የአንድ ህዝብ ጥንታዊ ታሪክና ማንነት እራሱ እንጂ ብልጣብልጥ መጤዎች ሊያውቁለት አይችሉም

 

we;qaitዜና ወልቃይት

ስለ ወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ የሚያውቅለት ተከዜን ተሻግሮ ያለው ጎረቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው/ለመሬቱ ስትሉ ትግሬ ሁኑልን;
ትግሬዎች አምርረው የሚጠሉት አማራ ህዝብ ጋር ምን አስለጠፋቸው፣ህዝቡን ጠልቶ መሬቱን ወዶ መቀላመጥ ምን የሚሉት ገገማነት ነው።ከጠሉ አለመድረስ ፣የጠሉትን ህዝብ ንብረት አለመመኘት ብልህነት ነው፣የሌለ ታሪክ እየፈጠረ ስለ ወልቃይት ጠገደ አማራ ህዝብ ታሪክ የሚያውቅለት ተከዜ ማዶ ያለው ጎረቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው የሚለው የሞኝ ፈሊጥ እራስን ማታለል እንጂ ጎረቤት ከባለቤቱ በላይ ሊያውቅ አይችልም ፣የአንድ ህዝብ ጥንታዊ ታሪክና ማንነት እራሱ እንጂ ብልጣብልጥ መጤዎች ሊያውቁለት አይችሉም ።

በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ጠለዴ፣ ጠለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጄል
ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው።Moges Alemu Azme Mile Dagnachew Eshetu

ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ ፕሮግራም በማለት አውግዘውት ነበር። ከነዚህ ካወገዙት መካከል ለምሳሌ ለመጥቀስ፤ አስገደ ገብረሥላሴ፣ ካህሳይ በርሄ (ዶ/ር ግንጽል)፣ ተሾመ ጉዶ፣ ሲሆኑ እነዚህ በህይወት ያሉ ሲሆን፣ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋእድ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዘርኡ ገሰሰ (አጋአዚ) ገሰሰው አየለ፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ ዘወንጀል በየነ፣ መሃረ ተክሌ ወዘተ እነዚህ ፕሮግራሙን በጠነከረ አቋም ስለተቃወሙ የተገደሉ ናቸው።

ተሓህት የፕሮግራም ዝግጅቱን ንድፈ ሃሳብ የጀመረው ገና በረሃ ሳይወጣ ማገብት ተብሎ በሚጠራበት ከ1966 ጀምሮ ነው። ይህንን ፕሮግራም በሃላፊነት ያዘጋጀው አረጋዊ በርሄ ሲሆን፣ ጥር 1967 ለወታደራዊ ስልጠና ኤርትራ፣ ስህል ወርደው ፕሮግራሙን በማጠናከር የተሰማሩት የትጥቅ ትግሉ መሪዎች አረጋዊ በርሄ፤ በዋና ሃላፊነት፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ አስፍሃ ሃጎስ፣ በህመም የሞተ፣ ዘርኡ ገሰሰ፣ በወያኔ የተገደለ፣ ሥዩም መስፍን፣ ሃይሉ /ነጠበ/መንገሻ ሲሆኑ ብዙ የጎደለው እንዳለ ተስማምተው በይደር ወደ ደደቢት ተዘዋወረ።

የካቲት 11፣ 1967 ታጋዮቹ ደደቢት በረሃ እንደገቡና የትጥቅ ትግሉ እንደተጀመረ፣ ግንባር ቀደም ተግባራቸው ሶስት ነጥቦች ላይ ነበር ትኩረት ይሰጠው።

1ኛ፣ የድርጅቱን ስም ማውጣት፣

2ኛ፣ ለወደፊቱ ለምትመሰረተው የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የግዛት ስፋት ከውጭ ሃገር፣ ሱዳን በሚገኘው መልኩ ማዘጋጀት፤

3ኛ፣ ፕሮግራሙን ለመጨረሻው ዝግጅቱ ታማኝ ታጋዮችን በማሰባሰብ ለሚከተሉት ሰዎች፣ ማለትም፣ አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር፣ ሥዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ስየ አብርሃ፣ ግደይ ዘርአጽዮን ወዘተ ሃላፊነቱ ተሰጠ። ለዚህ መሰናዶ ከበጌምድር ጠቅላይ ግዛት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ፣ ወልቃይት እንዲሁም ከወሎ ጠ/ግዛት፣ ራያና ቆቦ፣ ወልድያ፣ አላማጣ እስከ ላይኛው ሃሸንጌ ሃይቅ ድረስ በማጠቃለል የትግራይ መሬት ነው ተብሎ በመወሰን የፕሮግራሙን አቋም ደመደመ።

ይህ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ወደ 30 ገጽ የሚሆን ተባዝቶ በመጽሓፍ መልክ ተጠርዞ በብዛት ተያዘ። በሃላፊነት የጻፉት አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሥዩም መስፍን፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየ ናቸው። በየቦታው እንዲሰራጭም ተደረገ።
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ኢትዮጵያን ለመበታተን፣ ሕዝቧን በዘርና በጎሳ የከፋፈለ፣ አማራውን ደመኛ ጠላት ብሎ ያወገዘ ሆኖ የመጣና እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት የሆነ አስተሳሰብ ነበር።

አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው፣ ከሚለው ቀጥሎም ለብዙ ዓመታት ነፃ ሃገር ትግራይ ነፃነቷ ተገፎ በአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ አገዛዝ ወድቃለች፣ በማለት ብዙ ይተነትናል። በአጼ ዮሃንስ ዘመነ መንግሥት ሃይሏ በርትቶ በአካባቢዋ የነበሩትን ነገሥታት በቁጥጥር ስር አውላ ነበር። ይሁን እንጂ አፄ ዮሃንስ ከሞቱ በኋላ በዳግማዊ ምኒልክ አማካኝነት ትግራይ በሸዋው ማእከላዊ ግዛት ስር ወደቀች። ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው አማራው የመሳፍንት ቡድን እና ተከታዮቹ የትግራይን ነፃነት ገፈው የህዝቧን አንድነት ያናጉት። በግልጽና ስውር በሆነ ዘዴዎች (ሸዋዊ ዘይቤዎች) የትግራይ ህዝብ በድንቁርና፣ በበሽታ፣ በረሃብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት እያለ ይቀጥላል።

ከላይ የተጠቀስውና ሌላውን ጨምሮ ተሓህት የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራ ነው፣ ነፃ ሃገር የነበረቸው ትግራይ ሃገርህ በአማራ (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ሆና አንተ ለክፉ መከራ ተረግህ በማለት አመራሩ በሙሉና የተሓህት ታጋዮች ወደ ህዝቡ ተበታትነው ፖለቲካቸውን አስተማሩት። ማንኛውም የትግራይ ህብረተሰብ ይህ የምትናገሩት ሁሉ ፈጽሞ ከእውነት የራቀና የራሳችሁ የፈጠራ ፖለቲካ ነው። አማራ ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ አይደለም፣ ወንድሙና እህቱ እንጂ። ሁላችንም ተቃቅፈን በጋብቻ ተሳስረን በፍቅርና በሰላም የምንንሮር የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ነን። ከትወልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ፍቅርና ወንድማማችነትን እህታማችነት አታፍርሱብን። አማራ (ኢትዮጵያ) ትግራይን በቅኝ ግዛት ስር አድርጋለች የምትሉት ከየት ያገኛችሁት እንደሆነ እኛ አናውቅም። ትግራይ ዱሮም አሁንም የኢትዮጵያ የታሪክ ማእከል ናት በማለት የትግራይ ህዝብ ከገጠር እስከ ከተማ ተቃውሞ አደረሰባቸው። በዚህም ምክንያት የገጠርና የከተማ ኗሪው በቀን እና በሌሊት እየተለቀመ በሽብርተኞች ቡድን ተገደለ፣ ቤቱ ፈረሰ፣ ህፃናት በየቦታው ወድቀው ቀሩ። ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ከፋሽስቱ ጣሊያን ጋር የተዋጉ የትግራይ ኢትዮጵያዊ አርበኞች በወያኔ ትሓህት ከየቤታቸው እየተለቀሙ ሃለዋ ወያኔ ገብተው በጥይት እየተረሸኑ መስዋእትነት ከፈሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ፣ በ1969 የተሓህት መሪዎች ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃየ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሥዩም መስፈን፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ ተሰባስበው በትግራይ ውስጥ የሚኖረው አማራ፣ ኦሮሞና ሌላውም ከትግራይ ይውጡ፣ ትግራይ 2 ለትግራይ ህዝብ ብቻ ናት የሚል አዋጅ አስተላለፉ። ይህንን ሃሳብ ያልደገፉት ግደይ ዘርአጽዮን እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ብቻ ነበሩ።

በዚህ የዘረኝነት አጥር ውስጥ የገባው የተሓህት አመራር ከ1969 መጨረሻ በፕሮግራሙ ያካተተው የትግራይ መሬት ብሎ ያስቀመጠው ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ቃፍታ ላይ ማነጣጠር ጀመረ። በተቻለ መጠንም በፍጥነት ተቆጣጥረን በትግራይ ውስጥ ገብተው በተሓህት አመረር ስር መተዳደር አለባቸው የሚል እቅድ ያዘ። ከዚህ ቀደም ብሎ በአርከበ እቁባይ የተዘጋጀ ካርታ ከበጌምድር ጠ/ግዛት ከላይ የተጠቀሱትን ቦታዎ ች፣ ከወሎ ጠ/ግዛት ራያና ቆቦ፣ አላማጣ፣ ወልዲያ፣ አፍላ ደራ ለምትመሰረተው አዲሲቷ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትግራይ ሲካተቱ፣ በምእራብ በኩል ደግሞ ወልቃይት፣ ሁመራ ፀለምት፣ ፀገዴ ተጨምረው ትግራይ ከሱዳን ጠረፍ ጋር እንደትገናኝ፣ በደቡብ በኩል ደግሞ ወደውሃ ምላሽ ትግራይ እንድትሰፋ ሲወስን፣ እነዚህ ቦታዎች ሁሉ ለምና ሃብታም መሬቶች ናቸው። ይህንን ውጥን ለማሳካት በወልቃይት ፀገዴ ተሓህት ህዝቡን እያፈነ ማጥቃት ጀመረ።

የወያኔ/ህወሓት/ተሓህት መሰረታዊ የታሪክ ወንጀል
የወላቅይት ፀገዴ፣ ፀለምት፣ ሁመራ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ ለብዙ ሺህ ዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ታሪካዊ ቦታዎች የበጌምድር (ጎንደር) ግዛት መሬት ነው። ታሪክም የሚያረጋግጠው ይህ ነው።። በምንም ተአምር ከትግራይ ግዛት ጋር ግንኙነት የለውም። የሚገናኙበት ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊነት ነው። በጌምድርም ሆነ ትግራይ የአንዲት ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው። በሃይማኖትና በጋብቻ ተያይዘዋል። ይህ ደግሞ በሁለቱ ህዝብ ማካከል ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ውስጥም ያለ ነው። ኦሮሞው ከትግሬ፤ ትግሬው ከአማራ፣ አፋሩ ከጋምቤላው፣ ጉራጌው ከሌላው ዘር ጋር ወዘተ የተደባለቀ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በደም የተቆራኘና አንድ ህዝብ ነው።

አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ በመጠባበቅ የቆየው የተሓህት አመራር በየካቲት መጨረሻ በ1968 በድርጅቱ የተሰባሰቡት ታጋዮች ዲማ በተባለው በአጋሜ አውራጃ ውስጥ የዲማ ኮንፈረንስ በመባል የሚታወቅ ኮንፈረንስ በማካሄድ ከ150 የማይበልጡ ታጋዮች በአረጋዊ በርሄ ሊቀመንበርነት በሚመራ ስብሰባ ፕሮግራሙ ቀርቦ እንዲጸድቅ ቢጠይቅም ታጋዩ አልተቀበለውም። ይሁንና፣ ሊቀመንበሩ ጸድቋል ብሎ የድረጅቱ የፖሊሲ አቋም ሆኖ እስከመጨረሻው ቀጥሏል።

የተሓህት የሰሜን በጌምድር የወረራ ዝግጅት
ተሓህት ወደ ሰሜን በጌምድር/ጎንደር በቀጥታ ሃይሉን አሰባስቦ አልገባም። ምክንያቱም፡
1. በመጀመሪያ ጊዜና ሁኔታውን ማስተከካል ፈለገ፤
2. ኢህአፓ በአካባቢው በስፋት ይንቀሳቀስ ስለነበር በአቅምና በትጥቅ ጥራት ህወሓት ዝቅተኛ ስለሆነ፣ ኢህአፓዎቹ ይመቱናል፣ ያጠቁናል የሚል ስጋት ስለአደረበት፣
3. የወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ህዝብ አይቀበለኝም ብሎ በማመኑ፣ አቅሙን እስኪያጠናክር መዘግየቱን እንደ አማራጭ ወሰደ።
ቢሆንም ግን፣ ተሓህት በድብቅ በ1969 መጨረሻ ወደ ፀገዴና ፀለምት መሽሎክሎኩን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ ደጀና ውስጥ ሽሬላ ተብላ በምትታወቀው ትንሽ ከተማ የተሓህት ታጋዮች ቅዳሜ ቀን ህዝቡን ሲያንገላቱ በነበሩበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ቡድን ሁለቱን የተሓህት ታጋዮች በገበያው መሃከል ገደሏቸው።
በታህሳስ 1972 በሻእቢያና በጀብሃ፣ በወያኔና በኢህአፓ መካከል በተነሳው ጦርነት በኢህአፓ በሰነዘረውጥቃት ተበታትነው ሱዳን ገቡ። በወልቃይት ፀገዴ ፀለምት የኢህአፓን ሠራዊት በበላይነት ሲመሩት የነበሩት ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ታደሰ ቅንጥሾ ወዘተ አስቀድመው ለወያኔ ህወሓት እጃቸውን ስለሰጡ፣ እየመሩም የኢህአፓን ሠራዊት እንዲጠቃ አደረጉ። በጥቃቱም ብዙዎቹ ተገደሉ፣ ተማረኩ፤ የተማረኩትም ተረሸኑ። ለዚህ ተጠያቂቆቹ ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ናቸው።

ይህ ጊዜ ወያኔ ህወሓት ፍላጎቱ የተሳካበት ወቅት ነበር። አሁን ያለው የህወሓት አመራር በ1971 የካቲት 5 ቀን የተመረጡት፤ ስብሃት ነጋ፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር፤ አረጋዊ በርሄ፣ ወታደራዊ አዛዥ፤ አባይ ፀሃየ፤ ግደይ ዘርአጽዮን፤ ስዩም መስፈን፤ መለስ ዜናዊ፤ አውአሎም ወልዱ፤ አርከበ እቁባይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤ ተወልደ ወ/ማርያም፤ ገብሩ አስራት፤ ስየ አብርሃ፤ ጽድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ በወያኔ የተገደለ፤ አስፍሃ ሃጎስ፣ ታሞ የሞተ ናቸው። የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩና ሁሉን ትእዛዝ የሚሰጡት ደግሞ፣ ስብሃት ነጋ፤ መለስ ዜናዊ፤ አረጋዊ በርሄ፤ አባይ ፀሃየ፤ ስዩም መስፍን፤ ግደይ ዘርአጽዮን ናቸው። በወልቃይት ፀገዴ ጥቃቱን ያቀነባበሩት አመራሮች፤ ስየ አብርሃ፤ አርከበ እቁባይ፤ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፤ ዘርአይ አስገዶም፤ አውአሎም ወልዱ ናቸው። እነዚህ በሰሜን በጌምድር፣ ወልቃይት ፀገዴ ትእዛዝ ይጠባበቁ የነበሩ ሲሆኑ፤ ይህንን ሁሉ በበላይነት የመራው ስብሃት ነጋ ሲሆን፤ የቅርብ ተባባሪዎቹ ደግሞ አባይ ፀሃየና አርከበ እቁባይ ነበሩ።

ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት አመራር የሰሜን ጎንደር ኗሪ ሰላማዊ ህዝብ ለማጥቃት የታየው ሁኔታ አመራሩ ዝግጅት ያደረገው ነበር። በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን

ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።

ሁመራን በተመለከተ ወያኔ ተሓህት/ህወሓት የትግራይ ነው ቢልም በወቅቱ እስከ ግንቦት 1983 የኢትዮጵያ ምድር ጦር ሰፊ ጥበቃ ስለነበረው፣ ወያኔ ህወሓት መሬቱን የተቆጣጠረው አዲስ አባባን በያዘበት ጊዜ ነው። ወያኔ ህወሃት በትግ ላይ በነበሩበት ጊዜ 17 ዓመታት ሙሉ ሁመራ አልገባም፣ አልተቆጣጠረም። በአካባቢውም ድርሽ አላለም።

ከላይ የተጠቀስው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መኮንን ዘለለው የህዝቡን አንበገርም ባይነትና የሰሜን በጌምድር አማሮች ነን ባይነት፣ ለወራት የቆየበትን ሪፖርት ለህወሓት አመራር ለስብሃት ነጋና ሌሎችም አቀረበ። ስብሃት ነጋ በመኮንን ዘለለው ላይ ወረደበት፣ ወዲያውኑም ከሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊነት አወረደው። በዚህ ክስተት ባይታሰርም የአእምሮ በሽታ ሰለባ በማድረግ አሰቃዩት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.