የነፍጠኛ/ዓቀይታይ ስርዓት – አምዶም ገብረስላሴ

127በነ ‪#‎Abraha_Desta‬ ላይ የተመሰረተው የሽብር ክስ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ውሳኔ “በታችኛው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ልክ ነው። ተከሳሾች ነፃ ናቸው። ዓቃቤ ህግ የይግባኝ ጥያቄ ካለው ከውጭ ሁነው ይከታተሉ” የሚል ነው።

በዚህ መሰረትም ዳኛ ክእስር ይፈቱ የሚል ደብዳቤ ለቃሊቲ ማረምያ ቤት ሓላፊዎች ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ነፍጠኛው ማረምያ ቤት የፍርድቤቱ ትእዛዝ ሊያስፈፅሙ ኣልቻሉም።

ይሄው ነፍጠኛው የቃሊቲ ማረምያ ቤት ነፍጡን ተማምኖ “መስሚያዬ ድፍን ነው” ብሎ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳይቀበል ቀርቷል።
( ነፍጠኛ ወይም በትግርኛ ዓቀይታይ ማለት መሳርያ የታጠቀና መተዳደርያው በያዘው ጠበንጃ ያደረገ ሰው ሲሆን እንደ መንግስት ደግሞ ሁሉም ነገር በሃይልና በጠበመንጃ የሚያስፈፅም ስርዓት ማለት ነው።)

ኢህኣዴግ በነፍጥ ወደ ስልጣን እንደ መምጣቱ የህግ የበላይነት ሳይሆን የነፍጥ የበላይነት ኣንግሰዋል።

ነፍጠኛው ማረምያ ቤት የእኩያው ፍርድ ቤት መብት ደፍጥጦ ሃገራችን የህግ ልዕልና ሳይሆን የነፍጠኛ/ዓቀይታይ ስርዓት ልዕልና ያረጋገጠች ኢ_ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መሆንዋ ኣረጋግጦልናል።

መቸስ እነ ኣብራሃ ደስታና ኣባል የሆኑባቸው ዓረናና የመሳሰሉት ድርጅቶች ሰላማውያን መሆናችን ይታወቃልና እንደነ ሓየሎም ኦፕሬሽን ሰርተን ኣናስወጣቸውም።

ከኛ የሚጠበቀው ጉዳዩ መፍትሄ የማያገኝ ከሆነ ታላላቅ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፎች ጠርተን ድምፃችን ከፍ ብሎ እንዲሰማ ማድረግና መንግስት እንዲፈታቸው ማስገደድ ነው።

ያው ዓቀይታይ / ነፍጠኛ ስርዓት ማሳየት የሚፈልገው የነፍጡ ሃያልነት እንጂ የፍርድ ቤቱ ፍትሃዊነት ኣይደለም።

ኢህኣዴግ … የራስህና መሳርያህ የሆነው ልማታዊ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንድታከበርና ፍትሃዊነት እንድትለማመድ እናሳስበሃለን።

በነገራችን ላይ ዛሬ የዋለው ችሎት ለዓርብ 11 / 05 / 2008 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዘዋል። ነፍጠኞቹ የቃሊቲ ሓላፊዎችም ፍርድ ቤት ድረስ መጥተው ትእዛዙ ለምን እንዳላስፈፀሙ እንዲያስረዱ ታዝዘዋል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.