ለቀጣፊው ጌታቸው ረዳ -አዴው(አድ አዳማ) ከኖርወይ

getachew_reda1-satenaw
ቀጣፊው ጌታቸው ረዳ

በኦሮሚያ ዉስጥ የተነሳዉን ህዝባዊ ተቋውሞ አስመልክቶ በህዝብ ደም መፍሰስና በህዝብ ስቃይ ተደሳቹ የህወሃት ሚኒስተር ለጋዜጠኞች ሲተርኩ ተደመጡ እኔ ደሞ የታዘብኩትን ልጽፍ ወደድኩ።

ክቡር ሚኒስተር ጌታቸው ረዳ ክቡር አልኩ መሰለኝ መቼም ሚኒስተር ከሚለዉ ፊት ክቡር ስለማይቀር ብይዬ ነዉ።የሆነው ሆኖ ብዥታ ብዥታ እያሉ ደጋግመዉ ሲለፈልፉ ተሰምተዋል በርግጥም ብዥታዉ ማደናገሪያ እንጂ ሃቅ አለመሆኑን መላዉ ህዝብም ሆነ እርሶም በደንብ ያዉቁታል። ይልቁንም ብዥታዉ እርሶ ጋር ስለሆነ በግፍ ስካር የተሞላዉ ንግግሮት ፕሬስ ኮንፈረንሱን በብዥታ አጠናቆታል።

አዎ የተቀናጀዉ ማስተር ፕላን ይቅርታ የተቀናጀዉ ማስተር ጥፋት ማለቴ ነዉ ላይ ህዝቡን ማወያየት በመዘግየቱ በህዝቡ ዘንድ ብዥታን ፈጥሯል ሲሉ ተደምጠዋል። ኧረ እንደዉ ለመሆኑ ምን ያህል እንደዘገዩ ታውቆታል ? የለም የለም በፍጹም አያቁትም ምክያቱም ይህ ጉዳይ ከአመት በፊት ተነስቶ የበርካታ ዉድ የኦሮሞ ልጆች ህይወት ከቀጠፈ በሗላ በአንድ የከተሞች ስብሰባ ላይ “አሁን ህዝቡ ተወያይቶበታል ይህን ማስተር ጥፋት ማንም አያቆመዉም ለማቆም የሚቃወምም ካለ ልክ እናስገባዋለን ” የሚል የትምክህት ንግግር ተደምጡዋል። ማን እንደማይሉኝ እርግጠኛ ነኝ ምክያቱም የእርሶ የተንኮል አባት የሆኑት ፋሺስቱ አቶ አባይ ጸሃዬ ናቸዉና ! አዎ በእርግጥም ግጥም አድርገዉ ያውቁታል።

ታዲያ እንደ ፋሺስቱ አባባል ህዝቡ ተወያይቶ ከሆነ ከየት አምጥተዉ ነው እርሶ ማወያየቱ ዘግይትዋል ያሉት? ይህ ብዥታ አንድ ይባላል። ወግ አይቀርምና አቶ ኃ /ማርያም ደሳለኝም ታዘዉም ቢሆን ዘግይተናል ብለዉ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ትንሽ ዘግየት አላችሁና ደሞ ጭራሹኑ ማስተር ጥፋቱ በ 2006 ተዘግቷል አላችሁ, ይህን ደሞ ብዥታ ሁለት በሉልኝ።እረ እርሶ ምን ያልቅቦታል እንደገና ደሞ ያለእፍረት የማወያየቱ ስራ የዘገየው የማስተር ጥፋቱ ጉዳይ በጣም ረቂቅ ስለሆነ ነው አሉ , ይህን ደሞ ብዥታ ሶስት በሉልኝ። በጠቅላላዉ ለህዝብ የሰጣችሁት መግለጫ በግልጽ እርስ ብእርሱ የሚጋጭ አይደለምን ?እዉነት ለመናገር መቼም ይሄ ጠፍቷችሁ አይደለም አናንተ በንጹሃን ደም የምትቀልዱና የፋሺስት ምግባር ያላችሁ ስብስቦች መሆናችሁን ያረጋግጣል።

ሌላዉ ደግሞ ለእዚህ ህዝባዊ አመጽ እጃቸዉ ያለበትን ስም ዝርዝር መጥቀስ አልፈልግም ብለዋል ! አውነት ነው በጣም ያስፋራል ምክንያቱም የህዝብን ሕገመንግስታዊ መብት ረግጠዉ ሕዝብን ለአምጽ ያበቁትና ያባባሱት የሕውሀትና የኢሐድግ ቅጥረኞች በመሆናቸው ሕወሐትን ማሳጣት ይሆንቦታል። የሗላ ሗላ ግን ንጹ ዜጎችንና በሰላም የሚቁዋሙ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በማሰር ተጠመዳቹ እንግዲህ በነኚህ ግለሰቦች ዙሪያ የተሰራ ያልተዋጣለት ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ብቅ እንደሚል እርግጠኛ ነኝ። ሌላው ደሞ ሳያስቡት በምርቃና አንድ እውነት ተናግረዋል ይኸዉም አሁን ጥቄው የማስተር ጥፋቱ አይደለም ተቀይሯል አሉ።እርግጥ ነው ጥያቄው ከማስተር ጥፋቱ ይቁም ወደ መንግስት ይቀየርልን ድብን አድርጎ ተቀይሯል።

ምን ሆነ መሰለህ ተማሪዎች ማስተር ጥፋቱ የኦሮሞ ህዝብን ይጎዳል ብልው ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ እናንተ ደሞ አጋዚን አሰልፋቹ የኦሮሞ ተማሪን መግደል ጀመራችሁ ይሄኔ ተማሪው አትግደሉን ቤተሰብ ደሞ ልጆቻችንን አትግደሉ በማለት ጥያቄዉን አሳድገዉ በህብረት ገበሬዉን ጨምረው ሰልፍ ወጡ። እናንተ ምን ገዷችሁ 100% መረጠን ያላችሁትን የኦሮሞ ህዝብ በአደባባይ ረፈረፋችሁት ይሄኔ ታዲያ ህዝቡ በአንድ ድምጽ በዱርዬ መንግስ አንተዳደርም በቃን በማለት ጥያቄዉን ከማስተር ጥፋት ይቁም ወደ መንግስት ይቀየርልን አሳድጎታል። አቶ አያልቅበት ረዳ ሌላው የሚገርመው ነገር ደሞ በተደጋጋሚ ከተለያዩ ሚዲያዎች ስንት ሰው ሞተ ለሚለው ጥያቄ የእርሶ መልስ የነበረው የቁጥር እንካ ሰላምታ ውስጥ አንግባ እሱ ትርጉም የለዉም በማለት ደጋግመው ተናግረዋ።

እውነት ነው , 1 ኛ 10 ሰው ሞተ ወይም 10 ሺ የሚሞተው ኦሮሞ እስከሆነ ለእርሶ በፍጹም ትርጉም የለውም , 2 ኛ ገዳዮቹ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ የፌደራልና የአጋዚ ወታደሮች ቁጥርን ከ 5 በላይ መጥራ የማችሉ ስንት ገደላቹ ሲባሉ 5 እስከስንት ተማራቹ እስከ 5 እያኡ የሚመልሱትን እርሶም እንደብዥታ መፍጠሪያ ስንት ሰው ሞተ ሲባል 5 እያሉ ሲመልሱ ከቆዩ በሗላ የፈለግነውን ያህል ብንገል ማን ያገባዋል በማለት አሁን የቁጥር እንካ ሰላምታውስጥ መግባት አያስፈልግም ሲሉ መልሰዋል። ሌላኛው ሀቅ ደሞ ወያኔ ከጫካ ጀምሮ ሬሳ ለቅሞ የመደበቅ የካበተ ልምድ ስላላት የሟቾችን ቁጥር አሳምረው ያውቁታል ስለዚህ ባለዎት ዳታ መሰረት የሟቾችን ቁጥር በጊዜ እውነቱን ቢናገሩ ይሻላል እላለሁ አቶ ቀጣፊው ረዳ። ለምን ቀጣፊ እንዳልኮት በደንብ ያቃሉ ብዬ አስባለሁ ለነገሩ ሀቅ ተናግሮ የማያቅ ሰው ይሄ እንዴት ይጠፋዋል። የቅጥፈት ነገር ሲነሳ እስቲ አንድ የቀጠፉትን ነገር ላንሳ እንደው ማን ያምነኛል ብለው ነው አመጹን ያነሳዉን ሕዝብ መኪና እያስቆሙ በመኪና አምስት አምስት መቶ ብር ያስከፍሉ ነበር ብለው የወነጀሉት።

የኦሮሞ ሕዝብ እኮ በናንተ የተቀመጡት አሻንጉሊቶች ከነፖሊሶቻቸው ሲሸሹ በምትካቸው የሀገ ሽማግሌዎች መርጠው ለአንድም ቀን ቢሆን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደደር ምን እንደሚመስል በሚገባ ያሳያችሁ ሕዝብ ነው ። እውነት ነው እውነት ነው እናንተን ጨርቃችሁን ጥሎ ያሳበዳችሁ ነገር ቢኖር ወያኔ በግፍ ያካበተችው ሀብት ላይ ያንዣበበው አደጋ ነው ለምሳሌ በክፋታቸው ሰይጣን የሚቀናባቸው የናንተም ተንኮል አስተማሪ የሆኑት በአቶ መለስ ዜናዊ ስም በየቦታው ዘርፋችሁ የሰየማችሁት ፓርክ መቃጠሉ ነው። ይህ ደሞ የግፍ ንብረት ስለሆነ መላ ሕዝቡን እሰየው ያሰኘ ነው ።

ይልቁኑ አቶ መለስ ዜናዊ በስማቸው የቆመ ፓርክ ነው የተቃጠለው ነገር ግን ይህ ግፍ ያስመረረው ህዝብ አንተን ቢያገኝህ ምንህን ሊያቃጥልህ እንደሚችል አንተው እራስህ ገምት። በመጨረሻም በመደጋገም ጋንኤልን የጠራ የጠርራውን ጋንኤል ስለመቆጣጠሩ እርግጠኛ አይደለም። የተጠሩት አጋጋንት ከጠራቸው ጠንቁዋይ አቅም በላይ ስለሆኑ እያሉ ያለ እረፍት ለጋዘጠኞች ስለጋኔልና ስለ ጠንቁዋይ ባህሪ በእርግጠኝነት ሲናገሩ ምን ያህል ከጠንቁዋይና ከጋኔል ጋር አብሮ እየሰሩ እንዳለ ያሳያል። ይህ ደሞ የማትክዱት ሀቅ ነው ምክንያቱም ቦንብ ህጻናት ላይ መወርወር , እናት እባካቹ ልጄን አትግደሉብኝ ብላ እየለመነች እሷንም ልጇንም አንድላይ መግደል , አዛውንቶችን መግደል, እርጉዝን ገድሎ መጣል , እህቶችን አስገድዶ ደፍሮ መግደል ወዘተ የአጋንት ወይም የሰይጣን ባህሪ ነው።

እንደሚታወቀው ይህን ድርጊት የፈጸሙት ደሞ ፌደራልና አጋዚ የተባሉት አጋንንቶች ናቸው። የነዚህ አጋንንት አሰልጣኝ ደሞ እርሶና እርሶን መሰል የሕወሐት ባለስልጣናት ናቸው። ስለዚህ የአብዬን ወደ እምዬ የሚለውን ተውትና በኦሮሞ ህዝብም ይሁን በመላው የኢትዮዽያ ህዝብ እርሶ የአጋጋንቶች ቁንጮ ነው የሚባሉት። ማስተር ጥፋቱ ቆሟል የሚባለው የማደናገሪያ ሀሳባችሁ ላይ ደሞ ሰሞኑን እመለስበታለሁ!!!!!!

አዴው(አድ አዳማ) ከኖርወይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.