‪በጎንደር‬ ከተማ የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላት በገፍ እየከዱ ነው

federal policeeeeee

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)፡ በጎንደር ከተማና አካባቢው የጦር ካምፕ መስርተውም ሆነ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ አገዛዙን ሲያገለግሉ የቆዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ከነትጥቃቸው በመሰወር ላይ ናቸው፡፡ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ30 በላይ ፌደራል ፖሊሶች ከነትጥቃቸው ስርዓቱን በመቃወም ከየካምፓቸውና በውሎ ጠፍተዋል፡፡

የህወሓት አገዛዝ ይህን የፌደራል ፖሊስ አባላት መክዳት ለማስቆም ተደርጎ የማይታወቀውን ጥቅማጥቅምና የማዕረግ እድገት ለመስጠት ቢወስንም ሰራዊቱ እንደበፊቱ በቀላሉ ተሸውዶ ሰጥ ለጥ ብሎ ወደ ሎሌነት ተግባሩ ሊመለስ አልቻለም፡፡ እንዴውም በተቃራኒው የሚጠፉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥር ከቀደመው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር አየናረ መጥቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.