ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛ ሆነ

nn1644የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ፡፡ አምባሳደር ብርሃነ አዲሱን ሹመት ከሁለት ሳምንት በፊት በማግኘታቸው፣ በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በመሆን ሥራቸውን መጀመራቸው ታውቋል፡፡ አምባሳደር ብርሃነ ለረጅም ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩ ሲሆን በዋናነት በአሜሪካ አምባሳደር፣ በአውሮፓ ኅብረትና በቤልጂየም አምባሳደር፣ ቀጥሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እስከዚህ ዓመት መጀመሪያ ድረስ ሠርተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አምባሳደር ብርሃነ በኢትዮጵያ ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዋቅር ወጥተው፣ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት መክተማቸው ታውቋል፡፡

ዜና – በጋዜጣው ሪፖርተር’

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

..............