አዎ! የድሮው ስርዓት ናፋቂ ነኝ !! (ስንታየሁ ቸኮል)

ምክንያቴ ደግሞ

  1. Abay Tseyahe 56-satenawበድሮው ስርዓት ኢትዮዽያ በዓለም ታልቋ ወደብ አልባ ሀገር አልነበረችም።
  2. በድሮው ስርዓት እነ ሱዳን የፈለጉትን መሬት በፈለጉት መጠን ያለ ጥያቄ መውሰድ አይችሉም ነበር።
  3. በድሮው ስርአት እነሱዳን አንድ ኢትዮጵያዊ በስህተት ቢገድሉ በምላሹ ሀምሳ ሱዳናዊ ይጠየቁ ነበር፡፡
  4. በድሮው ስርዓት መታወቂያ ላይ ብሄሬን እንድፅፍ አልገደድም ነበር።
  5. በድሮው ስርዓት 97% የሚሆኑት የአገሪቷ የሚሊተሪ፣ ደህንነት እና ፓሊስ መኮንኖች የሚሾሙት በአገር ወዳድነት እና ብቃት እንጂ የአንድ አናሳ ብሄር አባል በመሆን ብቻ አልነበረም።
  6. በድሮው ስርዓት ንግድ ለመጀመር ከገዥው ብሄር እናም ገዠው ፓርቲ ስር ስር መለጠፍ አይጠበቅብኝም ነበር።
  7. በድሮው ስርዓት የግል ፣ የከተማ መሬት እና የከተማ ቤት የገዥው ብሄር ወይንም የገዥው ፓርቲ አባል የሆነ ሰው ስለፈለገ ብቻ ከባለቤቱ ላይ በጠራራ ፀሀይ ተነጥቆ mአይሰጠውም ነበር።
  8. በድሮው ስርዓት የሐገሬው ዜጋ ገበሬ ተፈናቅሎ ለም mመሬቱ ለአረብ፣ ለህንድ፣ ለቻይና እና ኮሪያ ሩዝ እያመረቱ ከሀገር እንዲወጣ አይሰጥም ነበር።
  9. በድሮው ስርአት <<ኢትዮጵያ ትቅደም>> እንጂ ትግራይ ትቅደም አይባልም ነበር፡፡ እና የድሮውን ስርአት ብናፍቅ ይገርምሃል እንዴ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.