የሰማያዊ አመራር ከመድረክ ጋር የጋራ ግብረ ኃይል እንዲኖር አሳሰቡ – የሚሊዮኖች ድምጽ

የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ “መድረክ እና ሰማያዊ በጋራ ግብረ ሀይል ትግሉን ይምሩ” ሲሉ ትግሉን የሚመራ የጋራ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም ትሪ አቅርበዋል። ድርጅቶቹ ከምን በላይ ለአገርና ለወገን መቆም እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ነገሰ፣ ከዚህ በኋላ የሚደረገው የጋራ ሥራ መቀልበስ እንደሌለበት አሳስበዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በመከር ደረጃ ከመድረካና ሌሎች ጋር ለመስራት መወሰኑ መዘገቡ ይታወሳል። ፓርቲው በቅር ጊዜ ዉስጥ ከመድረክ አመራሮች ጋር የሚነጋገር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ነገሰ ሰማያዊ ፓርቲን ከመቀላቀላቸው በፊት የአንድነት ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ነበሩ።

አቶ ነገሰ የሚከተለውን ነው በፌስ ቡክ የለጠፉት ። የርሳቸውን አስተያየት የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደም ላይክ አደርገዉታል።

=============
መድረክ እና ሰማያዊ በጋራ ግብረ ሀይል ትግሉን ይምሩ!!!!!!!!!!!!!!!

አመራራቸው በቅድሚያ ለሀገርና ለወገን ይሆናል፡፡ ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታና እንዳይቀለበስ በመልክ በመልኩ ማደራጀትና መምራት ወሳኝ ነው፡፡ በአመራር ክፍተትና ስህተት ከተፈጠረ በፍጥነት ማስተማር፣ማስተካከልና መምከር ይቅደም፡፡

በመሪዎች ስህተት ህዝብ ህዝብን እንደበደለ አንቁጠር፣ በጋራ እንዳንቆም ማሳሳቻ ነው፡፡ህዝብ ህዝብን በድሎ አያውቅም፡፡ ሰላማዊ የንቅናቄ ታጋዮች በገዢዎች ሴራ አትጠመዱ፡፡

ለህዝባችን ታማኝ እንሁን፣ በትብብር መስራትና መደጋገፍ ብቸኛው ፖለቲካው መፍትሄ ነው፡፡
በድርድር ሰበብ ችግር እንዳይመጣ መጠንቀቅና ለተደራዳሪዎቹ የይዘት ስልትንና ገደብን /መወሰን/ማበጀት፡፡ ከተጀመረ ተስፋ መቁረጥ ስለሌለ ለህዝባችን ዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ በጋራ እንታገል፡፡
==============

Comments are closed.