የታላላቅ ብሔራዊ ጀግኖቻቸንን ሥራ በጋራ እንዘክር! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ማስታወቂያ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በዘንድሮው ዓመት ሁለት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጀግኖችን ለመዘከር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል። እኒህ ሁለቱ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ፦

የዘመናችን ታላቁ ኢትዮጵያዊ አርበኛ እና ሠማዕት

54f0ee23-7d0c-4c99-896f-50393fa27742

የዘመናዊት ኢትዮጵያ ምሥረታ ፋናወጊ

ccbddced-0c57-406c-b0bd-cc371283e37f

የመታሠቢያ ዝግጅቶቹ በሚከተሉት ከተሞች በከፍተኛ ድምቀት ይከበራሉ።

1      የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ መታሠቢያ፦ በአትላንታ ከተማ፣ ጆርጂያ ክፍለ ግዛት፣ ዩ.ኤስ.ኤ.፤

2      የፕሮፌሰር አሥራት ወልደዬስ መታሠቢያ፦ በለንደን ከተማ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አውሮፓ።

ከዚህ በተጨማሪ አቅም እና ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን፣ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበራት ባሉባቸው በየትኞቹም ከተሞች እና አካባቢዎች በዓሎቹ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስበው ይውላሉ።

ማሣሠቢያ

  • ለእነዚህ ዝግጅቶች አከባበር የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ለማድረግ ዝግጁ የሆናችሁ አስተያየት እና ኃሣባችሁን በሚከተለው ኢሜይል ላኩልንmwaoipr@gmail.com
  • የመታሠቢያ ቀኖቹ መቼ እንደሚከበሩ ወደፊት በይፋ ይገለፃል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግኖች እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

 

Teddy-Asrat