ተስፋዬ ገብረአብና ወቅታዊ ውንብድናው! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

Tesfaye Gebreab
ተስፋዬ ገብረአብ


ዛሬ ጥር 25/2008ዓ.ም. “በእነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ንግግር አንድምታ ላይ የኦነግ እጅግ የሳሳተ ዕይታ!” የሚለውን ጽሑፍ በመጽሐ ገጼ (በፌስ ቡኬ) እንደለጠፍኩት አንድ የመጽሐፈ ገጽ ጓደኛዬ “ቦሩ በራቃን ታውቀዋለህ ወይ?” ብሎ ጠየቀኝ:: እንደማላውቀውና ሐሰተኛ ስም እንደሆነ እንደምገምት ነገርኩትና ያውቀው እንደሆነ ስጠይቀው “ተስፋዬ ገብረአብ ነው ከዓመት በፊት አጋልጨዋለሁ” አለኝ፡፡ እኔም እሱ እንደሆነ ገምቸ እንደነበርና ጽሑፉላይ አ ፊደልን መጻፍ ሲፈልግ ኣን በመጻፉና በአንዳንድ ሌሎች ነገሮች እሱ መሆኑን ገምቸ እንደነበር ገለጽኩለት፡፡

ባለፈው ጥር 4, 2008ዓ.ም. “ለኦነግና ኦነጋዊያን! የወያኔን ዓላማ አንግቦ ወያኔን ለመውጋት የእንተባበር ጥሪ አይሠራም!” በሚል ርእስ ለጻፍኩት ጽሑፍ ኢልማ ኦሮሞ (የኦሮሞ ልጅ) በሚል የብእር ስም በመጠቀምና “ይህንን ሐሳብህን የሚጋሩ እጅግ ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው እንደ ሌላው የወያኔ ሐሳብ ነው ብዬ መግፋት ያልፈለኩትና ለዚህ ጽሑፍህ መልስ መስጠት የፈለኩት” በማለት እራሱን ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ሰው የሆነ ባስመሰለ አቀራረብ መልስ ያለውን ሐሳብ “ትግሉን በአሸናፊነት ለመጨረስ መወሰድ የሚገባቸው ዋናዋና ነገሮች! ለሠዓሊ አምሳሉ ላወጡት ጽሑፍ መልስ” በሚል ርእስ የተሳከረ ነገር በመጻፍ መልስ የጻፈውም እሱ ነበር፡፡

ይህ የተሳከረና እንጭጭ አስተሳሰብ መጥራት ስለነበረበትም “ኦነግና ኦነጋዊያን ወያኔና ሌሎችም የጥፋት ኃይሎች ተፈጥሯዊ የተጠያቂነት ፖለቲካዊ ቁመና አላቸውን?” በሚል ርእስ መልስ ጻፍኩኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ለጻፍኳቸው ጽሑፎችም እየተከታተለ የሚመቸውን ነገር ብቻ እየመዘዘ በራሱ መንገድ እየተረጎመ የማይረባ ነገር እየደረተ የኦሮሞን ስም እየተጠቀመ የሸአቢያንና የኦነግን ጥቅም ለማስጠበቅ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ወገኖቻችን ኦነግና የኦነግ ደጋፊዎች ሆይ! እባካቹህ የሸአቢያ ዓላማና ፍላጎት ይግባቹህ፡፡ በየትኛውም መመዘኛ ቢታይ የሸአቢያ ዓላማና ፍላጎት እናንተን ተጠቃሚ ሊያደርግ አይችልምና እባካቹህ? መጠቀሚያ ከመሆን እራሳቹህን ጠብቁ? እኔ በእውነት ዓላማ አስተሳሰባቹህ በሀገርና በሕዝብ ህልውናና ደኅንነት ላይ ምን ያህል ከባድና አሳሳቢ አደጋ እንደጋረጠ መረዳት ሳትችሉ የጥፋት ኃይሎች መጠቀሚያ መሆናቹህ ስለሚያቆስለኝ ስለሚያበሳጨኝ እናንተን በተመለከቱ ጽሑፎቸ ተግሳጽና ዘለፋ አበዛለሁ እንጅ መሳደብ ፈልጌ ወይም ተሳዳቢ ስለሆንኩም አልነበረም የምገስጻቹህና የምዘልፋቹህ፡፡ በእውነት ስለእውነት ሌላው ሁሉ ቢቀር በእድሜ አረጋዊያን ናቹህና ልትሰደቡ የምትገቡም አልነበረም፡፡ እጅግ አድርጌም ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እንዲያው እባካቹህ? እባካቹህ? ኧረ ተው እባካቹህ? ተው? ተው? ተው?

የመጽሐፈ ገጽ ጓደኛየ ይህ ሰው ተስፋዬ ገብረአብ እንደሆነ እንዴት እንደደረሰበት ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በመመልከት ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡-

ቦሩ በራቃ ማን ነው?

ፊንፊኔ ትሪቡን በሚባል ድረ ገጽ ላይ የተጻፈውን “ከኣቶ ያሬድ ጥበቡ ኦሮምያን ለሁለት የመግመስ ነፍጠኛዊ ‘ጥበብ’ በስተጀርባ” የሚል ጽሁፍ ተከትሎ በተቀመጠው የኢሜል አድራሻ ላይ gulummaa75@gmail.com የሚል የቦሩ በራቃ የኢሜል አካውንት ተለጥፏል። ይህንን የኢሜል አድራሻ ፌስቡክ ላይ ገልብጣችሁ የኢሜል ባለቤቱን ስም ስትፈልጉ Galma Gulummaa የሚል የፈስቡክ ባለቤት ታገኛላችሁ። ፌስቡክ ምስጋና ይግባውና በኢሜል አድራሻ የተፈጠረን ስም ጎልጉሎ ያሳያል። በዚህ የኢሜል አድራሻ ተጠቅሞ የአካውንቱ ባለቤት How can I get a Tunisian visa? የሚል ጽሁፍ Trip Forums ድረገጽ ላይ እኤአ በ2010 አስመራ፥ ኤርትራ ሆኖ የጻፈውን ጽሁፍ ከታች እለጥፈዋለሁ።

ቦሩ በርቃ ባለፈው ሳምንት ጎንደር ውስጥ ስለሚገኙ የቅማንት ህዝቦች “የቅማንት ህዝብ ትግል በኦሮሞና በሌሎችም ነጻነት ናፋቂ ህዝቦች ሊደገፍ ይገባል” በሚል ርዕስ የኦሮሞ የዩኒቨርሲቱ ተማሪዎች የቅማንት ተማሪዎችን ትግል እንዲደግፉ ጽፏል። ይህንን ጽሁፍ ጃዋር መሀመድም ሸር አድርጎታል። ጀዋር መሀመድ ከዚህ በፊት አንድ አስመራ ለሚኖር ግለሰብም “መልዕክት በፌስቡክ ገጼ ጻፍልኝ” ብሎኛል ብሎ ስለሰውየው ጽፎ ለጥፎነት እንደነበር እናውቃለን። በተጨማሪም በተመሳሳይ የኢሜል አድራሻ ማለትም gulummaa75@gmail.com በሚለው ጂሜል አካውንት ያህያ ጀማል በሚል ሌላ ስም “ይድረስ በጀዋር መሃመድና በኦሮሞ ማንነት ላይ ለተነሳሳችሁ ወገኖች በሙሉ: ጀዋርን ለቀቅ ኣድርጉት” የሚል ጽሁፍ ጽፎ Madda Walaabuu Press በሚባል ድረ ገጽ ላይ ለጥፎት እናገኘዋለን።

ሁሉም ጽሁፎች አሁንም ድረስ በተጥቀሱት ድረ ገጾች ይገኛሉ። ስለቅማንቶች ከጻፈው ጽሁፍ ውስጥ ሁለት አንቀጾችን ቃል በቃል እንደሚከተለው አሰፍራለሁ፤

<<ቅማንቶች ለበርካታ ክፍለ ዘመናት በኣማራ ብሄር ተውጠው የኖሩ በመሆኑ፣ በኣብዛኛው ማነንታቸው ተመናምኖ ወደ መሞት ደረጃ ተቃርቦ እንደነበር የብሄረሰቡ ተወላጅ የሆኑ ምሁራን ይናገራሉ። ዛሬ እንደ ወሎዬው ኣማርኛ ተናጋሪ ኦሮሞ ሁሉ፣ ኣብዛኛው የቅማንት ተወላጅ ኣማርኛና ትግርኛ ተናጋሪ ከመሆኑ የተነሳ ጥቂት የማይባሉትም ራሳቸውን በኣማራነት የሚገልጹ ናቸው። እ.ኤ.ኣ. በ1994 በተደረገው የቤትና ህዝብ ቆጠራ መሰረት የቅማንት ህዝብ ኣጠቃላይ ብዛት ከ170,000 በላይ መሆኑ ተመዝግቦ ነበር። ቅማንትኛን መናገር የሚችሉት ደግሞ 1625 ኣንደሚደርሱ ተለይቶ ነበር።

ይሁን እንጂ ከ13 ኣመት በሁዋላ 2007 ላይ በተደረገው የቤትና ህዝብ ቆጠራ ወቅት በሚገርም መልኩ ቅማንት እንደ ቅማንትነቱ ሳይቆጠርና የህዝቡ ቁጥርም ሳይዘገብ ታልፏል። በዚህ ወቅት ቢያንስ ከ500,000 በላይ መሆን የሚችለው የቅማንት ህዝብ ቁጥር በኣማራነት ተውጦ የኣማራን ህዝብ ቁጥር ከፍ ኣደረገ። የቅማንት ብሄረሰብ ደሞ ብሄረሰባዊ ህልዉናው እንደገና ታፈነ። ይህም በብሄረሰቡ ተወላጅ ምሁራን ዘንድ ከፍተኛ ቅያሜና ቁጣ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። የወያኔ መንግስት የብሄር ማንነት ላይ የተመሰረተ የፌደራሊዝም ስርኣት ዘርግቻለሁ እያለ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ቅማንትን በቅማንትነቱ ማወቅ ኣልፈለገም። ዛሬም ቢሆን በጥቂቱም ቢሆን እንዲያውቅ ያስገደደው መንግስታዊ ሃላፊነት ተሰምቶት ሳይሆን የብሄረሰቡ ተወላጆች ያነሱት የመብት ጥያቄ ነው።>>

የጽሁፉ ማሳረጊያ አንቀጽ ደግሞ እንደ ወረደ እንደሚከተለው ይነበባል፤

<<የቅማንት ብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ በሁሉም የኣገሪቷ ነጻነት ናፋቂ ህዝቦች ዘንድ መደገፍ ያለበት ጥያቄ ነው።በተለይም የኦሮሞ ምሁራንና ብሄርተኞች በኣገሪቷ ባላቸው የብዙህነት ልክ ለቅማንት ህዝብ ያልተቆጠበ ድጋፍ የማድረግ ሃላፊነት ኣለባቸው። በኣገሪቷ ከፍተኛ የትምህርት ተቁዋማት የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ከቅማንት ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ዝምድና በማደስና መረጃ በመለዋወጥ የጋራ ትግላቸውን ማቀናጀት ጠቃሚ ነው።>>

እንግዲህ “ከኣቶ ያሬድ ጥበቡ ኦሮምያን ለሁለት የመግመስ ነፍጠኛዊ ‘ጥበብ’ በስተጀርባ” የሚለውም ሆነ “የቅማንት ህዝብ ትግል በኦሮሞና በሌሎችም ነጻነት ናፋቂ ህዝቦች ሊደገፍ ይገባል” የሚለው ጽሁፍ አላማቸውና መልዕክታቸው ለሁሉም ግልጽ ይመስለኛል።

በመጨረሻ ሶስቱም ጽሁፎች ላይ የተቀመጠውን የኢሜል አድራሻ፥ gulummaa75@gmail.com፥ ተጠቅማችሁ ከፍ ብሎ በየእንግሊዝኛ ተጽፎ በተቀመጠው የጉዞ አሳላጭ ድረ ገጽ ውስጥ ገብታችሁ ስትፈልጉ፡ የኢሜል አካውንቱን ተጠቅሞ How can I get a Tunisian visa? የሚል ጽሁፍ ኤርትራ ውስጥ ሆኖ ከታች ስሙ የሰፈረው ሰው እንደጻፈው የሚያሳይ ጽሁፍ እንዲህ ቀድቼ ሰጥፌዋለሁ፤

**************************************************************************************
How can I get a Tunisian visa?

YahyaAsmara2010-05-30 17:52

Dear Sir/Madam,

I am from Eritrea. There is no Tunisian embassy or consulate here in Eritrean capital, Asmara. I will have a trip to Tunis in next October to take part on the award cermony of UNESCO which will be held by African Developmental Bank headquarters. How can I get a Tunisian viza to fly from Asmara to Tunis? Please, give me general information how to travel to Tunis.

my email address is:

gulummaa75@gmail.com

kindly yours,

Yahya Jamal
**************************************************************************************
ከዚህ በመነሳት ስለቦሩ በራቃም ሆነ ስለያህያ ጀማል ማንነት መናገር የሚቻል ይመስለኛል፤ ከኤርትራ ተነስቶ ኢትዮጵያን እያደማ ያለ ማን እንደሆነ መገመት ስለማይከብድ። አበቃሁ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.