ጦሥ!! – አስገደ ገ/ ስላሴ

Woyaneበህወሓት ; በባኣዴን እና በኦሆዴድ መሪዎች ጦሥ በሠወሥቱ ክልሎች ህዝቦች ኣላሥፈላጊ ግድያ ግርፍያ እና ሥቃይ በጅምላ እሥራት እየተጎዳ ይገኛል

በእነዚህ ክልሎች እና በሌሎች ክልሎች ህዝቦች ኦጅግ በዙ ችግሮች እየተፈጠሩ ቢቆዩም በመላው የኦሮሞ ህ ህዝቦች የተነሣው የመሬት እና ሌሎች መብቶች ጥያቄ በተገቢ ኣገባብ እንደመመለሥ ፈንታ መልሣቸው እምቢ ላለ ሠው ጥይት ኣጉርሠው በመሆኑ እንሆ በመላው የኦሮሞ ክፍለሃገሮች ወይ ዞኖች ወረዳ ቀበሌ ጥያቄው ተቀጣጥሎ ዘግናኝ እርምጃ እየተወሠዱ እንመለከታለን ::
እነዚህ መሪዎች የዜጎችን ጥያቄ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንደመፍታት ፈንታ የህዝቦችን ጥያቄ በመናናቅ ንቅናቄው በጌታቸው ረዳ የመረቀነ ኣፍመፍቻ ኣነጋገር የኦሮሞ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ጥያቄ በመቋሸሽ ውንጀላቸው በመጠናከር የኣልቃይዳ : የኦነግ:: የኢህኣፓ: የሻኣብያ ዘመቻ ነው በማለት የሚሊዮኖች ህዝቦች ሥም ያጠፋሉ ::
በኣማራ ህዝብም የቅማንት እና ኣማራ ፈጽሞ በእኛ እድሜሥ ይቅ በኣያት ቀደምት ኣያቶች ተነሥቶና ተሠምቶ የማያውቀው እነዚ ፓርቲውች በፈጠሩት ጦሥ የኣማራና የቅማንት ህዝቦች ውሥጠ ጉዱ በመያቁት ወንድም ከወንድም ተላልቀዋል!!
የኣሁኑ ይባሥ ወልቃይት ጸገዴ : በኣማራ ዜጎቻችን የህወሓትና በኣዴን መሪዎ ች በፈጠሩት ጦሥ በወንድም ኣማቾች ወገኖች መፋጠጥን እንዲፈጠር ኣድርገዋል::ሌላ ቀርቶ የህወሓትና የበኣዴን ሥራ ኣሥፈጻሚ ኣማራሮች ከሠወሥት ቀን በፊት የህዝቦች ግርጭት እንፈታለን በለው በኣንድ የገንደር ሆቴል ተሠብሥበው ሣይሥማሙ ተጣልተው ተበታትነዋል ::
ይህ ተግባራቸው የሚያሣየው እነዚህ መሪዎች ምን ያህል
እንደወረዱና ያ ያልነበራቸው ህዝባውያን ነን እያሉ ይሸውዱን የነበረ መጋለጣቸውን ያረጋግጣል : :
ይህ ኣጀንዳ በሠፊው እቀጥልበት ኣለሁ

Asgede Gebreasilasie
2 mins ·

·

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.