በወገኔ ላይ አልተኩስም ያሉ ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እያቃጠሉ ሕዝቡን እየተቀላቀሉት ነው ተባለ

በኦሮሚያ እና በ150 የኦሮሚያ ከተሞች የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣን ለማብረድ መንግስት ወታደሮቹን አሰማርቶ ትናንት ብቻ በም ዕራብ ሸዋ እና በደቡብ ም ዕራብ ሸዋ 25 ሰዎችን መግደሉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ሕዝቤ አልተኩስም ያሉ ሕወሓት የሚያዘው መከላከያ ሚ/ር ወታደሮች በየቦታው ዩኒፎርማቸውን በአደባባይ በማቃጠል ሕዝቡን እየተቀላቀሉ ነው::

በኦሮሚያ የተነሳው ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ በም ዕራብ ሸዋ ባኮ እንዲሁም በም ዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ በወራ ጅሩ; አቹማ ጎሪ እና ጊዳ ከተሞች ተቃውሞ ሲሰማ ውሏል;; ቡራዩ ከተማ የመለስተኛ ሁልተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወታደሮች እንዳይገቡ በድንጋይ መንግዱን አጥረውታል:

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.