የአሁኑ አፈጉባኤና የቀድሞው ጄኔራል የተከበሩ አቶ አባዱላ ቪላ ቤቶችና እልፍኝ ታዳራሾች

የአሁኑ አፈጉባኤና የቀድሞው ጄኔራል የተከበሩ አቶ አባዱላ እኔ የማውቃቸው ብቻ አራት ልብ የሚያርዱ ቪላ ቤቶችና እልፍኝ ታዳራሾች (Mansions) አሏቸው፡፡ አንዱ ቦሌ ወሎ ሰፈር ይገኛል፣ ሁለተኛው ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጀርባ ይገኛል (አሁን የሚኖሩትም እዚህ ነው)፣ ሦስተኛው ለገጣፎ ፣ አራተኛው ደግሞ አዳማ ላይ ያስገነቡት ቪላ ነው፡፡ የያንዳንዱ ቪላዎቻቸው ወቅታዊ አማካይ ዋጋ 15 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ በድምሩ 45 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ቤቶች ባለቤት ናቸው ማለት ነው፣ ባለመዶሻውና ሳቂታው አፈጉባኤያችን ቀላል ሰው እንዳይመስሏችሁ፡፡ መዶሻ ይዘው የሚስቁትም ያለምክንያት አይደለም፡፡

ቀደም ብዬ የጠቀስኩት አሐዝ የአዳማውን ቪላ አይጨምርም፡፡ ከዓመታት በፊት ‹‹ይህን ቪላ ይዤ ለትግል አይመቸኝም››
ብለው ለኦሕዴድ በስጦታ አስረክበውት የነበረ ቢሆንም ኦሕዴድ ግን ‹‹ግዴለም ይያዙት፣ ባይሆን ሌላ ጊዜ…›› ብሎ
መልሶላቸዋል፡፡ የሚገርመው ከርሳቸው በተቃራኒ የሚቆሙት ሟቹ አቶ አለማየሁ አቶምሳ አንድም ቤት በስማቸው አልነበራቸውም፡፡ የሥልጣን ዘመናቸውን ከፊንፊኔ ይልቅ ባንኮክ ነበር ያሳለፉት፡፡ የርሳቸውን ድንገተኛ ሞት ተከትሎም ቤተሰባቸው ለመበተን ተቃርቦ የነበረ ሲሆን በየካ ክፍለከተማ የኦህዴድ አባላት የማግባባት ሥራ ሠርተው አንድ የኪራይ ቤት በዚሁ ክፍለከተማ ተፈልጎ እንዲሰጣቸው ሆኗል፡፡

(ዋዜማ ራዲዮ)

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.