ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ወይስ ዲሞክራሲያዊ ድንቁርና? በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ!!!

ዶ/ር ሰንበቴ ቶማ/ዶማ/ ከግራ መጋባት ወደ መናከስ እና ማናከስ ተሸጋግሯል… ሰንበቴ ቶማ ተቋሙን አገማ!!!

ቦቸራ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

tolaዶ/ሩ ባለፈው በዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ የተጻፈውን ቅሬታ እና ጥቆማ ከተመለከተ በኋላ ጉድለቶቹን ከማስተካከል ይልቅ የተናጠልና የጅምላ ጥቃት ዘመቻ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከፍቷል፡፡ መንግስት ለመሆኑ እንደራሱ መስሚያቸው ጥጥ የሆነውን ነው እንዴ የሚሾመው? መንግስትን መሳደብ ፈልገን ሳይሆን እንዲያው ከሰማ ብለን እንጂ፡፡ ቀበሌ መስሚያው ጥጥ ወረዳው መስሚያው ጥጥ ዞኑ መስሚያው ጥጥ ክልሉ መስሚያው ጥጥ እንዲያው ግን…..??? ያው ነው፡፡

ቆይ እኛ ያልገባን የመልካም አስተዳደር ችግር ይፈታልን፣ አድሎ እና ጠባብ ብሔርተኝነት ይወገድ እንዲሁም የመንግስትና የሕዝብ ሀብት መበዝበዙ ይቁም ማለት ወንጀል ነው እንዴ? በኛ እምነት የጥሩ ዜጋ መገለጫ ነው፡፡ ጥቂት ግለሰቦች ስልጣንን መከታ በማድረግ ያለአግባብ መበልጸግና የሌሎችን መብቶች መርገጥና መጣስ ማብቂያ ሊበጅለት ይገባል፡፡ የመንግስት ትልቁ ችግር በኛ እምነት በፖለቲካ ጭምብል ለብሰው አባለት ነን በሚሉ ሆዳሞችናንና ያለአግባብ መጠቀም የሚፈልጉ ገለሰቦችን መለየት አለመቻሉ ነው፡፡ እነዚህ ነገ የሥርዓቱ አደጋዎች ናቸው፡፡ ከወዲሁ ሀይ ሊባሉ ይገባል፡፡ የተቋሙ ሥራ መከናወን ያለበት በኛ እምነት ሕግንና አሰራርን መሰረት በማድረግ ነው ሆኖም እየሆነ ያለው በግለሰቦች በጎ ፈቃድ እና ፍላጎት ነው፡፡

የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረገው መቼ ነው? ለነገሩ አንዳንዶቹ ከጥሩ ሀይስኩል ጋር የሚወዳደሩ አይደሉም፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰቡን በተለይም መምህራኑን ማስፈራራት፣ ማግለል፣ ማፈን እና ማጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በነገራችን ላይ ጥቂት ሆዳሞችንና ደደቦችን ከተቋሙ ላይ ለማንሳት ጠመንጃ ማንሳት ያስፈልገን ይሆን? የሚገርመው ዶ/ሩ ወደ ተቋሙ ከመጣ በኋላ አንድም ፕሮጀክት አልተጠናቀቀም ያጠናቀቀው ነገር ቢኖር የዝርፊያ በሮችን አስፍቶ መክፈትን ነው፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች እንደነገሩን ከሆነ በተማሪዎች ቀለብ እና መመገቢያ ካፍቴሪያ ዙሪያ የሚሰራው ሙስና ቅጥ ያጣ ነው፡፡

የዪኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ይህ ችግር በአስቸኳይ ሊቀረፍ ባለመቻሉ ተስፋ ሳይቆርጥ ለትምህርት ሚኒስቴር እና ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ኃላፊዎች በአካል መጥተው ቅሬታችንና ጥቆማችንን እንዲያዳምጡ እንዲሁም እንዲመረምሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.