የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡

12743526_216378775381522_4220947580954263553_n

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)  የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ ዶጋው የተባለ ቦታ ውስጥ ይንቀሳቀስ በነበረው እና ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ከፀረ-ሽምቅ እና ከሚሊሻ ጦር ተውጣጥቶ በልዩ ሁኔታ የተደራጀ የህወሓት ኃይል ላይ የካቲት 10 2008 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በጥምሩ የህወሓት ኃይል ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ ጠንካራ ምት አሳርፎ 35 ገድሎ 52 በማቁሰል እንዳልነበረ በማድረግ በታትኖታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.