ተመስገን ልጆቹና በእውቀቱ -ዳዊት ሰለሞን

Temesgen chጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖለቲካዊ ውሳኔ ለእስር ከመዳረጉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመጨረሻውን ምሳ ከበእውቀቱ ጋር ለመመገብ ቀጠሮ ይዟል ።
ቀጠሮው ሌሎችን እንደማያካትት ያወቀው በእውቄ ብቻውን ቢገኝም ተመስገን ግን ብቻውን አልነበረም ።ሁለቱን ልጆቹን ይዟቸው ነበር ።
” ዛሬ የመጨረሻው ቀኔ በመሆኑ ልጆቹ አብረውኝ እንዲሆኑ እፈልጋለሁ፣ነገ እንደሚያስሩኝ ከውስጥ መረጃ ደርሶኛል “በማለት የበእውቀቱን ግርታ ለማጥራት ተመስገን እንደነገረው በአዲሱ መፅሐፉ በእውቀቱ አትቷል ።
ተመስገን የሁለቱ ህፃናት ተፈጥሯዊ አባት ባይሆንም በአንድ የቆየ ማለዳ እናትና አባት ሲጨቃጨቁ ከተመለከተ በኋላ ለማስታረቅ ጣልቃ የገባው ጋዜጠኛው በተመለከተው ነገር መጨከን አልቻለም ።
ተመስገን በዚያ ወቅት ፍትህ ጋዜጣን ገበያ ውስጥ ለማቆየት ከፋይናንስ ፈተና ጭምር ትንቅንቅ ገጥሞ የነበረ ቢሆንም ልጆቹን ለማስተማርና በኑሮ ፈተና ሰላም ያጡትን ወላጆች ለማገዝ አላመነታም።
ወረት ሳይሆንበትም ከበእውቀቱ ጋር ምሳ እስከተመገበበት የመጨረሻው ቀን ድረስ ልጆቹን ከአጠገቡ አላራቃቸውም ።
እንደ ተመስገን ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነት የሚሰማቸውንና ለሌሎች መኖርን እንደ ዜግነት ግዴታ የሚመለከቱ አርአያዎችን በማሰር የስንቱን ቤት እንደፈቱ ቤቱ ይቁጠረው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.