ትኩስ ዜና!! የወያኔ የደህንነት መስሪ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሱዋል

Woyane 788-0 ሰሞኑን በተነሳው የኦሮሚያ ሰላማዊ ተቃውሞና ወያኔን እያርበደበደ ያለው በዘንባባ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከጀርባው ሌላ ሀይል እንዳለ ደርሸበታለሁ ይላል የደህንነት ከፍተኛ አመራር የሆኑት የነ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቁልፍ የመረጃ የስራ አመራር ልዩ ታማኝ የሕወሓት ሚስጥር ጠባቂ የበላይ ሹም፡፡

ከጀርባው ጥምር በጠብ መንጃ የታገዘ ሀይል ሙሉ ሀይሉን በመያዝ ጠቅልሎ በመግባት ነፃ ቀጠና ተቆጣጥሩዋል በሚል ደህንነት መስሪያቤቱ ተሸብሩዋል ፡፡ በመሆኑም ይህ እስከሚሆን ድረስ ምን እያደረግን ነበር በሚል እርስ በእርሳቸው በጎሪጥ እስከመተያየት ደርሰዋል፡፡ መተማመን ጠፍቷል ፡፡ አሁን እነ አቶ ስብሃት ነጋ ታማኝ ጀሌያቸውን በድብቅ እየጠሩ ልዩ ግንኙነት እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ሚስጥር በኦሕዴድ እና በብአዴን አመራሮች ላለማሳወቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ይሄም የተደረገበት ምክንያት ከጥምር ሀይሉ ጋር በቀጥታ እነዚህን ሁለት የንጀራ ልጅ ባለስልጣናትን ከአንድነት ሀይሉ ጋር ለማላተም ታቅዶ እንደሆነ ታማኝ ምንጮቻችን ሹክ ብለውናል፡፡

ታዲያ ወያኔዎቹ ነፃ ቀጠና ያሉዋት ነገር የሆነ ነገር ብታጭርብኝ እውነት ይሆን እንዴ ብዬ ወደ አየር አወጣኋላት፡፡ ተጨማሪ መረጃ ያለው ካለ ሹክ ቢለኝም አሪፍ ነውና ፡፡ ካለ ጉዳዩ በተከታታይ ከህዝብ ጆሮ እንዲደርስ ማድረግና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግሉን እንዲቀላቀለው ተገቢ ነው ባይ ነኝ፡፡