍ ያለ ገንዘብ ወጭ ተደርጎ ህንጻው ከተሰራ ወዲህ በጀማራት ያለውን አደጋ ለመቆጣጠር ተችሎ ነበር ።

በአደጋው ላይ ኢትዮጵያውያን ስለመኖራቸው ከማለዳው ጀምሮ ለማጣራት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጌ ነበር ። ሆኖም የቆሰሉ አሉ የሚልና ከሁለት በላይ የሞቱ እንዳሉ ያልተረጋገጠ መረጃ ደርሶኛል ። የሞቱትን በሚመለከት ቁጥራቸው 2 ብቻ መሆኑን ያገኘሁት ሌላ መረጃ የሳውዲ መንግስት ኃላፊዎች የኢትዮጵያን የሃጅ ኮሚቴ ኃላፊዎችን እንዲቀርቡ መጠየቃቸው ከመንግስት ታማኝ የመረጃ ምንጮቸ መረጃ ደርሶኛል ። ጉደዩን በቅርብ እየተከታተልኩት ሲሆን አዳዲስ መረጃዎች እንደደረሱኝ የማቀርበው ይሆናል !

በአሳዛኙ የጀማራት ሚና አደጋ ዙሪያ በዛሬው የጀርመን ራዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ይኖረኛል ፣ ተከታተሉት!

ነፍስ ይማር !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 13 ቀን 2008 ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.