ሩሲያ የአሜሪካ አውሮፕላኖች በሶሪያ ግዛት እንዳይበሩ የሚጠይቅና የሚያግድ ኦፊሻላዊ ደብዳቤ አስገባች

ሩሲያና አሜሪካ ወደ የት እያመሩ ነው? በትንቢተ ህዝቅኤል ምዕራፍ 38 እና 39 የተነገረው የጉግ ማንጉግ የትንቢት ቃል ሊፈፀም ዳር ላይ የደረሰ ይመስላል. ሰሞኑን ከወደ ሩሲያ የሚሰሙ ዜናወች እጅግ አሳሳቢና አስደንጋጭ እየሆኑ መጥተዋል. በጠንካራ አቋማቸውና በግትርነታቸው በዓለም ዘንድ የሚታወቁት የሩሲያው መሪ ፕሬዝደንት ቢላድሜር ፑቲን ሶሪያና ኢራቅ ውስጥ የሚገኘውን አሼባሪ ቡድን አይስስን እና ሌሎችንም ጽንፈኛ የእስላም ተዋጊወችን ለመደምሰስ በሚል የአየር ሀኃይላቸውን ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያወችን ወደ ሶሪያ እያጓጓዙ ነው.

ይሁን እንጅ ውሎ አድሮ ሩሲያ እግረኛ ወታደሮቿን ማስገባቷ ይፋ ሆነ. ነገሩም ከማንም በላይ እስራኤልን ያሳስባት ጄመር. በኒዪክለር ግንባታ መር በመሆኑም ሃ ግብሯ ጉዳይ ከኢራን ጋር እስጥ አገባ የጀመሩት የጽዮናዊቷ ሀገር መሪ ናታንያሁ ወደ እሩሲያ ለመጓዝ ተገደዱ. የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ናታንያሁ የጉዞ ዓላማም የእስራኤልና የሩሲያ አውሮፕላኖች በሶሪያ ሰማይ ላይ ወደ ለየለት ጦርነት እንዳያመሩ ለመወያየት ነበር. ሞስኮ ላይ ቢቢን በቤተ መንግስት ተቀብለው ያስተናገዱት ፑቲን ሃገራቸው ሩሲያ የእስራኤልን ለዋአላዊነት አንደምታከብር ነገር ግን በሶሪያ ላይ በተደጋጋሚ እስራኤል የምትፈጽመውን የአየር ጥቃት አንድታቆም እንደሚፈልጉ ለነጠቅላይ ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል ሲል ኢንተር ፋክስ የተሰኘው የዜና አውታር ትናንት ዘግቧል. እናም በቀናት ልዩነት እስራኤል በ 1967 ዓ / ም ማለትም በስድስቱ ቀን ጦርነት ከሶሪያ በኃይል በተቆጣጠረችው የጎሊያን ኮረብታ አካባቢ ሁለት የአጭር ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች ወደቁ. እስራኤልም ከዚህ ቀደም እንደምታደርገው ሶሪያን በአዳፍኔ በመደብደብ አፀፋውን ሰጠች. በመሆኑም ይህ አይነቱ ድርጊትም እራሻን ሳያስቆጣ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው.

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሞስኮ ወደ ኒውዮርክ በርረው በተ.መ.ድ ንግግር ያደረጉት ፑቲን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ጋር በሃሳብና በርዕዮተ ዓለም ተጋጭተዋል. አሜሪካንም በጽእኑ ኮንነዋል. ኦባማም እሩሲያ በዩክሬን ጦርነት እጇን ማስገባቷን ጠቅሰው እስኪበቃቸው አብጠልጥለዋታል. ሁለቱን ሀገሮች ያላግባባ ነገር ቢኖር የአራጁ, የገዳዩ, የጨፍጫፊው የባሻር አል አሳድ ጉዳይ ነው. ይኑር ወይስ ይውረድ የሚለው. ሩሲያ በሳድ አል አሻር ጄግናየ ነው ብትልም ሰሚ አላገኘችም. ዘግየት እያሉ የሚወጡ ዘገባዎች እንደ ሚያመለክቱት ከሆነ ሩሲያ ሶራ ውስጥ የአየር ጥቃት እየፈፀመች ነው. ቢያንስ 35 ንፁሀን ሰዎችንም ገድላለች. ዛሬ ደግሞ እየተሰማ ያለው ነገር አስደንጋጭም አስቂኝም ነው. ሩሲያ የአሜሪካ አውሮፕላኖች በሶሪያ ግዛት እንዳይበሩ የሚጠይቅና የሚያግድ ኦፊሻላዊ ደብዳቤ አስገባች. ይህ ነገር ጉግ ማንጉግ ይሆን?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.