ለዓረና የቀረበ ከባድ ህዝባዊ ጥያቄ (ረሃቡን በተመለከተ) – አምዶም ገብረስላሴ

=*=*=*=*=*=*=*=*
በኣሁኑ ሰዓት ዓረና ትግራይ ንዲሞክራስን ሉኣላውነትን ፓርቲ ከባድ ህዝባዊ ጥያቄ ቀርቦለታል። ጥያቄው የቀረበው ከሁሉም የትግራይ ዞኖች፣ ከ23 ወረዳዎችና ከ205 በላይ ቀበሌዎች ኑዋሪ ህዝብ ነው። ጥያቄው “እዚሁ ቀዮዋችን ተቀምጠን በረሃብ ከምንሞት የምንሰደድበትና ሂወታችን የምናተርፍበት ቦታ ኣመቻቹልን። ኣገር ቤት የስደተኞች መጠልያ(ካምፕ) ማዘጋጀት የምትችሉ ከሆነ ኣስተባብሩልን። የማትችሉ ከሆነ ደግሞ ወደ ጎረቤት ኣገሮች ምሩንና የዓለም ማህበረሰብ ረሃባችን፣ ችግራችን ኣይቶ ሂወታችን እንዲታደገን የምትችሉት ጥረት ኣድርጉልን። ከናንተ ሌላ የሚሰማን የለምና ኣብየቱታችን ሰምታቹ መፍትሄ ኣበጁልን” እየተባልን ነው።

ይህ ከባድ ህዝባዊ የሂወት ኣድን ጥያቄ በተደጋጋሚ እየቀረበልን ነው። ህዝቡ በህወሓት መንግስት የነበረው የተመናመነው እምነት ጨርሶ እንዲጠፋ ኣድርጎታል።

እስቲ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን…… ! ይህ ህዝባዊ ጥያቄ ዓረና እንዴት ማስተናገድ እንዳለበት ሃሳባቹ ኣካፍሉት?

ህወሓት እንደሆነች “በድርቅ የተጠቃው ህዝብ 270 ሺ ብቻ ነው” ብላ ለፌደራል መንግስት ሪፖርት ኣቅርባ ነበር፣ ትንሽ ቆይታ “410 ሺ ህዝብ ብቻ ነው” ኣለች፣ ትንሽ ቆይታ “1 ሚልዮን ብቻ” ኣለች፣ ኣሁን 2.5 ሚልዮን ህዝብ ( 23 ወረዳዎች ኑዋሪዎች) በድርቅ ተጠቅተዋል። ለዚህ ህዝብ የመጣው የእርዳታ ብር 200 ሚልዮን ብቻ እንደሆነ የትግራይ ግብርና ቢሮ መግለፁ የሚታወቅ ነው። በዛ ላይ የመጣው እህል ” የመጋዘን ጠበበ፣ ለኣባይ ግድብ” ወዘተ እየተባለ መዘረፉ ይታወቃል።

ከዚህ ያመለጠው እህል ደግሞ “ኣንድ በሬ ያለው፣ የዓረና ኣባል ወይም ደጋፊ የሆነ፣ የመዳበርያና የደደቢት እዳ ያለበት፣ ልጁ የመንግስት ሰራተኛ ያለውና የሚረዳ ደህና ቤተሰብ ያለው ሰው እርዳታ ኣይመለከተውም” ተብሎ ተፈርዶበታል።

የተቀረው ህዝብ ” የድሃ ድሃ( በተኽ)” የሚባለው ሰውም ራስ በራሱ እያጣሉ “እኔ እብስ( ኣነ ገድድ) እያልክ ተጠቋቁመህ ውሰድ” የሚል ሰይጣናዊ መመርያ በህወሓት መንግስት ወጥቶበታል።

BBC በከትናንት በስትያ UN ዋቢ ኣድርጎ እንደዘገበው “15 ሚልዮን ህዝብ ተርበዋል፣ በቀን 2 ህፃናት እየሞቱ እንዳሉ” ይፋ ኣድርጓል።

ለነገሩ ህወሓት ፈሪሃ እግዜር ሳይሆን ፈሪሃ ፈረንጅ ስላለው ነው እንጂ እኛም ከመስከረም ወር ጀምረን እየሞተ ያለው የሰው ሂወት ነግረነው ነበር።
መንግስት የሞት ሪፖርቱ ከየ ቀበሌው የደረሰው ሲሆን ኣቶ ኣባይ ወልዱ ኣፅቢ ወንበርታ ሂዶው በረሃብ የሞቱት ሴትዮ ኣረጋግጡው ተመልሰዋል።

የእንስሳት ሞት፣ የህፃናት ትምህርት ማቋረጥ፣ ተረጋግቶ የነበረው የወጣቶች ስደት እንዳዲስ ማገርሸት፣ የወረርሽኝ በሽታ ምልክቶች መታየት ወዘተ በጉብኝታቸው ወቅት ለኣቶ ኣባይ ወልዱ ተነገራቸው። በቂ እርዳታ ግን ሊያቀርቡ ኣልቻሉም።

ይህ ለዓረና እየቀረበ ያለው ከባድ ህዝባዊ ጥያቄ በትግራይ ክልል ብቻ ኣይደለም። ከኣጎራባች የኣማራ ክልል ዞኖችም ጭምር ነው። ባለፈው ሳምንት የኣማራ ክልል ርእስ መስተዳድር በራያ ቆቦ ዞን በጎበኙበት ወቅት ህዝቡ ኣስቸኳይ የእልና ውሃ እርዳታ የጠየቀ ቢሆንም ከአቶ ደጉ የቀረበ መልስ “እርዳታ ምንም ኣይጠቅመንም” የሚል ነበር።

የዋግህምራና ሰሜን ጎንደር ህዝብም በቂ እርዳታ ያልቀረበለት ከመሆኑ በተጨማሪ “ስደት ከሄድክ መሬትህ ትነጠቃለህ” የሚል ትእዛዝ በማውረድ “ቤትህ ሁነህ ሙት” የሚል ሃላፊነት የጎደለው ትእዛዝ ኣውርደውበታል። ስለዚ እነኚህ ህዝቦች እስካሁን መንግስት ድርቅ ለመከላከል በወሰደው እርምጃና እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ ደስተኞች ካለመሆናቸው በተጨማሪ እምነት ኣጥተውበታል።

ዓረና ለዚህ ከባድ ህዝባዊ ጥያቄ እንዴት ያስተናግደው?

ዓረና ህዝቡ ከቤቱ ሳይፈናቀል የሚረዳበት መንገዶች ያላቸው የራሱ ኣማራጭ ሃሳቦች ኣስቀምጠዋል። የናንተ ሃሳቦች ግብኣት እንዲሆኑት ይፈልጋልና ሃሳባቹ ለግሱልን።
ህፃናት በረሃብ እየሞቱ እንደሆኑ BBCና UN እየገለፁ ነው። ዘገባው ከማስተባበል ይልቅ የሂወት ኣድን ስራ እንስራ።

ህዝብና ንዓንግል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO……!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.