ሱዳን በኣቶ መለስ የተሰጣት መሬት ለመረከብ ሽርጉድ እያለች ትገኛለች -አንዶም ገብረስላሴ

ሱዳንና መሬታችን
***********

12744301_983839321707724_4548579024881089412_n

በ2002 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ወቅት ኣቶ ስዬ ኣብራሃ በኢትዮ_ሱዳን ድንበር ከ35_65 ኪ/ሜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ ቆዳ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተደራድረው እንደጨረሱ ኣጋልጠው ነበር።

በዚህ መሰረት እንደ መተማ ዮውሃንስ፣ ቋራ፣ ልጉዲና ሌሎች ለም መሬቶች ለሱዳን ሊሰጡ በሁለቱ መንግስታት ዝግጅት መጠናቀቁ እየተገለፀ ነው።

በወቅቱ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ሁለቱ መንግስታት ከ17 ግዜ በላይ በድብቅ እየተደራደሩ የነበሩ ሲሆን የዚህ ድንበር ውጤትም ሱዳን በሑመራ በኩል ከነበረው ባህረሰላም የሚባለው የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግፋት ልጉዲ በተባለው የድንበር ከተማ ኣድርገው በመትከል የሱዳን የድርድር ኮሚሽ ፅሕፈት ቤት ኣዲስ ህንፃ ገንብተዋል።

12742249_983839408374382_3752827038832033189_nየሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ለቀረበለት ገፀ በረከት ለመረከብ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣዲስ ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።

*መንግስት እነ ሃፀይ ዮውሃንስ ደማቸው ያፈሰሱበት፣ እነ ሃፀይ ቴድሮስ የተወለዱበት የኢትዮጵያ ሉኣላዊ መሬት ቆርሶ ለባእድ ኣገር መለገሱ ያቁም…!

*መንግስት ስለ በሁለቱ መንግስታት እየተካሄደ ያለው ድርድር ለህዝብ በይፋ ይግለፅ…!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO.

Amdom Gebreslasie

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.