ኤርትራ ሄዳ ያልሄደች ሀገር – (ከተስፋዬ መኮንን)

ነጻነት፣ ማንነትና አንድነት የማይለያዩ አንድዮሽነት ያላቸው ናቸው።

ከላይ ላስቀመጥኩት መርህ መነሻ መሰረቱ ቁሳዊው ዐለም ነው። ሂደቱም በቀጣይነት ያለ። ሰው አካባቢውን ሲቆጣጠር አንጻራዊ ነጻነቱን ይቀዳጃል። በዚያ በተገኘ ነጻነት ልክ የአለማወቅ አድማስን ድንበር በገፊ መልኩ አንጻራዊ የማንነት ሰገነት ላይ ይቆማል። ተያይዞም ከሌሎች ሰብአውያን አቻዎቹ ጋር ይገናኛል። አንድነትንም ይፈጥራል። ይህ ነው የሰው ልጅ የማያቋርጥ የህይወት ጉዞ ታሪኩ። ስራ፣ምርትና ልውውጥ፣ማንነትና፣አንድነት ምንጊዜም ሳይለያዩ የሚጓዙ የሰው ልዩ ባሕሪያት ናቸው። ሁልጊዜም በሽግግር ላይ የሚኖር ሕይወት።

እነዚህ ሰብአውያን ያማከሏቸው ሀገራትን የታሪክ እድገታቸውን ሚዛን ላይ አስቀምጠን ዋጋቸውን የምንሰጥ በዚህ የሂደት ጉዞ ውስጥ ሰው የደረሰበትን የእድገት እርከን መለካት ስንችል ብቻ  ይሆናል። ደሀና ሀብታም  ብለንም እንፈርጃለን። ፍትሀዊና ጨቋኝ ስርአት ብለንም የህሊና ፍርድ እንሰጣለን።

ሐገራችንንም የምንመለከት ከዚሁ ሚዛን አኳያ ነው። ኤርትራንም እንደዚሁ። ዛሬ እነዚህ በረጅም የታሪክ ጉዞ በአንድ ላይ የነበሩ ሕዝቦች በሁለት በተከፈለ መልካ ምድር ላይ ተካለውና ተለያይተው እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል። ለመለያየት ህልክ ያስጨረሰ ጦርነትን አስተናግደዋል። አንድ ትውልድ ዶጋመድ ሁኖ አልፏል። የዚያን ጦርነት መራርነት በቅርብ ሁነው ከተከታተሉትም አንዱ ነበርኩ። በጦርነቱ ውስጥ ልውውጡ የጥይት ብቻም አልነበረም። በሁለት የተፈጠጠ ጦር መሀል አጥንት የሚሰብር የቃላት ጦርነትም ተካሂዷል። ያን መሰሉን በመረረ ጥላቻ የተስተናገደን እልቂት አልፈን፣አስነዋሪ ሽንፈትንም ተጎንጭተን፣ሲለዩንም ለመሸኘትም፣ስሜታችንን እንዳንገልጥም ተከልክለን  ይባስ ብለውም ምርጫችን “ከባርነት ነጻነት”ነው ብለው ሲሄዱ በትዝብ ተመልክተን  ከዚህ በኋላ ዳግም መገናኘት እንዴት ይታሰባል?ብለው የጠየቁም የበዙ እንደነበርም ታዝበናል።

እርግጥ ነው ያንን በብዙ ሰው ሰራሽ የጥላቻ ዘመቻ የተካሄደን ጦርነት ብቻውን ለተመለከተ ምንጊዜም የማይገናኙ ሁለት ሕዝቦች ብሎ መደምደም ይቻላል  በጊዜው የነዚህ በሁለት የመሬት ወሰን እንዲከለሉ የተደረጉ ሕዝቦችን ምንጊዜም እንዳይገናኙ ተፈልጎ የተሰራ ደባ እንደ  ነበር ደጋግመን አሳይተናል  መለያየት ያልነበረባቸው ሕዝቦች ናቸው እንዲለያዩ የተደረጉት  ኤርትራ ለትዳር የሚያበቃት ማንነቷን ሳታገኝ ነው ሳትዳር ኮብልላ እንድትሔድ የተደረገ  ዛሬ ኤርትራ ከናቷ ተለይታ ከጫጉላዋ ወጥታ የመኖሪያ ጎጆዋን መቀለስ የተቸገረች ልጅ የሆነችውም በዚያ ምክንያት ነው።

ይህንን አስመልክቼ ሸአብያ ኤርትራን ሳይዝ፣ ህወሀትም ሀገሬን ሳይወስድ በጻፍኩት ይድረስ ለባለታሪኩ መጽሀፌ ላይ ሰው ሰራሽ ማንነት በእድገት ፈቅ እንደማያደርግ ገልጫለሁ  እንዳው ህዝብን ወደማያልቅ የእልቂት አዙሪት ውስጥ መክተት መሆኑን አመልክቻለሁ  የዚህንም ትክክለኝነት ከ25 አመታት በኋላ እናት ሀገር ኤርትራ ያለችበትን አሳዛኝና ምናልባትም ፌቷ የቆመን የመበታተን አደጋን እንታደግ በሚል ጩኅት ልጇ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሀኔ “ኤርትራ እንደ እናት ሐገር፣ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም”በሚል ርዕስ በጀንዋርሪ 2013ላይ በተጻፈ የጥናት ፅሁፋቸው ላይ  እኔ ከ25 አመታት ቀደም ብዬ ለስለስ ባለ የብእር አንደበት ስገልጥ የተጠላሁበትን እርሳቸው ያገጠጠውን እውነት እንዳለ ስለአቀረቡት ለግልጥነታቸው ሊመሰገኑ ይገባል።

እጠቅሳለሁ “ኤርትራ ሦስተኛ ዓለም ተብለው ከተመደቡት አገሮች አንዷ ነች  ይህች አገር በውስጣዊ የታሪክ ሂደት የተገነባች ሳይሆን ጣሊያን ከውጭ መጥቶ ለጣጥፎ ያቆማት ሰው ሰራሽ አካል ናት  ከጣሊያን ቅኝ አገዛዝ በፊት ኤርትራ ለብቻዋ እንደ አንድ አካል የቆመች አልነበረችም  እንዳውም ደጋማው ክፍል የሰሜን ኢትዮጵያ አካል ነበር  ምእራባዊው ቆላማው ክፍልም በባህላዊው ራስ ገዝ ህይወታቸውን ሲመሩ የነበሩ አብዛኛውን ጊዜ ከምስራቃዊው ሱዳን አካባቢ ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲከሰት የነበረ ግኑኝነት ነበራቸው  በ1941የኢጣሊያን ቅኝ ግዛት ካበቃ በኋላ የታሪክ ድጋፍ አለን በማለት ኢትዮጵያና ግብጽ ኤርትራን በመላ ወይንም በከፊል እንዲሰጣቸው ጠየቁ  እንግልዝና ኢጣሊያንም የየራሳቸው ስትራተጂ ነበራቸው  እንድዲያውስ ኤርትራ ሉዐላዊ እናት ሀገር ለመሆን ብቃት አላትን?የሚል ፈታኝ ጥያቄ ወደ ግልጽ መድረክ ብቅ ማለት የጀመረው በዚህ ወቅት ነበር  ”ፕሮፌሰር በዚህ ጥናታቸው ያስቀመጡልን ስንለው የመጣነውን የማንነት ጉድለትንና በሁለቱ ህዝቦች መሀል የነበረን የታሪክ አንድነትን ነው  በጥናታቸው ዛሬ በኤርትራ የግዛት ክልል ውስጥ ያለውን የአፋርን ህዝብ ስለመኖሩም የሚሉት ነገር የለም።

ታዲያ ይህን የራስን የነጻነት ጎጆ ለመቀለስ ወሳኝ የሆነን የአንድ ህዝብን የማንነት ጥያቄን በምን ማሟላት ተፈለገ?የሚለው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው  ይህ በእንግሊዝ የሞግዚትነት አስተዳደር ወቅት ወደነበረው ጊዜ ይወስደናል  እንግሊዝ ሞግዚትነቱን ወደቅኝ ግዛትነት መቀየር ፈለገች  ባርካንና ቆላማውን አካባቢ ከቅኝ ግዛቷ ሱዳን ጋር እንዲዋሃድ፣አፋር ከኢትዮጵያ ጋር እንዲሆን፣ደጋማውን ትግርኛ ተናጋሪው የኢርትራን ክፍል ምጽዋን አካቶና ከኢትዮ ጵያ ትግራይን ጨምሮ “ትግራይ ትግርኝ”በሚል ግዛት ስር እንዲጠቃለል እቅድ አወጣች  ፕሮፌሰሩ የትግራይ ትግርኝም ርዕዮት በተዳከመ የማንነት መንፈስ ላይ የብሄረተኝነት ትንፋሽን የመርጨት እቅድ ነበረው በሚል ይህ መሰሉ እርምጃም በኢጣሊያን ዐንድነት ታሪክ ላይ የተጫወተውንም ሚና ያነሳሉ  በኤርትራ ውስጥ የተነሱት ግንባሮችም፣በኋላም በህወሀት የተደረገውም ይህን የሌለ ማንነትን እንዲተካ በሚል ጥላቻን መሰረቱ ያደረገ፣ታሪክን ያዛባና በደም የተደገፈ ረጅም የፕሮፓጋንዳ ስራ ተሰራ  እናም መለያየቱ ከአለም የፀረ—ኢትዮጵያ ቅንብር ጋር እጅ ለጅ ተያይዞ ተግባራዊ ሆነ  ከሆነ ላይቀር በመለያየቱ ፀንተን በሰላምና በጉርብትና ለመኖር በቻልን ነበር  አልሆነም  ኤርትራም ሄዳ አልሄደች  እኛም የሰላም ኖሮአችንን አላጋኘን  እንዳው የማያልቅ መታመስ ሆነ የተነዛውም የጥላቻ ዘመቻ ወየበ  ዛሬ በኢርትራ በስልጣን ላይ ያለው ሸአብያ እንደትናንቱ አያስብም  ትናንት “ነጻ አውጪ”  ነበር  እናም ነጻ አወጣዋለሁ ያለውን ህዝብ በአንድ የጥላቻ ልጓም ሸብቦና በአንድ ለጥላቻው ኢላማነት የተመረጠ (የአማራ) ሕዝብ ላይ “ጃስ” ማለት ነበረበት በወቅቱ ዘዴው ሰርቷል  ኢላማውንም በግዛት ነጻነት መገኘት አረጋግጧል  የግዛት ነጻነት መገኘት ግን ብቻውን በቂ አይደለም  ዋናው የሰው፣ የሰብአዊ ፍጡሩ ነጻነት አልተገኘም  እንዳውም ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ ከነበሩበት የኋሊት “አድገዋል”  እንቆቅልሹ ደግሞ እኛም ከነበርንበት ድጥ ወደ ማጡ ወርደን ኤርትራን መቀላቀላችን ነው።

ታዲያ ሸአብያ ዛሬ የሚያስበው እንደ ነጻ አውጪ ሳይሆን እንደ ሀገር መሪ ነው  በዚያን ወቅት አብረነው ሜዳ በነበርንበት ጊዜ “ነጻነታችንን ካላወቃችሁ በግዛቴ አታልፉም” የለበት ጌዜ ላይ አይደለንም  የኤርትራን እንደሀገር መኖር “የአማራ ሊህቃን”ተብዬ እውቅና አያስፈልገውም  በገሀዱ ዐለም ላይ ያለውን እውነታን ተቀብሎ መኖር ብልህነት ነው  ስለሆነም ዛሬ ይህቺን በፕሮፌሰሩ ተለጣጥፋ ስለመሰራቷ የምትነገር ሐገራቸውን ሳትበታተን እንደተለጣጠፈች እንድትቆይ ማድረግ ከባዱ የአመራሩ ዋና ስራ ነው  ለዚህ ዘላቂና ወሳኝ እቅድ እውን መሆን ከማንም ጋር ግንባር ይከፍታል  የመኖር አለመኖር ጥያቄ ነው  በዚህ ረገድ ሸአብያ የዳበረ ተሞክሮ አለው  ለግዛት ነጻነት መገኘት በኢትዮጵያ ከበቀሉ “ድርጅቶች ”ጋር ሲያብር መጥቶ ነው አላማውን ዕውን ያደረገ  አሁን ከሱ የሚጠበቅበት እንደሀገር መሪ ረጅም ርቀት ላለው ግኑኝነት በመልካም ጉርብትና አብረውት ለመኖር የሚያስችሉትን እስትራተጂክ ተጣማሪዎችን ከኢትዮጵያ ፈልጎ ዘላቂ ግንባር መፍጠር ነው  አሁን በቅርቡ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ያደረገው መቀራረብ የዚያ አቅጣጫ ጉዞ ነው።

ሁለቱን ያገናኘ ስትራተጂክ ጥያቄ ምንድነው?ለሁለቱም ወገኖች የጋራ ስትራተጂክ ጠላት ሆኖ ብቅ ያለው ለግዛት ነጻነቱ መገኘት በተደረገ ትግል ከጎኑ ቁሞ ኢትዮጵያን ሲወጋ የነበረው ባንዳው ህወሀት ነው  ከድል በኋላ በሽግግሩ ሂደት ላይ ስለኤርትራ ነጻነት ህጋዊ አካሄድና ስለሕዝበ ውሳኔ አውርተዋል  የሕዝበ ውሳኔው ቃል ሲቀረፅ “ባርነት ወይስ ነጻነት” ብለው በመረጡት ቦታ ሌሎች አማራጮችን ለሕዝቡ አቅርበውለት ቢሆንስ ኑሮ?ብለን ብንጠይቅስ  ያለምንም ጥርጥር በሆነ መተሳሰር ሕዝቡ ከኢትዮጵያ ጋር ይቀር ነበር  ለዚህ ድምዳሜ ምን ማስረጃ አለ?እኛ ሕዝቡን ከኛ ከወገኖቹ ለይቶ የሚያሳየው ማንነት የለውም የሚል የጸና አቋማችንን በሚገባ ያረጋገጠው የፕሮፌሰር ተስፋፅዮን በማስረጃ የተረጋገጠ ሰነድ ነው

እተቅሳለሁ “እናት ሀገራችን (አደቦና)ማነች ትላላችሁ?ሲል ዓለም ሰገድ አባይ በኤርትራ ደጋማው ክፍል ላሉት ተራ ሕዝበ—መጥይቅ አቅርቦላቸው ነበር  21. 4%ብቻ ነበሩ ኤርትራ ናት ያሉት  53.6%እናት ሐገር የሚሏት መንደራቸውን ወይንም እናት አባቶቻቸው ተወልደው ያደጉበትን አካባቢን ነበር  በጣም ጥቂት የሆኑት ትግራይ ትግርኝ ናት ብለው የመለሱ ነበሩ  ተራው የትግራይ ሕዝብሳ?39.3%የሚሆነው ሐገራችን ብለው የሚሏት መንደራቸውን ነው 25%የሚሆ ነው ሐገራችን ትግራይ ናት ብለዋል  የህወሀት አመራርስ?97% የሆኑት ሀገራችን ትግራይ ናት ብለው መለሱ  ”የጥቅሱ መጨረሻ  እዚህ ላይ አንባቢ የሚረዳው ከዚያ በኢትዮጵያ ላይ የከፋ የማስጠላት ዘመቻም ተካሂዶ፣የደጋው የኤርትራም ሕዝብ የጦር ማገዶም ሁኖና የግዛት ነጻነትም ተገኝቶ 53.6%የሚሆነው ሀገራችን መንደራችን ናት ነው ያለው  ኤርትራ ናት አላለም  የማንነት ጉድለት ይሏል ይህ ነው  ይህ መሰረታዊ ነው
ከፕሮፌሰር ተስፋጽዮን ጋር እንቆይ  እጠቅሳለሁ “ኤርትራውያንና ትግሬዎች በጣልያን አገዛዝ ምክንያት ለ62 አመታት ተለያይተው ኖረዋል  ይህ መለያየት ባስከተለው ምክንያት ታሪካዊ ጠላታችሁ ማነው?በሚለው ጥያቄ ላይም ይለያያሉ  ኤርትራ የኢጣሊያን ባሪያ ነበረች  ትግሬዎች ደግሞ የአጤ ዮሃንስ ንግስናን ተነጥቀው በሸዋ አማራዎች ይገዙ ነበር  በዚህ መነሻ ይመስላል ጠላታችሁ ማነው?ተብለው ሲጠየቁ  ከደገኞቹ ኤርትራውያን 86%የሚሆኑት ቱርክን፣ግብጽን፣ጣልያንንና እንግሊዝን በቅደም ተከተል አስቀምጠዋል  በመጭረሻ ያስቀመጡት ንጉሱንና የደርግን አገዛዝ ነበር  ትግሬዎች ግን 82.1%የሚሆነው ጠላታችን አማራ፣በተለይም የሸዋ አማራ ነው ብለው ነበር የመለሱት  ”እንደገናም የደጋው የኤርትራ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ ጠላት አላስቀመጠም  ይህም በሚገባ መጤን ያለበት ነጥብ ይሆናል።

ይህ መጠይቅ ኤርትራ ውስት ላለው ትግርኛ ተነገሪ የቀረበ ጥያቄ ነው  እንኳን ሕዝቡ ባንዲራዋን ግመሏም ታውቀዋለች የተባለለትን የቀይ ባህር የአፋርን ሕዝብ፣ለኢትዮጵያ አንድነት በጦር ሜዳ ተፋልሞ የግዴታ ተይዞ ያላውን የኩናማን ሕዝብ ያካተተ ቃለ መጠይቅ አልነበረም  መጠይቁ እነዚህን ሕዝቦች አካቶስ ቢሆን ኑሮስ የሚሉ ቁም ነገሮችን በአንድ ላይ ይዘን ለኤርትራ ህዝብ ግልጥና የማያሻማ አማራጮች ቢቀርቡለት ኖሮ ያለምንም ማወላዳት በሆነ መተሳሰር ከኢትዮጵያ ጋር ይቀር ነበር ብለን መደምደም እንችላለን  መለስና ኢሳያስ ይህንን በሚገባ በመረዳታቸው ነው “ባርነት ውይስ ነጻነት”የሚል የማያፈናፍን ትያቄን ያቀረቡለት  አማራጭ ቀርቦለት ቢሆን ኖሮ ዛሬ ያላው የሀገራችን የፖለቲካ ገፅታ ፍጹም ሌላ በሆነ ነበር  ኤርትራ በህዝበ ውሳኔው እራሱንም ኢትዮጵያንም ነጻ አወጣ የሚያስብል ታሪካዊ ድርጊት ይሆን ነበር።

ከዚህ በኋላ ወደተነሳሁበት የህወሀት የጋራ ጠላት መሆን አመራለሁ  በወቅቱ ኤርትራውያኖች በጠቅላላና በተለይም አመራሩ ይህን የህወሀትን የጠላትነት እርምጃ ይረዱትም አይረዱት ቋጠሮው የተቋጠረው በዚህ የህዝበ ውሳኔ አቀራረፅ ላይ ህወሀት የተጫወተው ሚና ላይ ነው  ከዚያ የታሪክ ቦታ ላይ ነው ሁለቱን ሀገራት የሚመሩት ድርጂቶች የማይገናኙ ጎዳናዎችን የተከተሉ  ህወሀት በኢትዮጵያ ላይ ቋንቋንና ሰፈራን የተከተለና ለነገ የትግራይ መለየት አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር የዘር አገዛዝን መሰረተ  የኤርትራው መሪ ለኢሳት ተለቪዥን በሰጡት ቃል “መለስ የህገ-መንግስቱን ረቂቅ አሳይቶኝ አለመስማማቴን ገልጫለታለ”ይበሉ እንጂ አጥፊነቱ ለኤርትራም ጭምር እንደነበር አላጡትም  የትግራይ የመለየት ፕሮግራም ከግዛት ማስፋፋት ጋር፣በተለይም ዛሬ ኤርትራውያን ከማይፈልጉት የትግራይ ትግርኝ ታሪክ ጋር የተቆራኘ መሆኑን የኤርትራ ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ የሚስማሙበት ነው  የትግራይ ተገንጣዮች ህልም በትግራይ ትግርኝ መመሪያ የቋንቋው ተነጋሪ የሆነን በየመንደሩ በማፈላለግና ግዛት በማስፋት፣ከኤርትራ ያለውን ትግርኛ ተናጋሪን ጠቅልሎ ታላቅ የአግአዚ ህዝብ ግዛትን በመመስረት “የጠላት አማራን ” ሀይል መቋቋም የሚለው መሆኑ ገሀድ ሁኗአል  ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲሆን ዛሬ በኤርትራ ያለው የህዝብ ሚዛን ይሰበራል  ተለጣጥፋ የተሰራችው ሀገር ትበታተናለች  ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን ይህን አስመልክቶ ሲገልጡ ህወሀት ዛሬ በኢትዮጵያ የዘረጋውን አገዛዝ የትግራይ ትግርኝን መመሪያ የተከተለ ነው ብለው ያምናሉ  ነገ ወደ ኤርትራ እንዳይመጣ የሚፈሩት ይህንን ነው  የአንቀጽ 39ኝንም አደገኝነት ይገነዘባሉ  ከዚህ ስትራተጂክ አመለካከት አኳያ በኤርትራ ተቃዋሚዎችና በመንግስት መሀል ልዩነት የለለም
ከዚህ ነገርን አርቆ ከመመልከት አኳያ በዛሬው የሀገራችን የተቃዋሚ ተብዬው የፖለቲካ ቤተሰብ ውስጥ ያለ አመለካከት የባለህበት እርገጥ እይታ ነው  ምንም መሻሻል የማይታይበት  በተቃራኒው በኤርትራውያን ፖለቲከኞች በኩል የአመለካከት ለውጥ በገሃድ ይታያል  በጦርነቱ ወቅት አንስተውት የነበር የፀረ-አማራ መፈክራቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ህወሀትን በታኝ ጠላት አድርገው ቁመዋል  የሞኝ ዘፈን ደጋግሞ ደጋግሞ እንዲሉ ስልጣን ለብቻው ሳይዝ የስልጣን ባለቤትና ጭቋኝ ተብሎ ሲረገም የኖረ ምስኪን የአማራ ሕዝብ ዛሬም ጠላት ነው  ልጆቹ ለሁሉም ህዝቦቿ አኩል መሆን በግንባር ቀደምትነት ቢሰዉም ዛሬም “የአማራ ሊህቃን” “ሴራ” ሲያባንናቸው የሚያድሩ ጥቂት አይደሉም  ለአንድነት መቆምም የአማራ የብቻ ህመም የሚመስላቸው ቁጥር ቀላል አይደለም  ለአንድነት መቆም የማንነት ጥያቄ መሆኑና ጥያቄውም የአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ መሆኑን መቀበል አይፈልጉም  በመሆኑም ለአንድነት በሚደረግ ተግል ዙሪያ የዚያ የ“ሊህቃኑ”ስውር እጅ እንዳለ ይሰብካሉ  ዘዴው ተወደደም ተጠላ የህውሀትን እድሜ የሚያራዝም እንጂ የነጻነታችንን ቀን የሚያቀርብ አይሆንም  በሌላውም ጎኑ የሰፋ የአንድነት ሀይል ላይ የተሰነዘረ ስድብም ነው።

ዛሬ ተደራጅቶ ውስብስብ ከሆነው የትግል ዘዴውች ውስጥ አንዱን መርጦ መታገል እየተቻለ፣ግለሰቦችም በፖለቲካ ማህበር ጥላ ስር ሳይቆሙ ብዙ ማድረግ እየቻሉ ለምን ጥንትም ያልነበረ፣ዛሬም የሌለ “ጠላት” ይዞ ባደባባይ በማናፋት ጊዜውን እንደሚያባክኑ ያሳዝናል  አንድ ብግልጽ መቀመጥ ያለበት ቁም ነገር አለ  በአናሳ አመለካከት ምክንያት በጠላትነት የተፈረጀው የአማራ ሕዝብ የያዘው ኢትዮጵያዊ መለዮ በወያኔ ጥይትም፣በዘር ምንጠራም፣በጠባብ የዘረኞች እርግማንና ውግዘትም የማወይብ፣የማይጠፋ መሆኑን ሁሉም ሊረዳው ያስፈልጋል  የታሪክ ስሪት ነውና ማንም ኋላ ቀር ጉዞውን አይገታውም  የህወሀትና የወደሉ አህዮቹም ያልተቋጭ የቤት ስራቸው ክሽፈት ምክንያቱ ከዚያ እውነት ይመነጫል
በኤርትራ መንግስትና የትጥቅ ትግሉን እንደ አንድ አማራጭ በወሰዱ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሀል ለተገኘው አብሮ መስራት ምንጩ ህወሀት ከተከተለው የዘር ስርአት ዝንድ ይነሳል  በህወሀት የተነደፈውና በተግባር ላይ የዋለው ስልት የሁለቱንም ሀገራት ውስጣዊ የህዝብንና የግዛት አንድነትን ይንዳል  ህዝቦችን ማለቂያ ወደሌለው እልቂት ያመራል  ይህንን ሰይጣናዊ ሀይል የማስወገድ ተግባር የህሊና ህውከት የሌለውና ማሰብ የሚችል ሰብአውያን ሁሉ ተግባር ሆኖ የቀረበ ጥያቄ ነው  ይህ ተልእኮ በሁለት ሀገር መሪ-ፓርቲዎች መሀል ያለ፣ቢሆን በውይይት እምቢም ሲል በመለስተኛ የማስፈራሪያ የድንበር ግጭት የሚፈታ ቅራኔ አይደለም  ትግሉ ድላማ ከሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘረኛ ህወሀት የተወሰደበትን ነጻነቱን ያስመልሳል  ከወደቀም ለጊዜውም ቢሆን ሊከተል የሚችልን በረሃብና በቸነፈር መጠቃትንና የእርስ በእርስ ግጭትን ተቋቁሞ እንደገና ታጥቆ መነሳቱ አይቀሬ ነው  ይህ ከባድና ወሳኝ ምርጫ ነው  የኤርትራ አመራር ይህን የወስድነውን ከባድ ምርጫ ከዚህ አኳያ ተመልክቶት እንደሆነ ይታመናል  ይህንን በመረዳቱም ነው ከዚህ የኛ ድል በኋላ የተረጋጋችና ሰላሟ ሊጠበቅላት ለምትችል ኤርትራ ሲል የትብብር እጁን የዘረጋው የሚል እምነት አለ።

ይህንን ስትራተጂክ አመለካከት ሳያስተነግድ ቀርቶ አንዳንድ የፀረ-ኢትዮጵያ ሀይሎች እንደሚያቀርቡትና እንደሚመኙት ትብብሩን የሚፈልገው ከህወሀት ጋር ለመደራደሪያነት ለማቅረብ ነው የሚለውን ጎዳና የሚከተል ከሆነ የኤርትራ የግዛት ነጻነት ፕሮግራም የሙከራ ጊዜ ብቻ ሆኖ ወደመፍረሻው ጎዳና ውስጥ ይገባል  የኛ ትግል ግን ኤርትራም ፈረሰች ቀረች ውጣ ውረዱን አልፎ የድል አክሊሉን መድፋቱ አይቀርም።

በግለሰቡ ሰው የነጻነት መረጋገጥ የሚገኝ መሰባሰብ ለእውነተኛ ፈደራላዊ መስተዳደር መገኘት መሰረት ነው። 
በቋንቋና በሰፈራ ላይ የተመሰረተ አገዛዘ የግለሰቡ ሰው እስር(ክልል)ቤት ነው  የእልቂት ሂደት። 
ምርጫችን ግልፅ ነው 

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑርልን!!! 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.