የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ አመታዊ የቦርድ ስብሰባ ተጀመረ

የመጪው አመት አዘጋጅ ከተማ በነገው እለት ይታወቃል

የኢትዮጵያውን ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ ቦርድ አመታዊ ስብሰባ በዛሬው እለት በቶሮንቶ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ፡፡

በዚህ ለሁለት ቀናት በሚደረገው ስብሰባ ላይ ከ31 ቡድኖች የተወጣጡ ተወካዮች የሚገኙ ሲሆን፤ ተወካዮቹ ከአርብ እለት ጀምሮ ወደ ቶሮንቶ ገብተዋል፡፡

በሁለት ቀናቱ ጉባኤ ላይ፤ የ2008 አመታዊ የስፖርትና ባህል ዝግጅት አስተናጋጅ ከተማ የሚታወቅ ሲሆን፤ ቶሮንቶ የአስተናጋጅነቱን ከተማ ለመውሰድ ሲቀሰቅስ ከርሟል፡፡

ስብሰባው በቅዳሜ እለት ከተከፈተ በኋላ፤ የቦርዱ አባላት ቶሮንቶ በእጩነት ያቀረበውን ስቴዲየምና የመዝጊያ ዝግጅት አዳራሽ ጎብኝተዋል፡፡

የቶሮንቶ የንግድ ድርጅቶችና ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ለቦርዱ አባላት የምሳ ግብዣ አድርገውላቸዋል፡፡

ስብሰባው እሁድ እለት ይጠናቀቃል፡፡

Toronto - satenaw News 1

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.