የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ ዶጋው የተባለ ቦታ ውስጥ ይንቀሳቀስ በነበረው እና ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ከፀረ-ሽምቅ እና ከሚሊሻ ጦር ተውጣጥቶ በልዩ ሁኔታ የተደራጀ የህወሓት ኃይል ላይ የካቲት 10 2008 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በጥምሩ የህወሓት ኃይል ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ ጠንካራ ምት አሳርፎ 35 ገድሎ 52 በማቁሰል እንዳልነበረ በማድረግ በታትኖታል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት

12744127_933381463425241_4804296239051805393_n

10565119_933381213425266_795884614089067920_n

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት

Comments are closed.