ዓምዶም ገብረስላሴ እና ኮካዎች!!! – ናትናኤል አስመላሽ

Amdom
ዓምዶም ገብረስላሴ

ዓምዶም ገብረስላሴ የዓረና ፓርቲ ኣባል ብዙ ጊዜ ሲጽፍ ኮካዎች መልስ ይሰጡታል፣ ኣናም ትንሽ ቆይቶ ያለው ነገር እውነት ሲሆን ኣፍረው እንካን ዝምታን ኣይመርጡም።

1. ዓምዶም ገብረስላሴ ይሁን ኣብርሃ ደስታ እና ሌሎች ህውሃትን የምንቃወም የትግራይ ልጆች በአማርኛ ስንጽፍ እናንተ የሽዋ ተላላኪዎች ናቹ የትግራይ ህዝብን ኣትወክሉም ይሉናል። ለትግራይ ህዝብ የምታስቡ ከሆነ ለምን በትግርኛ ብቻ ኣትጽፉም ይላሉ? እኛም ዝም ብለን ጊዜ ጠበቅን እና ኣሁን ኮካዎች ራሳቸው በአማርኛ መጻፍ ጀምረዋል እሰየው ነው፣ ኣሁን እኛም እነሱ እንዳሉት የሽዋ ተላላኪዎች ሊንላቸው ነው? ኣይደለም ነገር ግን የ ብአዴን የበረከት ተላላኪዎች የማለት መብት ኣለን። ለምሳሌ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው ኣውራ ኮካ ባለፉት ኣምስት ስድስት ወራቶች ብቻ ከሰላሳ በላይ ጹሁፎቹ በ አማርኛ ናቸው። ይባስ ብሎ ደግሞ ወይን መጽሄት በአማርኛ መጻፍ መጀመርዋ ነው።ስለዚህ ኮካዎች በአማርኛ የመጻፍ መብት ሲኖራቸው እኛ ግን የለንም፣ ለነገሩ ኣብርሃ ደስታ ኮካ መሆን የማሰብ መብትህን ኣሳልፈህ መስጠት ማለት ነው ብሎ የለም።

2. ዓምዶም ገብረስላሴ በኦሮምያ ለመጀመሪያ ጊዜ ኣመጽ ሲነሳ የጻፈ ጊዜ ኣንድ ስለ ዋጣ(ማሲንቆ) ብቻ ማውራት መጻፍ የሚወድ ያልበሰለ ኮካ ኣምዶም ገብረስላሴ የጻፈው ውሸት መሆኑን በትግርኛ ጻፈ። በሱ ቤት ኣምዶም ገብረስላሴ ውሸታም መሆኑን ለትግርኛ ተናጋሪዎች ለማስረዳት ነው። ጊዜ ለኩሉ ኣሁን ኦሮምያ ውስጥ ብዙ ሰው ተገደለ፣ታሰረ፣ታፈነ ኮካው ምን ይዋጠው፣ ይባስ ብሎ የኦሮሞ ህዝብ ተቃውሞ ኣስፈርቶት ለወደፊቱ ኣዲስ ኣበባ ለመኖር ኣሰቸጋሪ ነው በማለት በትግርኛ እንዲህ በማለት ጻፈ “ዓድኻ እዩ ዓድኻ” ማለት ኣገርህ ነው ኣገርህ!! እኛ የምናውቀው ደግሞ ኢትዮጲያ የምትባል ኣገር እንዳለች ነው ለካ ለኮካዎች ኣገራቸው ትግራይ ብቻ ናት።

3. ዓምዶም ገብረስላሴ ከሁመራ 85 የትግራይ ወጣቶች በሻእብያ ታፍነው እንደተወሰዱ ጻፈ፣ ኮካዎች እንደለመዱት ውሸታም በማለት ዓረናዎች ማለት ውሸታሞች ናቸው በማለት ኣሁንም በትግርኛ ጻፉ፣ መንግስት ስለታፈኑ የትግራይ ወጣቶች መግለጫ ሳያወጣ ዝምታን መረጠ፣ ድምጺ ወያኔ (ሬድዮም) ቶግ ቲቪ ስለታፈኑት ወጣቶች ዝምታን መረጡ። እንደማይሰማ የለ የአሜሪካን ድምጽ ሬድዮ ስለ ታፈኑት በይፋ ተናገረች፣ደስ የሚለው ቪኦኤ በትግርኛ ቋንቋ ፕሮግራ ማስተላለፍዋ ነው። ለምስክርነት የቀረቡት ደግሞ ታፍነው ካመለጡ ሁለት የትግራይ ወጣቶች ናቸው።ኣሁን ቪኦኤም በኮካዎች እውነቱን ስላጋለጠች እንደ ኢሳት ውሸታም መባል ጀምራለች። ኣሁንስ ምን ይዋጣቸው ከ ሀ እስከ ፐ ዓምዶም ገብረስላሴ ያለው ሁሉ እውነት ሆነ። እናማ ግዜ ለኩሉ የትግራይ ኮካዎች እውነቱን ድምጺ ወያኔ ፣ቶግ ቲቪ ወይም ኢቲቪ እስክትነግራቹ ኣትጠብቁ ኣለም ሰልጥናለች ከአለማችን ጋር ፍጥነታቹ ጨምሩ።

4. የዓምዶም ደስ የሚለኝ ባህሪው ኣንድ ነገር ሲጽፍ መልስ ኣለመስጠቱ ነው። ይህም ኮካዎች የማስታወስ ችግር ስላለባቸ ጊዜው ጠብቆ ይገባቸዋል ከሚል እሳቢ ይመስለኛል። እናማ ዓምዶም ኣንተ ቀጥል፤ጻፍ መልስ ኣትስጥ እኛም እናነባለን፣ ኮካዎች ግን የጻፍከው ሲያነቡ ቶሎ ስለማይገባቸው ልክ እንደ No War No Peace ፖሊሲ ጊዜ ስጣቸው። ሁሉም ነገር ቶሎ ኣይገባቸው ምክን ያቱም ከነሱ ጋር ያለው ሆዳቸው እንጂ ህሊናቸው እና የማሰብ ችሎታቸው ኣይደለም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.