‹‹አዲስ›› የደቡብ ትብብር ያስፈልጋል ?? – ግርማ በቀለ

unityትናንት አንድ ወዳጄ በሰጠኝ ቀጠሮ መሰረት ተገናኝተን ስለወቅቱ የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ መረጃ ከተለዋወጥንና ከተነጋገርን በኋላ ወደ ቀጠሮኣችን ጉዳይ አመራን፡፡ በጥቅሉ እንዲህ ሲል አስረዳኝ፡፡ ‹‹በወላይታ አንድ ልማድ አለ፤አንድ ህጻን/ልጅ ከልጅነት ‹‹ራሱን ወደ መቻል›› ሲሸጋገር ኮርማ ይታረዳል፣ዕለቱም ‹‹የኮራማ ቀን›› ይባላል፡፡ እናም ቀጠሮኣችን የ‹‹እኛ የኮርማ ቀን›› መቼ ነው? የሚለው ላይ እንድንነጋገር ነው አለኝ ፡፡ አብራራልኝ አልኩት፡፡ አብራራልኝና እንዲህ እንዲህ ኃሳብ ተለዋወጥን፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያለው ፖለቲካ ሲታይ የፖለቲካ ድርጅቶች መተባበርና ትግሉን ማስተባበር ግድ የሚል ነው፡፡ በተለይ ደግሞ 56 ብሄር/ብሄረሰቦች ( ከአገሪቱ 67%/ ሁለት ሦስተኛ እጅ በላይ) ያሉባት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጉዳይ ከዚህ ጋር በተያያዘ አስፈላጊነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ነው፡፡ ለክልሉ ህዝብ እንታገላለን ብለን የተነሳን ከዚህ በፊት ለትብብር ፋናወጊ/ደቡብ ኅብረትን በማስታወስ/ የነበርን ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ‹‹ራሳችንን ለመቻል›› ስላልተቻለን ዳግም ሞክረናል /ደቡብ አንድነትን በማስታወስ/፣ ይህም አልተሳካልንም፡፡ ህልም ተፈርቶ ሳተኛ አይታደርምና የአገራችን ፖለቲካ ዛሬ ከደረሰበት ደረጃ ላይ ሆነን ስንመለከት ይህ የግድ ነውና የትናንትናዎቹን እንደ ተሞክሮና መማሪያ መድረክ ተጠቅመን ‹‹አዲስ ›› የደቡብ ትብብር የጋራ ትግል መድረክ ስለመመስረት ለመምከር ነው አለኝ፡፡

ኃሳቡን ለማጠናከርም ትናንት የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ትግል በአገሪቱ ፖለቲካ የነበረውን ቦታ ዛሬ ካለበት እውነታ ጋር አነጻጽረን ተነጋገርን፣ በወቅቱ ያለው ፖለቲካ በሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች/ በገዢው ህወኃት፣ ‹‹የኮርማ ቀን›› እናክብር የሚል ጥያቄ እያነሱ ያሉ በሚመስሉት ኦህዴድ እና ብአዴን/ መካከል የተገደበና ‹‹ደኢህዴን››ን የጨዋታው ተመልካች ያደረገ ይመስላል የሚለውን አነሳን፣ …. ፣

ስለዚህ የደቡብ ኢትዮጵያ ትግል በአገራዊው ፖለቲካ መድረክ የሚገባውን ሥፍራ እንዲያገኝ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች መተባበር አለባቸው የሚለውን ተመለከትን፡፡ ይህ ለደቡብ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው አገራችን ፖለቲካ ያለውን ጥቅምም ደቡብን የ‹‹አዲስቱ ኢትዮጵያ›› ተምሳሌት በማድረግና የተቃውሞ ጎራው መሰባሰብ እርሾ በመሆን… ረገድ ያለውን አስተዋጽኦም አነሳን፡፡…

በአጠቃላይ ብዙ ካነሳንና ከጣልን በኋላ ኃሳቡ ላይ ተኝተን ለማደር፣በየመስመራችን ለመምከርና ሌላ ጊዜ ሌሎችን ጨምረን ለመነጋገር ተስማምተን ተለያየን፡፡>> በስምምነታችን መሰረት እኔም በአንዱ መስመሬ /ፌስቡክ ወዳጆቼ/ ለመምከር ሃሳቡን በጥያቄ ወደናንተ አመጣሁ፤ <<የልጁ/ህጻኑ መፀነስ- መወለድና ስለ‹‹ኮርማ ቀን›› ማሰብ ይጠቅመናል ?>> መቼም ጉዳዩ የሁላችን /የአገራችን/ በመሆኑ ባለድርሻ ናችሁና ምክራችሁን ለግሱን፡፡ መልካም የሳምንቱ መጨረሻ ብዬ ስለአስተያየታችሁ በቅድሚያ ባመሰግን በሙስና አይቆጠርብኝም፡፡ በቸር ያገናኘን፡፡ 12/06/08

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.