ከይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኣሰጣጥ ጋር በተያያዘ በኣዲስ ኣበባ ከፍተኛ ተቃውሞ ይነሳል የሚል ስጋት ኣይሏል

የኦሮሞ ገበሬዎችን ለማፈናቀል ሲነሳ በተቃውሞ ምክንያት መግቢያ መውጫ ያጣው የሕወሓት ኣገዛዝ ፊቱን በማዞር የኣዲስ ኣበባ ነባር ነዋሪዎችን ኣፈናቅሎ በምትካቸው በሕወሓት ስር ያሉትን የኣንድ ብሄር ትግሬ ካድሬዎችና ዘመድ ኣዝማዶችን ለመተካት እና በኢኮኖሚ የበላይነት ሌላውን በማደህየት ረግጦ ለመግዛት ያሰበው ሃሳብ በከፍተኛ ደረጃ የሕዝብ ተቃውሞ ይነሳል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ጽፈዋል።የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለማግኘት በሚሊዮን ብሮች አየተጠየቁ መክፈል ስለማይችሉ በዝምታ የተለጎሙ በድህነት የተመቱት የኣዲስ ኣበባ ነዋሪዎች ከየመኖሪያቸው በካርታ ሰበብ እየተባረሩ ንብረቶቻቸው ሊወረስ መሆኑ ታውቋል።

ሰሞኑን የይዞታ ማረጋጋጫ ካርታ እየተሰጠ ነው፣ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች፣ ግን የሊዚ ዋጋ የሚቀመስ አይደለም፣ እንኳን ለመክፈል ለማሰበም ይከብዳል ለአነድ ካሬ ሜትር 3600 ብር ወጋ ተቆርጦለት ህዝቡን በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከቶታል፣ ምን አልባትም በኦሮሚያ የተፈጠረው ነገር እዚም ሊቀሰቀስ ይችላል።

3600 የተወሰነው ኮተቤ አካባቢ ነው፣ ለምሳሌ አንድ ባለ ግቢ 471 ነው፣ 75 ካሬውን ይፈቅድልቸዋለ መንግስት ሌላውን በሊዝ ያስበዋል፣ ስለዚ ከአንድ ባለጊቢ መንያህል ይጠበቃል 1446000 ብር ለመንግስ ገቢ ማድረግ፣አለበት አብዛኛው የኮተቤ አካባቢ ሰው እንደዚ ነው የመጣበት፣ ማናችንም መክፈል አንችልብለዋል መንግስትም በግዴታ እተገብረዋለሁ እያለ ነው፣ ሰውም ሞተን እንጂ አይናችን እያየ ለአመታት የለፈንበትን ይዞታ በትነን አንቀርም በሚል ለአመፅ እየተዘጋጀ ይገኛል፣ ያው ለሞሞትም ማለት ነው።

በነገራችን 3600 በኮተቤ አካባቢ ነው፣ ያውም ዝቅተኛ ተብሎ በሌላው አካባቢ ደግሞ ከዚ የበሰ ነው፣ ጭራሽ የሚመሩትን ህዝብ አያውቁትም ከ500000 አስከ 2000000 ብር እንደ ቀልድ ክፈል ሲሉት፣ እንኳን በአይናችው፣ በህልማችው አስበት አያቁም ከኮተቤ ጀምሮ ካራ ነው፣ አብዛኛው ማህበረሰብ በዝቅተኛ ንሮ ውስጥ ያለ ነው፣ ገጠር የነበረን አካባቢን ለፍቶ ጥሮ ወደ ከተማነት የቀየረ ጠንካራና ሰራተኛ የሆነ ህዝብ ነው፣ ለዘመናት የለፋበትን ንብረት ነው ከከፈልክ ክፋል ካልቻል ዞር በል እየተባለ ያለው፣ ህዝቡ ደግሞ መጀመሪያ እኛን ገድላችሁ ነው ንብረቴን የምትወስዱት ብሎ ለከፍተኛ አመፅ እየተዘጋጀ ነው፣ ከፍተኛ የሆነ ደም አፋሳሽ ነገር ነው አሁን ሊፈጠር የሚችለው

(Yonas Tekelea)

Yonas Tekelea's photo.
Yonas Tekelea's photo.
Yonas Tekelea's photo.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.