ዓረና-ምድረክ ውክሎ በሸራሮ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበው ሃለቃ ገብረሃወርያ ኣርኣያ የሁለት ዓምት ፅኑ እስራት ተበየነበት

አንዶም ገብረስላሴ

ሃለቃ ገብረሃወርያ ኣርኣያ
ሃለቃ ገብረሃወርያ ኣርኣያ

ዓረና-ምድረክ ውክሎ በሸራሮ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበው ሃለቃ ገብረሃወርያ ኣርኣያ ከስኔ 10/10/2007 ዓ/ም በሸራሮ ከተማ ፀጥታ ሃይሎች ታፍኖ ባልታወቀ ቦታ ኣስረው በማቆየት በ14/12/2007 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሁለት ዓምት ፅኑ እስራት ተበይኖ በታል።

ሃለቃ ገብረሃወርያ መጀመረያ የሸራሮ ከተማ ኣስተዳዳሪዎች ጠርተው “መድረክ የምርጫው ውጤት ኣልቀበልም ብለዋልና ያንተ ኣቋም ምንድነው” ብለው የጠየቁት ሲሆን እሱም “መድረክ የወሰደው ኣቋም እኔም እጋራዋለው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህ መልሱ የተናደዱት የወረዳዋ ኣስተዳዳሪዎች “በሃይል ንብረት ነጥቆ መጠቀም” ክስ ቀይረው፣ የውሸት ምስክሮች ኣስመስክረው ኣሳስረውታል።

ሃለቃ ገብረሃወርያ ለወራት የታሰረበት ቦታ እንዳይታወቅና ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት ያደረጉት ሲሆን ሰሞኑ ዓብይ ዓዲ ማረምያ ቤት በጥየቃ ሊገኝ ችለዋል።

የትግራይ እስር ቤቶች በዓረና መድረክ ኣባላትና ደጋፊ ተብለው የተጠረጠሩ ዜጎች እየተሞሉ ነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.